Get Mystery Box with random crypto!

የልብ ነገር ክፍል ዘጠኝ (ፉአድ ሙና) *** ቃ ቃ ቃ! እንደ እቃቃ ህይወት ሲንቃቃ! ቃ! ቃ! | ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች

የልብ ነገር
ክፍል ዘጠኝ
(ፉአድ ሙና)
***

ቃ ቃ ቃ!
እንደ እቃቃ
ህይወት ሲንቃቃ!
ቃ! ቃ! ቃቃ! ቃቃቃ!

ጓ ጓ ጓ!
ልብ ሲደቅቅ
ሲሰበር ከአንጓ!
ጓ! ጓ! ጓጓ! ጓጓጓ!

***
ነገሩ የትዕግስት ጉዳይ ነው እንጂ የማይደርስ ቀን .... የማይነጋ ለሊት የለም። እነሆ ፈሪሀም ሀገሯ ገብታለች። አራት አመት ሙሉ ከናፈቋት ወዳጆችዋ ጋር በሰላም ተገናኝታለች። አባቷም የቋመጠለትን እድል አገኝቷል። ሰርግ የሚመስል ድግስ ደግሶ ምርቃቷን አክብሯል። ይህ ሁሉ ግን ለእኔ ስሜት አይሰጥም .... ምክንያቱም የቀድሞው ፉአድ አይደለሁም። ለፈሪሀ ፍቅር የተንበረከከው ፉአድ ከጉልበቱ ላይ አቧራውን አራግፎ ከተንበረከከበት ተነስቷል። ፈሪሀን ያክል ፍቅሩ ላይ ሴራ ጎንጉኗል።

