Get Mystery Box with random crypto!

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_orthodox — የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_orthodox — የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopian_orthodox
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.47K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡
ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-07 00:30:05
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
120 viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 21:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-07 00:30:05 ሰኔ ፴
ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ


ሰኔ ሠላሳ በዚህች ዕለት ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ተወለደ። ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው። በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጐረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው።

በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን አይሆንም ዮሐንስ ይባል አለች። ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም አሏት። አባቱንም ጠቅሰው ማን ሊባል ትወዳለህ አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም 'የልዑል ነቢይ' እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ።

ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው።

ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ።

"የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ" እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እነሆ ብሎ ኢሳይያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለሱ እንዲህ አለ። "በፊትህ ጐዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልእክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ።'

ራሱ መድኃኒታችንም ስለርሱ ሲናገር "ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም" ብሏል። ይህ የእግዚአብሔርን ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና።

ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ፡፡

ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
122 viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 21:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 08:25:55
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2.7K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 08:25:55 ዘመነ ክረምት በኢትዮጵያ

በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ሥርዓተ አስተምህሮ በቅዱስ ያሬድ የዜማ መጻሕፍት እና በመጽሐፈ ግጻዌ መሠረት፣እንዲሁም በሀገራችን ኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ስሌት መሠረት ወቅቶች በአራት ይከፈላሉ፡፡ እነዚህም ወቅቶች ዘመነ መጸው (መከር)፣ ዘመነ ሐጋይ (በጋ)፣ ዘመነ ጸደይ (በልግ) እና ዘመነ ክረምት ይባላሉ፡፡

ከአራቱ ወቅቶች መካከልም ከሰኔ ፳፮ እስከ መስከረም ፳፭ ቀን ድረስ ያለው ጊዜ (አሁን የምንገኝበት ወቅት) ዘመነ ክረምት ተብሎ ይጠራል፤ ቃሉን ለማብራራት ያኽል፣ "ክረምት" የሚለው ቃል ‹ከረመ – ከረመ› ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን፣ ትርጕሙም የዝናም፣ የአዝርዕት፣ የአረም ጊዜ፣ እንደዚሁም ዕፀዋት፣ አዝርዕትና አትክልት በቅለው፣ ለምልመው የሚያድጉበት፣ ምድር በአረንጓዴ ዕፀዋትና በልምላሜ የምታሸበርቅበት ወቅት ማለት እንደሆነ የአማርኛ መዝገበ ቃላትና ልዩ ልዩ ድርሳናት ያስረዳሉ።

በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት አራቱ ወቅቶች የጌታችንና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ወንጌል በጻፉት በአራቱ ወንጌላውያን እንደሚመሰሉ ማለትም: ዘመነ ክረምት - በወንጌላዊው ማርቆስ፣ ዘመነ ፀደይ - በወንጌላዊው ማቴዎስ፣ ዘመነ ሀጋይ - በወንጌላዊው ዮሐንስ እና ዘመነ መፀው - በወንጌላዊው ሉቃስ እንደሆነ ሊቃውንት ያስተምራሉ።

ከአራቱ ወቅቶች መካከል ከሰኔ ፳፮ እስከ መስከረም ፳፭ ቀን ድረስ ያለው ጊዜ (አሁን የምንገኝበት ወቅት) በወንጌላዊው ማርቆስ የተመሰለው ዘመነ ክረምት ተብሎ ይጠራል፡፡

በዓተ ክረምት (የክረምት መግብያ)

ከሰኔ ፳፮ እስከ ሐምሌ ፲፰ ቀን ድረስ ያለው የመጀመሪያው የክረምት ክፍለ ጊዜ "በዓተ ክረምት" ወይም ‹ዘርዕ፣ ደመና› ይባላል፡፡ ‹በዓተ ክረምት› ማለት <የክረምት መግቢያ፣ መጀመሪያ› ማለት ነው፡፡ በዚህ ወቅት በቤተክርስቲያናችን ስለክረምት መግባት፣ ስለዘርዕ፣ ስለደመና እና ስለዝናም የሚያዘክሩ መዝሙራትና ምንባባት ይዘመራሉ፣ ይነበባሉ፡፡ ይህ ወቅት ደመና ሰማዩን የሚሸፍንበት፣ የዝናም መጠን የሚያይልበትና መሬት በዝናም ረክታ ዘር የምታበቅልበት ጊዜ ነውና፡፡

