Get Mystery Box with random crypto!

«ምንሼ?» «ግጭት ይመስለኛል!» «ኢክሩ በታጠፈችበት በኩል እኮ ነው!» «የምርህን ነው?» « | ጣፋጭ ታሪኮችና ወጎች

«ምንሼ?»
«ግጭት ይመስለኛል!»
«ኢክሩ በታጠፈችበት በኩል እኮ ነው!»
«የምርህን ነው?»
«አዎ .... እስኪ አየት አድርገን እንለፍ!»
ማዞሪያ ጋር ስንደርስ አዙረን ወደ ኋላ ተመለስን። ኢክሩ በታጠፈችበት በኩል የትራፊክ መዘጋጋት ተፈጥሯል። ከርቀት ሰው ከቦ ይመለከታል። ቆመጥ የያዙ ፖሊሶች ሲሮጡ ይታየናል።

ሰሚሬ አንዱን ህንፃ እያሳየ «ለምን መኪናችንን እዚህ ፓርክ አናደርግም?» አለ።
«አዎ የሚለቅ አይመስልም ጃሙ!»
መኪናችንን ህንፃው ስር ፓርክ አድርገን ከመኪናችን ወረድን! ለማንኛውም ብዬ ኢክራም ጋር መደወል ጀመርኩ!

ይቀጥላል!
.
@Ethiopianislamic
@Ethiopianislamic