ፈሪሀ አይኖቼን በትኩረት ተመለከተቻቸው።
«ቀልደኛ! .... አሁን በሁለተኛ ሚስት ይቀለዳል?»
«ቀልዴን አይደለም ፌሪ .... ሁለተኛ ሚስት አግብቻለሁ።»
«ምን እያልክ ነው?» ፊቷ ወደ ቲማቲምነት መቀየር ጀምሯል።
«እንዳልኩሽ ነው።» ግድየለሽ ሆኛለሁ።
«የኔ ውድ .... አንተ አታደርገውም። እኔ አውቅሀለሁ ፋሚ! አንተ እኔ ላይ ሌላ ሴት ማግባት ቀርቶ አታይም ውዴ! አውቅሀለሁ የኔ ጌታ አንተ አታደርገውም።» አይኖቿ በእንባ እየተሞሉ ነው።
«አዝናለሁ ፌሪ .... አግብቻለሁ።»
«በምን ልመንህ? አንተን አውቅሀለሁ። እንደዚህ አታደርግም በፍፁም! በአላህ ቀልዴን ነው በለኝ!»
«አራት አመት ከባድ ነበር ፌሪዬ .... ከሁለት አመት በላይ መታገስ አልቻልኩም።» ስልኬን ከፍቼ የእኔ እና የኢክራምን ፎቶ በሩቁ አሳየኋት። ፊቷ ላይ እሳት ተንቀለቀለ። የእንባዎቿ ዘለላዎች አፏ ውስጥ ቀድሞ በገባ ተሽቀዳደሙ። ሰውነቷ መርገፍገፍ ጀመረ።
«ፉአድ ሙና!» በሳግ በታፈነ ድምጿ ጮኸች።
«አቤት?»
«ከአጠገቤ ጥፋ!»
«እሺ!» ተነሳሁ።
«የት አባህ ነው የምትሄደው? .... ተቀመጥ!» ተንደርድራ የመኝታ ክፍሉን በር ቆለፈችው። ስትመለስ በጥፊ ወለወለችኝ። ደረቴን ትከሻዬን በእጆቿ እየደበደበች ማልቀሷን ቀጠለች። መቧጨር እንዳትጀምር በጥንቃቄ እየጠበቅኳት ነው። ልብሴን በሁለት እጆቿ እንደጨመቀች ደረቴ ላይ ተጋድማ ማልቀሷን ቀጠለች። ማልቀሱ ሲደክማት ወደ መሳደብ ተመለሰች።
«ይኼኔ ከድሮም ትማግጥብኝ ነበር!
ውሻ ነህ! ውሻ ነህ!
ምን ጎደለህ ከእኔ?
ስድ ነህ! ልክስክስ ነህ!» ማቆሚያ የሌለው ስድብ አወረደችብኝ።
«ብርጭቆ እንደሰበረ ሰው ይቅር በይኝ ትላለህ ደግሞ! ወይኔ ፈሪሀ! እኔ እዚያ ባንተ ናፍቆት እሰቃያለሁ .... አንተ እዚህ ከማንም ጋር አልጋ ለአልጋ ትንከባለላለህ! ቆሻሻ! ቆሻሻ ነህ!»
ደረቴን በስስ መዳፏ ትደበድባለች።
«የአንድ ቀን ስህተት እኮ አይደለም ይኼ! አስበህ .... ወስነህ .... ሽማግሌ ልከህ እኮ ነው ያደረግከው! ቢያንስ እንዴት አታማክረኝም? ስሜትህ አናትህ ላይ ከወጣ ተመለሽ ብትለኝ እመጣ አልነበረ ወይ? እሱን ምክንያት አድርገህ ሴሰኝነትህን ነው ያረካኸው! ሰው ሚስቱን አጥቶ ነው ብሎ ይረዳኛል ብለህ .... ሆን ብለህ ነው እድሉን የተጠቀምከው! ውሻ ነህ! ቆሻሻ ነህ!»
ዝም ብዬ የሚወርድብኝን ስድብና ድብደባ እቀበላለሁ።
«ለመሆኑ ሽማግሌ ማን ሆነልህ? አባትህ ለዚህ ሴሰኝነት እሺ ብለው ሽማግሌ ሆኑ? ወይስ መስጂድ የሰበሰብካቸው አራት ማግባት እያሉ የሚውሉ ሴሰኛ ወንዶችን ይዘህ ሄድክ? ሚስትየውስ ለራሷ ክብር የላትም ወይ? እንዴት ሰው የሰውን ትዳር ሊያፈርስ ይገባል? እንዴት ባል ያለው ወንድ ላግባ ትላለች? ወይስ ሸ ር ሙ ጣ ነው ያገባኸው?»
ለቅሶዋ ጉልበት ማጣት ድምጿም መዘጋት ጀመረ።
«እሺ ብሎ ግን ቆ መ ል ህ? አካልህ ታዘዘህ ወይ? ይኼኔ እኮ እዚህ አልጋዬ ላይም ይዘሀት መጥተህ ይሆናል! ውሻ! ልክስክስ! ልክስክስ ነህ!»
እቅፍ አደረግኳት። ጭምቅ!
«ልቀቀኝ! ልቀቀኝ አልፈልግም! ሂድና ሸ ር ሙ ጣ ህን እቀፍ! ደረትህ ይሸታል! እሷን ያቀፍክበት ይገማል!»
«ይቅርታ ....» አልኩኝ በሚንቀጠቀጥ ድምፅ!
«ለምኑ ነው ይቅርታ? ልብሴ ላይ ውሀ የደፋህብኝ ነው እንዴ የመሰለህ?»
ፌሪ የመኝታ ክፍሉን ቁልፍ ይዛ ስትሰድበኝና ስትደበድበኝ ቆየች። ሁሉም ሰለቸኝ።
«ይኼ የተፈቀደልኝ ነው! መብቴን ነው ያደረግኩት! ይቅርታ የጠየቅኩሽ ስለምወድሽ ነው። ስህተት ስለሰራሁ አይደለም!»
«ትወደኝ የለ እንዴ! ድንቄም መውደድ!»
ቁልፉን ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠችው።
«ይኸው ውጣ! ሸርሙጣህ ጋር ሂድ! Bitch!»
ቁልፉን አንስቼ በሩን ከፈትኩ።
«ንገራት ..... እንደምገላት ንገራት እሺ! ቤቴን በትና እንደማልተዋት ንገራት! Son of a bitch!»