በዘመነ ክረምት መጀመርያ (መግቢያ) ሳምንት በቤተክርስቲያናችን የሚቀርበው የቅዱስ ያሬድ መዝሙር የሚከተለው ነው፤ ‹‹ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ሶበ ይዘንም ዝናም ይጸግቡ ርኁባን ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ሶበ ይዘንም ዝናም ይትፌሥሑ ነዳያን ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ወሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ደምፀ እገሪሁ ለዝናም›› የመዝሙሩ ቀጥተኛ ትርጕም፡-‹‹የዝናም ኮቴው ተሰማ፣ ዝናም በሚዘንም ጊዜ የተራቡ ይጠግባሉ፡፡ የዝናም ኮቴው ተሰማ፡፡ ዝናም በሚዘንም ጊዜ ድሆች ይደሰታሉ፡፡ የዝናም ኮቴው ተሰማ፣ አምላካችን ለሰው ልጅ ዕረፍት ሰንበትን ፈጠረ፤ የዝናም ኮቴው ተሰማ፡፡ የዝናም ኮቴው ተሰማ፡፡>>

ይህ መዝሙር ከሰኔ ፳፮ ጀምሮ ያለው ወቅት ክረምቱ የሚገባበት እና ዝናም በብዛት የሚጥልበት ጊዜ መኾኑን የሚያበሥር ሲኾን፣ በተጨማሪም ዝናም በሚዘንብበት ጊዜ የሚበቅለውን እኽልና የምንጮችን መብዛት ተስፋ በማድረግ የተራቡ እንደሚጠግቡ፤ የተጠሙም እንደሚረኩ የሚያትት ምሥጢር ይዟል፡፡ እንደዚሁም ጊዜ ለበጋ፣ጊዜ ለክረምት የሚሰጥ አምላክ ለሰው ልጅ ማረፊያ ትኾን ዘንድ ዕለተ ሰንበትን መፍጠሩንም ያስረዳል፡፡

አያይዞም ቅዱስ ዳዊት "ዘይገለብቦ ለሰማይ በደመና ወያስተዴሉ ክረምተ ለምድር ዘያበቍል ሣዕረ ውስተ አድባር፡፡››መዝ ፻፵፮፥፰ ትርጕም፡- ‹‹ሰማዩን በደመና የሚሸፍን፣ ለምድርም ዝናምን የሚያዘጋጅ፣ ሣርን በተራሮች ላይ የሚያበቅል እርሱ ነው፡፡>> እግዚአብሔር ሰማዩን በደመና የሚሸፍን፤ ዝናምንም (ክረምትን) ለምድር (ለሰው ልጅ) የሚያዘጋጅ፤ እንደዚሁም በተራሮች ላይ ሣርን (ዕፀዋትን) የሚያበቅል አምላክ መኾኑን ያስገነዝባል። ዘመነ ክረምት በየትኛውም ክፍለ አኅጉር ወቅቶችን እየቀያየረ ምድርን ሲያድስ የሰው ልጆችንም ሕልውና አብሮ በማደስ ሰውና ክረምት ያለውን ቁርኝት ዘላለማዊ አድርጎታል።

ስለሆነም ክረምት እና በጋውን በማፈራረቅ ምድርን በልምላሜ እና አበባ የሚያሸበርቀውን ፤ በዘመናት መካከል በፀጋና በረከት የሚያኖረውን የዘመን ባለቤት አምላካችን እግዚአብሔርን ከልባችን እያመሰገንን ለዘላለማዊ ክብሩ በመገዛት እንኑር። በክረምት የሚሠሩትን ሥራዎች በሙሉ በመከወን ለፍሬያማው ወቅት እግዚአብሔር ያደርሰን ዘንድ አብዝተን እንጸልይ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

በመ/ር ሽፈራው እንደሻው

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
2.8K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 09:32:26
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
5.1K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 09:32:26 ሠኔ ፳ እና ፳፩ በእመቤታችን ስም የተሠራች የመጀመሪያዋ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንና ቅዳሴ ቤት የእመቤታችን ፪ኤቱ ክብረ በዓላት ታሪክ

