Get Mystery Box with random crypto!

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_orthodox — የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_orthodox — የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopian_orthodox
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 30.48K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡
ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot
Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 37

2022-09-23 11:55:50 ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበርን በማስመልከት መግለጫ ሰጡ
***

ስከረም ፲፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
""""""""""""""""""""""""""""""""
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
***

ፁዕ አቡነ አብርሃም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበርን በማስመልከት ከመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ከአቢይ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል።

መስቀል የሰላም ምልክትና አርማ መሆኑን በመግለጫቸው የጠቀሱት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በዓላችንን ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቻችንን በሚገባ አጠናቀናል ብለዋል።

ቤተክርስቲያን የሰላምና የህግ ምንጭና ባለቤት ነች ያሉት ብፁዕነታቸው በዓላችንን በሰላም ለማክበር የምንችለው ወቅታዊውን የአገራችንን ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ከጸጥታ አካላት ጋር ተናበንና ተግባብተን መስራት ስንችል በመሆኑ በጋራ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

በበዓሉ ወቅት ህውከት ቀሰሰቃሽ መልዕክቶችን በቲሸረሰቶች ላይም ሆነ በባነሮች ላይ ይዞ መገኘት እንደማይፈቀድ የገለጹት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚከተሉትን ዋና ዋና  ነጥቦች በመግለጽ መግለጫቸውን አጠቃለዋል።

ቤተክርስቲያን የህግና የሰላም ባለቤት እንደመሆኗ መጠን የመንግስትን ህጎችና መመሪያዎች ማክበርና ማስከበር የቤተክርስቲያን ተቀዳሚ ሥራዋ መሆኑን በመገንዘብ መንግስት በህገ መንግስቱ የደነገገውን የፌዴራል ሰንደቅ ዓላማ ወይም የቤተክርስቲያናችንን ዓርማ ብቻ በበዓሉና በዝግጅቶቻችን ላይ በመጠቀም ህግና ሥርዓት አክባሪነታችንን በተግባር  ማሳየት ይገባል። ከዚህ ውጪ የሆነ ምንም ዓይነት አርማም ሆነ ሰንደቅ አላማ መያዝ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

በቲሸርቶች፣በባነሮች እና በትርኢቶች ላይ ሁሉ ሌሎች ወገኖችን የሚያስከፉና ህውከት ቀስቃሽ የሆኑ ጥቅሶችን መጠቀም ከሥነ ምግባር ውጪ ከመሆኑም በላይ ለህውከትና ግርግር መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

ወደ መስቀል አደባባይ በሚደረግ ጉዞ ሁሉ ተደጋጋሚ ፍተሻ የሚደረግ መሆኑን ማወቅና የሚደረገው ፍተሻም ለደህንነታችን ተብሎ የሚደረግ ፍተሻ መሆኑን በመገንዘብ መላው ህዝበ ክርሰቲያን ራሱን ለፍተሻ ዝግጁ ማድረግና ፍጹም በሆነ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ለፍተሻ መተባበር እንደሚገባው በመረዳት የጸጥታ አካላትን መተባበር እንዳለበት አሳስበዋል።

አጠራጣሪና ለጸጥታ ስጋት የሚሆኑ ነገሮች ሲያጋጥም በቦታው ለተመደቡ የሥነሥርዓትና የጸጥታ አስከባሪ አባላት ወይም ለፖሊስ አካላት በመጠቆም  ክርስቲያናዊ ኃላፊነታችንን መወጣት ይገባናል።

በቤተክርስቲያናችን ማዕከላዊ አሰሰተዳደርና በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ተዘጋጅቶ ከሚሰራጨው መጽሔትና ብሮሸር ውጪ ምንም ዓይነት የህትመት ውጤት ስለማይሰራጭ ከእነዚህ ውጪ የሆኑ የህትመት ውጤቶችንና በራሪ ወረቀቶችን ይዞ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው።ይዞ የተገኘም በህግ ተጠያቂ ይሆናል።