ከቤት እንደወጣሁ መኪናዬ ውስጥ ሆኜ ኢክራም ጋር ደወልኩ።
«ኢክሩ .... »
«ወዬ ፉዬ እንዴት ሆንክ?»
«ኧረ ስሰደብ እና ስደበደብ ነው ያረፈድኩት!»
«ቤቱን ለቅቃ ሄደች ወይስ እዛው ናት?»
«ኧረ ምን ትሄዳለች .... እዛው ተቀምጣለች። እያለቀሰች ነው።»
«በቃ እኔ ጋር ና ..... ባልየው!» ሳቀች።
«የት ነሽ?»
«ቤት ነኝ እወጣለሁ .... የተለመደው ቦታ ቢሆንስ?»
«ይቻላል። ከሰሚር ጋር እመጣለሁ።»
ሰሚር ጋር ደውዬ አነሳሁትና ወደ ኢክራም ሄድን።
«ባ ሌ!» ኢክሩ በደስታ ተፍነከነከች።
«ሚስትየው!» የደረሰብኝን ድብደባ በኢክሩ እቅፍ አበረድኩ።
«በቃችሁ .... ሆድ አታስብሱኛ!» ሰሚሮ አለያየን። ከከተማችን ታዋቂ ሆቴሎች መካከል ከአንዱ ተሰይመናል።
«ምነው ግን በጠዋቱ አረዳሀት?» ሰሚሬ ይስቃል።
«መርዶ በጠዋቱ ነዋ የሚርረዳው!» ኢክሩ መለሰች።
ኢክሩዬ ነፃነቴ ሆናለች። የምላትን የምትሆን የፍላጎቴ ጥግ! ሳያት እረጋጋለሁ።
«ፉዬ ግን ምን አሰብክ? ዛሬ ማን ጋር ልታድር ነው?» ይስቃል።
«ያው ሁለተኛ ሚስቱ ጋር ነዋ! ሁለት ሳምንት አብረው አደሩ አይደል!»
«አንቺ ደግሞ ለእሷ የዋሸነውን አመንሽው እንዴ? አልተጋባችሁም እኮ ገና!»
«እጠይቅሻለሁ እያልኩ ነበር። ባባ የለም እንዴ? ወደ ቤት ከቸኮልሽ ቆየሳ!»
«ከልብ ካለቀሱ ሲባል አልሰማህም? በእህቶቼ እያሳበብኩ ነው ‘ባክህ!»

ምግቡ ቀርቦልን በልተን እንደጨረስን እቅድ ማውጣት ጀመርን።

«ለጊዜው ነገሩ እስኪለይለት ..... እስክትፈታት እሷ ጋር ሁን! ባየችህ ቁጥር ስለምትበሳጭ ፍቺው ይፈጥናል!» አለ ሰሚር!
«እስኪ እናያለና! ግን ‘ባክህ ይኼኔ እስካሁን ሻንጣዋን ጭና ቤተሰቦቿ ጋር አዳማ ደርሳ ይሆናል።»
ኢክሩ መዳፎቿን እያማታች! «ግልግል ነዋ!» አለች።
ሰሚር በግርምት እያያት «ግን ሴቶች እርስ በርስ ስትጨካከኑ ለከት የላችሁማ!» አለ።
«በምንወደው ቀልድ ስለማናውቅ ነዋ!»
ኢክራም ዛሬ ሳቅ ሳቅ ብሏታል። የለፋችበትን ሰው ..... ፉአዷን የሷ ብቻ የምታደርግበት ቀን ከፊቷ ተደቅኗል። ለከፈለችው የትዕግስት መስዋዕትነት ራሷን እያመሰገነች ይመስላል።

ለጊዜው ፈሪሀ ጋር እንድቆይ ተስማምተን ከሆቴሉ ወጣን። ቢሮ እንግዳዎች እየጠበቁኝ ስለነበር ከኢክሩ ጋር ተሰነባበትን። ሰሚር ጋቢና ተቀምጦ በሀሳብ እንደተዋጥኩ እየነዳሁ ነው። የኢክራም መኪና ከፊታችን ይታየኛል። መገንጠያው ጋር ስንደርስ የኢክራም መኪና ወደቀኝ እኛ ደግሞ ወደ ፊት ሄድን። ከመቅፅበት ከባድ የግጭት ድምፅ ሰማን። ጓ! ጓ! ጓጓ! ጓጓጓ!