በሠኔ ፳ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በፊልጵስዩስ የተሠራችው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ትታሰባለች፤ ይኸውም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስረዳን ጳውሎስና በርናባስ ወደ ፊልጵስዩስ ከተማ ገብተው ባስተማሩ ጊዜ ሕዝቡ “መካነ ጸሎት ለዩልን” ብለዋቸዋል፤ ይኽነንም ለጴጥሮስ በነገሩት ጊዜ ጌታችን የሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን አሠራር እንዲገልጽላቸው ሱባዔ ገቡ፤ ሱባዔውም ሲፈጸም ጌታ ሐዋርያትን የሞቱትን አስነሥቶ ያሉትን ጠርቶ በሕይወተ ሥጋ በፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፨

“በናቴ ስም አብያተ ክርስቲያናት ሊታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ላሳያችኊ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናትን ላስተምራችኊ ሰብስቤያችኋለኊ” ብሏቸው፤ ወደ ምሥራቅ አገር ይዟቸው ወጣ፤ በዚያ በምሥራቅ ሀገር ሦስት ደንጊያዎች ነበሩ ተራርቀው የነበሩትን አቀራረባቸው፤ ጥቃቅን የነበሩትን ታላላቅ አደረጋቸው፤ ቁመቱን ወርዱን ለክቶ ሰጣቸው፤ ቁመቱ 24 ወርዱ 12 ክንድ ነው፡፡

፳፬ቱ የ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ አምሳል ነው፤ ፲፪ቱ የ፲፪ቱ ሐዋርያት ምሳሌ ነው፤ ከዚኽ በኋላ ሥራ ጀመሩ፤ ሲሠሩትም ሰም እሳት ሲያሳዩት እንዲለመልም በእጃቸው ላይ እየተሳበ ሠርተው ፈጽመውታል፤ ይኽ የኾነ እመቤታችን ባረገች በአራተኛው ዓመት በሠኔ ፳ ቀን ነው፨

በሠኔ ፳፩ኛው ቀን ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ መጣ፤ እመቤታችንን ታቦት፤ ሐዋያትን ልኡካን አድርጎ፤ ጌታ ዐቢይ ካህን ኾኖ ቀድሶ አቊርቧቸዋል፤ ከዚያም “እምይእዜሰ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ” (ከእንግዲኽ ወዲኽ እናንተ እንዲኽ ሥሩ) ብሎ አዝዟቸው ዐርጓል፤ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የተጀመረ በቅድስት ድንግል ስም ነው፡፡

ሦስቱ ደንጊያዎች የሥላሴ አምሳል ናቸው፤ ከታች አቀማመጣቸው ፫ ከላይ ሕንፃቸው ፩ ነው ይኽም የአንድነታቸው የሦስትነተኛው አምሳል ነው፤

አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ፡-

“በሠላስ አእባን ገጸ ሥላሴሁ ለአምሮ
ሐኒጸ ቤትኪ ድንግል ድኅረ ፈጸመ ሣርሮ
አመ ወረደ ለበዓል ምስሌኪ በአማኅብሮ
እንዘ ይብላ ቃለ ለዘምሮ
ልዑል ቀደሰ ማኅደሮ
ደናግል ለጽጌኪ ዘበጣ ከበሮ”