ከመስቀል አደባባይ ውጪ በአድባራትና ገዳማት የሚከበሩ የመስቀል ደመራ በዓላትም በሰላማዊ መንገድ ተከብረው ማለፍ ይችሉ  ዘንድ ሁሉም ህዝበ ክርስቲያን ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር እና በመረዳዳት መሥራት እንደሚገባቸው  ተገንዝበው ህውከት ቀስቃሽ  ከሆኑ መልዕክቶች  በመታቀብ እና ህጋዊ ያልሆኑ ሰንደቅ ዓላማዎችን ባለመጠቀም ጭምር የበዓሉን ሰላማዊነትና የመስቀሉን ዓላማ መሰረት ያደረጉ  ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን የተላበሱ እንቅስቃሴዎች እንዲያደርጉ ብፁዕነታቸው አሳስበዋል።

በመጨረሻም ለመላው ኦርቶዶክሳዊያን በዓሉ የሰላም ፣የፍቅ፣የአንድነት፣የስምምነትና የደስታ በዓል እንዲሆን በመመኘት መግለጫቸውን አጠናቀዋል።

ኢኦተቤ-ሕ/ግ/መ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
1.3K views08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 07:20:01
@Ethiopian_Orthodox
2.8K views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 07:20:01 መስከረም ፲
ጼዴንያ ማርያም