(ድንግል በአካል ሦስት መኾኑን ለመግለጽ በሦስት ድንጋዮች ቤትሽን መሥራት ከፈጸመ በኋላ፤ ከአንቺ ጋር ለበዓል በተገለጸ ጊዜ ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ እያሉ ልጅሽን ለማመስገን ደናግል በከበሮ ምስጋናን አቀረቡ) በማለት ገልጸዋል፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሠራሯ በሰማያት አምሳል እንደኾነ ሊቃውንት ይተነትናሉ፤ ይኸውም የመጀመሪያዋ ሰማይ “ጽርሐ አርያም” ስትባል ከእሳት ብርሃኗን ነሥቶ ከብርሃን ብርሃንን ጠምቆ አጥርቶ፤ ኹለንተናዋን በብርሃን ቀለም ሸልሟታል “አልቦ ሰማይ ዘይጼልል ላዕሌሃ እስመ መልዕልታዊት ወጽንፋዊት ይእቲ ወኲለንታሃ ብርሃን ፍጹም ዘኢይትነገር በልሳነ ኲሉ ፍጡር ወኲሎሙ ብርሃናት አምሳለ ቀለምጺጸ እሳት በኀቤሃ” ይላል ፤ ብርሃኗን ማንም ከቶ ሊገልጸው አይችልም፤ ከርሷ ብርሃን አንጻር ሲታዩ ሌሎቹ ብርሃናት የእሳት ፍንጣሪ ያኽላሉ፤ ከሰማይ ኹሉ በላይ ስትኾን ከርሷ በላይ ምንም ሰማይ የለም፤ ከዚኽ የተነሣ “ሰማየ ሰማያት” ትባላለች (ዘዳ ፲፥፲፬፤ ፩ነገ ፰፥፳፯)፡፡
ምሳሌነቷን ሊቃውንት በመጽሐፈ ቅዳሴ መቅድም ላይ የሰማይ ሥርዓት በምድር ላይ ስለመሠራቱ ሲተነትኑ በጽርሐ አርያም ውስጥ መንበረ ብርሃን፣ ታቦተ ብርሃን፣ መንጦላዕተ ብርሃን፣ አራቱ ጸወርተ መንበር፣ ኻያ አራቱ ዐጠንተ መንበር ይኖራሉ፤ ጽርሐ አርያም የመቅደስ፤ መንበረ ብርሃን የመንበር፤ ታቦተ ብርሃን የታቦት፤ መንጦላዕተ ብርሃን የመንጦላዕት፤ አራቱ ጸወርተ መንበር የአራቱ ሊቃነ ጳጳሳት፤ ፳፬ቱ ዐጠንተ መንበር የጳጳሳት የኤጲስ ቆጶሳት አምሳል ናቸው፡፡
ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ሰዓታቱ ላይም “ወኊልቈሙ ለእሙንቱ መላእክት ወሊቃነ መላእክት... ወቡርክት ዛቲ ቤተ ክርስቲያን እንተ አሕዛብ ትመስል ኀይለ ሰማያት” (የእነዚኽ መላእክት የመላእክት አለቆች ቊጥርም መናብርትና ሥልጣናት፣ አጋዕዝትና ኀይላት፣ ሊቃናት፣ ኪሩቤልና ሱራፌል ነው፤ እየጮኹም እንዲኽ ይላሉ የእስራኤል አምላክ ይመስገን የሕዝቡ የአሕዛቡ የምትኾን የተባረከች ቤተ ክርስቲያን የሰማያት ኀይልን ትመስላለች) ይላል፡፡
ሊቁ ሰራዊተ መላእክትን በሚያመሰግንበት በዚኽ ክፍል ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አሠራሯና እና አከፋፈሏ በመላእክት ከተማ እና በአሰፋፈራቸው ልክ የተመሰለች መኾኗን አስረግጦ አስተምሯል፡- ይኸውም ሦስቱ የቤተ ክርስቲያን ክፍሎች (መቅደስ፣ ቅድስት፣ ቅኔ ማሕሌት) የሦስቱ ዓለመ መላእክት ምሳሌ ሲኾን ይኸውም መቅደስ የኢዮር፤ ቅድስት የራማ፤ ቅኔ ማሕሌት የኤረር ምሳሌ ናቸው፡፡
ኢዮር በተባለችው ሰማይ ኪሩቤል፣ ሱራፌል፣ ኀይላት ይኖራሉ፡፡ ራማ በተባለችው ሰማይ አርባብ፣ መናብርት፣ ሥልጣናት ይኖራሉ፡፡ ኤረር በተባለችው ሰማይ ሊቃናት፣ መኳንንት፣ መላእክት ይኖራሉ፡፡ እነዚኽ 9ኙ ነገድ የ፱ቱ መዓርጋተ ቤተ ክርስቲያን አምሳል ናቸው፡፡
ይኸውም በኢዮር ከሚኖሩት መላእክት ውስጥ ኪሩቤል የሊቃነ ጳጳሳት፤ ሱራፌል የጳጳሳት፤ ኀይላት የኤጲስ ቆጶሳት አምሳል፡፡
በራማ ሰማይ ከሚኖሩት ነገደ መላእክት ውስጥ አርባብ የቆሞሳት፤ መናብርት የቀሳውስት፤ ሥልጣናት የዲያቆናት አምሳል፡፡
በኤረር ሰማይ ከሚኖሩት ነገደ መላእክት ውስጥ ሊቃናት የንፍቀ ዲያቆናት፤ መኳንንት የአናጒንስጢሳውያን፤ መላእክት የመዘምራን አምሳል ናቸው፡፡

ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ ስለ ክብረ ቤተ ክርስቲያን፦
“እንተ ተሐንጸት በስሙ፤ ወተቀደሰት በደሙ ወተዐትበት በዕፀ መስቀሉ ጊሡ ኀቤሃ እስመ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕሌሃ” (በስሙ ታነጸች፤ በደሙም ከበረች፤ በዕፀ መስቀሉም ተባረከች፤ ወደ ርሷ (ቤተ ክርስቲያን) ኺዱ የእግዚአብሔር ኀይል በርሷ ላይ ነውና) ይላል፡፡

ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ተአምኆ ቅዱሳን በሚባለው ታላቅ መጽሐፉ ላይ፡-
“ሰላም ለቤተ ክርስቲያን ቅድስት ማኅደረ ስብሐት ምዕዋደ መላእክት እመ ኲሉ ሕዝብ” (የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ (ቦታ) የምስጋና ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ይገባል) ብሏታል፡፡

ይኸው ሊቅ አባ ጊዮርጊስ በተመሳሳይ መልኩ እናትነቷን በሰባቱ ጊዜያት የሕማማት ሰላምታው ላይ፡-
“ሰላም ለኪ ቤተ ክርስቲያን እምየ ዘትጼንዊ መጽርየ ብኪ ጸናዕኩ እምከርሠ እምየ
ቤተ ክርስቲያን አክሊለ ርእስየ ሰላም ለኪ”
(እንደ ቀጋ የምትሸትቺ ቤተ ክርስቲያን እናቴ ሰላምታ ለአንቺ ይገባል፤ ከእናቴ ማሕፀን ዠምሮ በአንቺ ጸናኊ፤ የራሴ አክሊል የምትኾኚ ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ለአንቺ ይገባሻል)

“በሐኪ በሐኪ ቤተ ክርስቲያን እምነ
ግበሪ ሰላመ ማእከሌነ እምኀይለ ጸላኢ ወፀር ዕቀቢ ኪያነ ትንብልናኪ የሀሉ ምስሌነ፤ ሰላም ለኪ”
(ሰላምታ የተገባሽ እናታችን ቤተ ክርስቲያን ሰላም ሰላም እንልሻለን፤ በመኻከላችን ሰላምን አድርጊ፤ ከፍጹም ጠላት እኛን ጠብቂ፤ ልመናሽም ከእኛ ጋራ ይኹን) በማለት እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አወድሷል፡፡
በተጨማሪም ሠኔ ፳፩ ቀን ቅድስት ድንግል ማርያም በጎልጎታ ቃል ኪዳን መቀበሏም ይታሰባል።
የቅድስት ቤተ ክርስቲያን በረከት ይደርብን፡፡
በመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
@Ethiopian_Orthodox
4.7K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-19 08:57:39 " ቅዱስ ላሊበላ "