ጼዴንያ በምትባል ሀገር ማርታ የምትባል ደግ ሴት ነበረች፡፡ ይህች ደግ ሴት በቤቷ ትልቅ አዳራሽ ሠርታ እንግዶችን እንደ አባታችን አብርሃም ተቀብላ አብለታ አጠጥታ ማደሪያ ቦታም ሰጥታ ታስተናግድ ነበር፡፡ አባ ቴዎድሮስ የሚባል ኢትዮጵያዊ መነኩሴ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ መሽቶበት ከማርታ ቤት በእንግድነት አደረና ጠዋት ሊሄድ ሲነሣ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚሄድ ሲነግራት ‹‹የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተህ አምጣልኝ ዋጋውን ልስጥህ›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ገንዘቡን ሥዕሉን ሳመጣልሽ ትሰጪኛለሽ›› ብሏት ሄደ፡፡ ኢየሩሳሌምም ደርሶ ቅዱሳት መካናትን ተሳልሞ ሥዕሉን ረስቶ ሳይገዛ ሲመለስ «አደራ ጥብቅ አይደለምን? ያቺ ሴት አደራ ያለችህን ለምን ረሳህ» የሚል ድምፅ ሰማ፡፡ በጣም ደንግጦ ተመልሶ ሄዶ ገዝቶ በረሃ በረሃውን መጓዝ ጀመረ፡፡ በመንገድም እየተጓዘ አንበሳ ሊበላው እየሮጠ ወደ እርሱ ሲመጣበት አየ፡፡ መነኩሴው አንበሳውን ከመፍራት የተነሣ ደነገጠ፣ ተንቀጠቀጠ ደንግጦ ቁሞ ሳለ ያች ሥዕል ከአንበሳው ጩኸት ሰባት እጅ በሚበልጥ አስፈሪ ድምፅ ጩሃ ተናገረች፡፡ ያን ጊዜ አንበሳው ደንግጦ ፈጥኖ ሸሸ፡፡ መነኩሴውም መንገዱን ቀጠለ፡፡ በመንገዱም ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ወጥተው ወንበዴዎች ሊቀሙትና ሊገድሉት ከበቡት፡፡ ከሥዕለ ማርያሟም እንደ መብረቅ ያለ ታላቅ ቃል ወጣ፡፡
ወንበዴዎችም እጅግ ፈርተው ሸሽተው ከጫካው ውስጥ ገቡ፡፡ ያም መነኩሴ እነኚህን የሚያስደንቁ ተአምራት በተመለከተ ጊዜ በልቡ «ለእኔ ረዳት ትሆነኝ ዘንድ ወደ ሀገሬ ይዣት እሄዳለሁ እንጂ ለላከችኝ ሴት አልሰጥም» ብሎ ወደ ሀገሩ ሊሄድ በመርከብ ተሳፈረ፡፡ በባሕር ላይም ሳለ ጽኑ ነፋስ ተነስቶ መርከቡን እየገፋ ማርታ ወዳለችበት ሀገር ወደ ጽዴንያ ዳርቻ አደረሰው፡፡ ማደሪያም ስለሌለው ወደ ደጓ ሴት ወደ ማርታ ቤት ከእንግዶች ጋር አብሮ ገብቶ አደረ፡፡ ሲነጋ ወጥቶ ሊሄድ ከደጃፍ ሲደርስ ደጃፉ ጠፍቶት ከአጥሩ ሲታገል ዋለ፡፡ ማርታም «አባቴ ያመመህ የደከመህ ትመስላለህ ዛሬ ደግሞ እዚህ እደርና ነገ ትሄዳለህ» አለችውና አደረ፡፡ በሁለኛውም ዕለት እንደ መጀመሪያው ቀን በሩን አልፎ መሄድ አቃተውና እዚያው ማርታ ቤት አደረ፡፡ በሦስተኛው ቀን መውጣት ፈልጐ አሁንም ከአጥሩ ጋር ሲታገል አይታ «አባቴ የሆንከው ምንድነው? እነሆ ዛሬ ሦስተኛ ቀንህ ነው» አለችው፡፡
መነኩሴውም «ይህችን ተአምረኛ ሥዕል አልሰጥም ብዬ ነው፡፡ እኔኮ ሥዕል ከኢየሩሳሌም ግዛልኝ ያልሽኝ መነኩሴ ነኝ» ብሎ ሥዕለ ማርያምን አውጥቶ ሰጣት፡፡ እርሷም እጅግ በጣም ተደስታ እግዚአብሔርን አመሰገነች፡፡ በሥዕሏም ፊት ሰግዳ ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ምስጋናን አቀረበች፡፡ ተቀብላም ሥዕል ቤት አሠርታ በክብር አስቀመጠቻት፡፡ ይህችም ሥዕል ቅዱስ ሉቃስ የሳላት ናት፡፡ ሥጋ የለበሰች ትመስላለች፡፡ ከፊቷም ወዝ ይንጠባጠባል፡፡ በዚህችም ሥዕል ብዙ ተአምራት ተደረገ ሕሙማን ተፈወሱ፣ ዐይነ ስውራን ማየት ቻሉ፡፡ በዚያ ዘመን የነበረው ሊቀ ጳጳስ ተአምሯን ሰምቶ ሥዕሏ ወደ ማርታ ቤት የገባችበት ዕለት መስከረም ፲ ቀን እንዲከበር ሥርዓት ሠራ፡፡ ይህም በዓል በቤተ ክርስቲያናችን ሁልጊዜ ይከበራል፡፡
የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክ ፍቅሯን ጣዕሟን ታሳድርብን፣ ልጇ አምላካችን በጸሎቷ ይማረን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2.7K views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-18 12:48:23 ----------------------------
"ቢፈልግባትም" በዘማሪ ቀሲስ ዳዊት ፋንታዬ

ቢፈልግባትም መልካሙ ገበሬ
አልተገኘባትም ከበለስዋ ፍሬ፤
            
ለስልሶላት ነበር ሃይማኖት መሬቱ፤
ተቀጥሮላት ነበር አጥር ሥርዓቱ፤
ተነቅሎላት ነበር ድንጋይ ፈተናዋ፤
ፍሬ ግን ታጣባት በመጨረሻዋ፤
            