በዘማሪ ዲያቆን ዮሐንስ ምስጌ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
6.6K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-19 08:57:39
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
5.8K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-19 08:57:39 የምትፈልግ አይደለህም፤ ለጠፈራቸው መማገሪያ ገመድ የምትሻ አይደለህም፣ እንጨትንም ለማገር፣ ለምሰሶዋቸውም ገበታ፣ ለዙሪያቸውም ለማያያዣ ጭቃን የምትፈልግ አይደለህም፡፡ የቤተመቅደሶችን ፈቃድ ሁሉ ከአንድ ቋጥኝ ድንጋይ ትፈጽማለህና፡፡ የማሳይህ እኚህ የቤተ መቅደሶች አኗኗር ከምድር ልብ ውስጥ እስከዛሬ አለ፡፡ ከአሁን ጀምሮ በእጅህ እስኪገለጡም ድረስ በምድር ልብ ይኖራሉ፡፡ በሰው ልጅ ጥበብ ያይደለ በእኔ ሥልጣን ከምድር ልብ ውስጥ ታወጣቸው ዘንድ መረጥሁህ፡፡ ሕዝቦቼ ተወልጄ አድጌ ሞቼ ተቀብሬ ከሞትም የተነሳሁባትን ሀገር ለማየት ኢየሩሳሌም በመሄድ ግማሹም በበረሃ ይቀር ነበር አሁን ግን አንተ ኢየሩሳሌምን በሀገርህ ትሠራለህ፡፡ በማንም እጅ ዳግመኛ ሊሠሩ የማይችሉ ቤተ መቅደሶቼን እንዳሳየሁህ ትሠራለህ፡፡ አንተም እንዳሳየሁህ በልብህ ውስጥ አኑራቸው፡፡ ስትሠራቸውም እየልካቸው ይሁን፤ ከእርዝመታቸውም በላይ ቢሆን፣ ከወርዳቸውም በላይ ቢሆን፣ በመወጣጫቸውም ላይ ቢሆን አንዳች እንዳትጨምር፡፡ ያሳየሁህ እሊህ ዐሥሩ መቅደሶች ከአንዲት ቋጥኝ ድንጋይ ሲወጡ አይተሃልና….› እያለ ጌታችን ሲነግረው ጻዲቁ ንጉሥ “ይህ እንዴት ይሆናል?” በማለት ይጠይቃል፡፡ ጌታም እውነት እልሃለሁ እነዚህ ያሳየሁህ መቅደሶች በሰው ኃይል የሚሠሩ ሆነው አይደለም፤ ጀማሪያቸው ሠሪያቸውና ፈጻሚያቸው እኔ ነኝ ነገር ግን ኃይሌ በአንተ እጅ እንዲገለጽ ለምክንያት ተልከሃል፤ አንተ አነጽካቸው እየተባለ እስከ ዕለተ ምፅዓት ድረስ ስምህ ይጠራባቸዋል…›› እያለ ይቀጥላል የቅዱስ ላሊበላ ገድል፡፡ ቤተ መቅደሶቹንም ለመሥራት ቦታውን ያውቅ ዘንድ ሱባኤ ገብቶ ሳለ ዛሬ ቤተ ማርያም ካለችበት ቦታ ላይ ቅዱሳን መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ታይተውት በቦታው ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ መቅደሱን መሥራት ጀመረ፡፡ ዓሥሩን ቤተ መቅደሶች ሲሠራ እርሱ አንድ ክንድ ሠርቶ እንደሆነ ሌሊቱን አድሮ በቀጣዩ ቀን አሥር ክንድ ሆኖ ያገኘው ነበር፣ ቀንም በማይታወቁ ሰዎች አምሳል እየተገለጡ መላእክት ይራዱት ነበር፡፡

5. አንዳንድ ነገሮች ስለ ቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፡- ቅዱስ ላሊበላ ዓሥሩም ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በጣም በሚያስገርም ሁኔታ በውስጥና በውጭ ያሉት ብዙ ቅርጾች ነገረ ድኅነትን በምሳሌ እንዲወክሉ አድርጎ ነው ያነጻቸው፡፡ የክርስቶስን መከራና በእርሱም የተገኘውን ፍጹም ዘላለማዊ ድኅነት በእያንዳንዱ ቤተ መቅደስ ውስጥ እንዴት አድርጎ በምሳሌ እንዳስቀመጠው እጅግ አስገራሚ ነው፡፡
በላስታ ቅዱስ ላሊበላና አካባቢው የሚገኙ ሌሎች አስደናቂ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፡- ከአሥሩ የቅዱስ ላሊበላ አስደናቂ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በተጨማሪ የቅዱስ ነአኵቶለአብና የቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም አሸተን ማርያም በዋናነት ሕዝበ ክርስቲያኑ የሚጐበኛቸው ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ናቸው፡፡ በላሊበላና አካባቢው ግን እጅግ ጥንታዊና አስደናቂ የሆኑ በጣም በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ሣርዝና ሚካኤል፣ ብልባላ ቂርቆስ፣ ብልባላ ጊዮርጊስ፣ አርባዕቱ እንስሳ፣ ትርኩዛ ኪዳነምሕረት፣ ገነተ ማርያም፣ ቀንቀኒት ሚካኤል እነዚህ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ሲሆኑ እንዲሁም ዋልድቢት ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም፣ አቡነ ዮሴፍ ገዳም፣ ገብረ ክርስቶስ ዋሻ ቤተክርስቲያን፣ ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን፣ ቀደሊት ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ እመኪና መድኃኔዓለምና እመኪና ልደታ፣ ማውሬ እስጢፋኖስ፣ የቅዱስ ገብረ ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ማይ ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ተከዜ ኪዳነምሕረትና መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዳንዶቹ ከ485-536 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ በዐፄ ካሌብ ዘመነ መንግሥት የታነጹ ናቸው፡፡ ሌሎቹንና በሰሜን ላስታ ያሉትን ደግሞ እነ ላሊበላና ይምርሃነ ክርስቶስ አንጸዋቸዋል፡፡