ፍሬ የሌለባት ቅጠል ስለኾነች፤
ተካይዋን በምግባር ስላላስደሰተች፤
መልካሙን ገበሬ ሊቆርጣት ተነሳ፤
ሌሎች እንዳይጠፉ በእርሷ የተነሳ፤
            
ለንስሐ የሚሆን እድሜ እንዲሰጣት፤
ጠባቂ መልአኳ ተማጸነላት፤
ምክር እና ተግሳጽ ይጨመርላት፤
ታፈራ እንደኾነ ለዓመት እንያት፤
              
ልመናውን ሰምቶ ጌታውም ፈቀደ፤
ጥቂት እድሜ ሊሰጥ ሊታገስ ወደደ፤
ዳግመኛ ሲመጣ ፍሬ ካላፈራች፤
ተቆርጣ ወደ ቶን እሳት ትጣላለች፤
----------------------------
ሉቃስ ፲፫ ÷ ፮
በዚህ ዓመት እንኳ ለማፍራት አስበን ይሆን!???
----------------------------


@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
3.3K views09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 08:09:48 ፍቁረ እግዚእ ዮሐንስ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
4.5K views05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 08:08:06 እነርሱም በታላቅ ጉስቁልና ውስጥ እየኖሩ እያለ በአንዲት ዕለት የአገረ ገዥው ልጅ ለመታጠብ ወደ ውሽባው ቤት ገባ፡፡ በውሽባ ቤቱም የሰይጣን ኃይል ስለነበረበት የመኰንኑን ልጅ አንቆ ገደለው፡፡ የአገሪቱም ሰዎች ሁሉ ለሞተው የመኰንን ልጅ ሊያለቅሱ ሲሰበሰቡ ቅዱስ ዮሐንስም አብሮ ቆሞ ሲመለከት ሮምና መጥታ "በጌታዬ ልጅ ሞት ልትደሰት መጣህን" እያለች ረገመችው፡፡ እርሱም "አይዞሽ አትዘኚ" አላትና ወደ ሞተው ልጅ ቀርቦ በመስቀል ምልክት ካማተበበት በኋላ በፊቱ እፍ አለበት፡፡ የሞተውም ልጅ ድኖ ተነሣ፡፡ የሀገሪቱም ሰዎች እጅግ ደነገጡ፡፡ ሮምናም ደንግጣ "እግዚአብሔር የሚሉት አምላክ አንተ ነህን" ብላ ጠየቀችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም "በፍጹም እኔ አምላክ አይደለሁም፣ እኔ የእርሱ አገልጋዩና ሐዋርያው ነኝ እንጂ" አላት፡፡ ሮምናም ስለበደለቻቸው በደል ሁሉ መሪር ዕንባን እያለቀሰች ይቅር እንዲሏት ለመነቻቸው፡፡ እነርሱም አረጋጉዋት፡፡ ከሕዝቡም ውስጥ ብዙዎቹ በጌታችን አመኑ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ሌሎች ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ ወንጌልን እየሰበከ ከጣዖት አገልጋዮች በቀር ሁሉንም አሳምኖ አጠመቃቸው፡፡ አገልጋዮችን ኤጲስቆጶሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ከሾመላቸው በኋላ ወደ ሌሎች አቅራቢያ አገሮች ሄደ፡፡

በመጨረሻም በከሃዲውና በጨካኙ በድምጥያኖስ ዘመን በጣዖት አምላኪዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ፡፡ በፈላ ውኃ ካሠቃዩት በኋለ በፍጥሞ ደሴት አጋዙት፡፡ በዚያም ሳለ ራእዩን ተመልክቶ ጻፈው፡፡ ድምጥያኖስም ከተገደለ በኋላ ከግዞቱ ተመልሶ ሦስቱን መልእክታቱንና ቅዱስ ወንጌሉን ጽፏል፡፡ ጌታችንም አስቀድሞ ሞትን እንደማይቀምስ ለዮሐንስ ቃል ገብቶለት ነበርና (ዮሐ 21፡22) ጥር 4 ቀን እንደ ኤልያስና ሄኖክ ሞትን እንዳያይ ወደ ብሔረ ሕያዋን ወስዶታል።

ጌታችን ለዮሐንስ ያልነገረው እርሱም ያላስተማረው ምሥጢር የለም፡፡ ወንጌሉን መጻፍ ሲጀምር "በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ…" ብሎ የጌታችን ነገር ተመራምሮ ለመድረስ ሲል በመሀል መልአኩን በዮርዳኖስ ባሕር ላይ ሲሄድ አገኘው፡፡ መልአኩም የዮርዳኖስን ባሕር በእንቁላል ቅርፊት እየጨለፈ ወደ ውጭ ሲያፈስ ተመለከተው፡፡ ዮሐንስም ተገርሞ "ምን ማድረግህ ነው" አለው፡፡ መልአኩም "የዮርዳኖስን ባሕር ቀድቼ እየደፋሁ ልጨርሰው ነው" ሲለው ዮሐንስም መልሶ "ታዲያ በእንቁላል ስባሪ ነውን?" አለው፡፡ መልአኩም "አዎን" አለው፡፡ ዮሐንስም "በከንቱ ደከምክ" አለው፡፡ ይህን ጊዜ መልአኩም መልሶ "አንተስ እንጂ ደግሞ የአምላክን መገኘት፣ አኗኗሩንም ተመራምረህ በጥበብ ለማግኘት ብለህ 'በመጀመሪያ ቃል ነበረ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ..' ብለህ ጀምረህ የለምን? አንተ ጌታን ተመራምረህ ካገኘህና ከደረስክበት እኔም የዮርዳኖስን ወንዝ በዚህ እንቁላል ቅርፊት ቀድቼ እጨርሰዋለሁ" አለው፡፡ ዮሐንስም ይህን ጊዜ ደንግጦ ዝቅ ብሎ "ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ…" ብሎ ሀሳቡን ለወጠና ሌላ ታሪክ ቀጠለ፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ጌታችንን እስከ እግረ መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ክርስቲያኖችን ሁሉ ወክሎ እመቤታችንን በአደራ የተቀበለ እርሱም ለመቤታችን በአደራ የተሰጠ ሲሆን እመቤታችንን ከወሰዳት በኋላ ለ16 ዓመት እየተንከባከበ ጠብቋታል፡፡ እናቱም በሕፃንነቱ ስለሞተች እመቤታችን ናት እየተንከባከበች ያሳደገችው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ በመልኩም ከጌታችን ጋር ይመሳል ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ሥዕል የመሳል ተሰጥኦም ነበረው፡፡ ጌታችን በተሰቀለበት ዘመን የነበረው ጢባርዮስ ቄሳር ልጁ በሽተኛ ነበር፡፡ የጌታችንን የማዳን ሥራ እየሰማ እነ ጲላጦስም ስለጌታችን የሚጽፉለትን ይሰማ ስለነበር ልጁን ከጌታችን መቃብር ላይ እንዲያኖሩለት ላከው፡፡ ልጁም ፈጥኖ ተፈወሰለት፡፡ ጢባርዮስ ቄሳርም በልጁ መዳን ምክንያት የጌታችንን ውለታ ማስቀመጥ ፈልጎ የጌታችንን ሥዕሉን የሚሥልለትን ሲያጠያይቅ ዮሐንስን አገናኙት፡፡ ዮሐንስም ጌታችንን ልክ በዕለተ ዓርብ እንደተሰቀለ አድርጎ በመሣል ለጢባርዮስ ቄሳር ሰጠው፡፡ ሲሥለውም በመጀመሪያ ጌታችንን ልክ እንደተሰቀለ አድርጎ ራቁቱን ነበር የሳለው፡፡ ዮሐንስ የሳለው የጌታችን ሥዕልም አፍ አውጥቶ "በመጀመሪያ አይሁድ በኢየሩሳሌም ራቁቴን ሰቀሉኝ፣ አሁን ደግሞ አንተ ድጋሚ በሮም ራቁቴን ትሰቅለኝን?" ብሎ ተናገረው፡፡ ዮሐንስም እጅግ ደንግጦ "እንዴት አድርጌ ልሳልህ?" ብሎ የሳለውን ሥዕል ቢጠይቀው ሥዕሉም "ከለሜዳ አልብሰህ ሳለኝ" አለው፡፡ ዮሐንስም እንዳለው ከለሜዳ አልብሶ ከሳለው በኋላ ሥዕሉን ትኩር ብሎ ተመልክቶ ቢስመው ከንፈሩ አንድ ቀን ተኩል ያህል ተጣብቆ ቆይቷል፡፡ ዛሬም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የምትጠቀምባቸውን የጌታችንን ስነ ስቅለት የሚያሳዩ ሥዕሎች መገኛቸው ይህ ወንጌላዊው ዮሐንስ የሳለው ሥዕል ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፦
በሕይወቱና በኑሮው ሁሉ ጌታችንን ለመምሰል ይጥር ነበርና ጌታችንም እጅግ ይወደው ስለነበር "ፍቁረ እግዚእ" ተባለ፣
የታላቁ ያዕቆብ ታናሽ ወንድም ስለሆነና አባቱም ዘብድዮስ ስለሚባል "ዮሐንስ ወልደ ዘብድዮስ" ተባለ፣
ለጌታችን ባለው ቅናትና ከወንድሙ ጋር ሆነው ባሳዩት የኃይል ሥራ እንዲሁም የጌታችንን አምላክነት በመግለጡ "ቦአኔርጌስ ወይም ወልደ ነጎድጓድ" ተብሏል:
ነገረ መለኮትን ከሌሎቹ በበለጠ ሁኔታ አስፍቶና አምልቶ በማስተማሩ "ነባቤ መነኮት ወይም ታዖሎጎስ" ተብሏል።
ኃላፊውንና መጻዒውን ጊዜ በራእዩ ስለገለጠ "አቡቀለምሲስ" ተባለ፣ ይህም በግሪክኛ ባለራእይ ማለት ነው፡፡
የጌታችንን መከራ መስቀሉን እያስታወሰ ፸ ዘመን ሙሉ እያለቀሰ ስለኖረና ፊቱም በሀዘን ስለተቋጠረ "ቁጹረ ገጽ" ተብሏል፡፡

የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱ አይለየን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
4.1K views05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 08:08:06
መስከረም ፬
ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ

መስከረም አራት በዚህች ዕለት ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ከእናቱ ማርያም ባውፍልያ ከአባቱ ዘብዴዎስ የተወለደበት ዕለት እንደሆነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌልን ለመስበክ ዕጣ የደረሰው እስያ ስለነበር ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን አስከትሎ ሄደ፡፡ ይኽችውም ኤፌሶን በጥንቱ በታናሽ እስያ በዛሬው የቱርክ ግዛት ውስጥ ከተማ ናት፡፡ ዛሬ ኢያዞሎክ ተብላ የጥንት ታሪኳ ጠፍቷል፡፡ አስቀድሞ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ሰብኮባታል፡፡ ደቀ መዝሙሩን ቅዱስ ጢሞቴዎስንም በከተማዋ ላይ ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾሞት ነበር፡፡ እርሱም በግፍ እስከተገደለበት ጊዜ ድረስ ቅዱስ ዮሐንስን እየረዳው በከተማዋ ብዙ አገልግሏል፡፡ በኋላ ግን በግፍ ገድለውታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ኤፌሶን ለመሄድ በመርከብ ሲሳፈር መርከቡ በማዕበል ተሰበረ፡፡ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን መዕበሉ ወደ አንዲት ደሴት አደረሰው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን በመርከቡ ስባሪ ተንጠልጥሎ በባሕሩ ማዕበል መካከል 40 ቀንና 40 ሌሊት ከኖረ በኋላ ማዕበሉ ተፍቶ አብሮኮሮስ ካለበት ደሴት አደረሰውና ተያይዘው ኤፌሶን ከተማ ገቡ፡፡ የከተማይቱም ሰዎች እጅግ ክፉዎች ስለነበሩ መጀመሪያ ላይ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ አልቻሉም ነበር፡፡ እነርሱም እጅግ ክፉዎች መሆናቸውን ስላወቀ ቅዱስ ዮሐንስ ገና ዕጣው ሲደርሰው በሀዘን አልቅሶ ነበር፡፡ አሁንም ከተማው በገቡ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ምክንያት በመፍጠር ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤቷ እሳት አንዳጅ ሆኖ አብሮኮሮስም ዕቃ አጣቢ ሆነው ተቀጠሩ፡፡ የቀጠረቻቸው ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ጀመር፡፡ ባሮቿ እንደሆኑ ተስማምተው ስለጻፉላት ትደበድባቸውም ነበር፡፡
3.0K viewsedited  05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-12 23:49:37 * የቤተ ክርስቲያንን ክብር ለመጠበቅ ይቻል ዘንድ በአዲሱ ዘመን ነቅፈው ለነቃፊ ከሚያሰጡን ተግባራት ራሳችንን ማራቅ፤ ሃይማኖቱና ፖለቲካ ተቀላቅሎበት ግራ የተጋባ ካለም ለሃይማኖቱ ብቻ ግንባር ቀደም ጠበቃ በመሆን ሃይማኖቱንና ቤተክርስቲያንን ጠብቆ ማስጠበቅ የሚችልበትን ሥራ መስራት ይኖርበታል።

*አዲሱ ዓመት ከፖለቲካ ጋር ከተቀላቀሉ ጉዳዮች ርቀን፤ ሴራ፣አድማ፣ተንኮልና ምቀኝነትን የመሳሰሉ ተግባራት ሁሉ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ተጠርጎ ወጥቶ በምትኩ ሰላምና ፍቅር ነግሶ በአንድነት ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን እድገት የምንረባረብበት ጊዜ መሆን ይገባዋል።

*የአብነት ትምህርት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወሳኝ ምዕራፍ በመሆኑ የአብነት መምህራን በሥራ እጦት የሚንገላቱበት ጊዜ አብቅቶ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል የሚደረጉ ቅጥሮች ለአብነት መምህራን ቅድሚያ የሚሰጡ መሆን ይገባቸዋል።

*ሃይማኖትን ከፖለቲካ ፖለቲካን ከሃይማኖት
መቀላቀል አይቻልም።

*እኛ የቤተክርስቲያን ወታደሮች ነን፤

*ከዛሬ ጀምሮ በዘር በጎሣ በነገድ በክፋት በሴራ
ቤተክርስቲያንዋን ዝቅ ማድረግ አይቻልም።ቤተክርስቲያን ትናትም ዛሬም ታላቅ ናት ነገም ታላቅ ትሆናለች ፤

EOTCDPR

@Ethiopian_Orthodox
3.6K views20:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-12 23:49:25
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቅዱስነታቸው የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር ላይ ካስተላለፏቸው መልዕክቶች የተወሰደ፦
*
መስከረም
፪ቀን፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
"""""""""""""""""""""""""""""
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
***

*ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መሪ የሚሆኗት እውነትና ብርሃን ናቸው።
በዚህ ወቅት ያ ብርሃን እየደደበዘዘና የቤተ ክርስቲያን ክብር እየቀነሰ መጥቷል።

*በአዲሱ ዓመት  ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን"'መጥዎተ ርእስ "" ራስን መሥጠት"ያስፈልጋል።
3.1K views20:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-12 07:24:06
ዘከመ:መተሮ:ለዮሐንስ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
3.4K viewsedited  04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