ቅዱስ ላሊበላ እኛ ከምናውቃቸው ከድንቅ ሥነ ሕንፃዎቹ ሥራ በተጨማሪ ከሺህ ዓመታት በፊት በሥዕል፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በሃይማኖት፣ በኢኮኖሚ፣ በውጭ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙትና በመሳሰሉት ሁሉ እጅግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ከሺህ ዓመታት በፊት አዳራሾችን፣ ፎቆችን፣ የውስጥ ለውስጥ መተላለፊያዎችን፣ የእንግዳ መቀበያዎችን፣ የሕፃናት ማሳደጊያዎችን፣ የሕሙማን መፈወሻዎችን፣ የሕንፃ መሳሪያዎችን፣ የትምህርት ማዕከሎችን፣ የመደጎሻ ቦታዎችን ያቋቋመ መሆኑን የብራና ገድሉ እንደሚናገር የደብሩ አባቶች ይገልጣሉ፡፡ ወደፊት ተርጎመው እንሚያቀርቡልን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ከዚህ በተጨማሪ የግእዝ ቋንቋን በጽሑፍ አበልፅጎ ያቆየ ባለውለታ ነው፡፡ ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ውጭ ሌሎችንም በርካታ ቤተ መቅደሶች ሠርቷል፤ ከሀገራቸንም አልፎ በሱማሌ ሞቃዲሾ ላይ መቅደሰ ማርያም የተባለች ቤተክርስቲያን ሠርቷል፡፡ ክርስትናን ከግብፅ ምድር ጨርሰው ለማጥፋት ተንባላት በተነሡ ጊዜ ዓባይን ሊያግድባቸው ሲነሣ በብዙ ምልጃና ልመና ስለማራቸው በሀገሪቱ ውስጥ ክርስትና እስካሁን እንዲቆይ የራሱን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ በአጠቃላይ ቅዱስ ላሊበላ ነቢይም ሆኖ፣ ሐዋርያም፣ ጻዲቅም፣ ሰማዕትም ሆኖ ጥበብ መንፈሳዊንና ጥበብ ሥጋዊን ከእግዚአብሔር ተሰጥቶት ንግሥናንና ክህነትን፣ ቅድስናንና ንጽሕናን በሚገባ አስተባብሮ በማያዝ እግዚአብሔርንም ሰውንም በቅንነት ሲያገለግል ኖሮ ሰኔ 12 ቀን 1197 ዓ.ም ከፈጣሪው ታላቅ ቃልኪዳን ተቀብሎ በዝማሬ መላእክት፣ በመዝሙረ ዳዊት ቅድስት ነፍሱ ከሥጋው ተለይታ ሰማያዊ ክብርን ወርሷል፡፡ ክቡር ሥጋውም ራሱ ባነጸው ቤተ ሚካኤል መቅደስ ሥር በክብር ዐርፏል፡፡

(ምንጭ፡- ገድለ ቅዱስ ላሊበላ፡- የቅዱስ ላሊበላ ደብር በ2003 ዓ.ም ያሳተመው፣ ስንክሳር ዘወርሃ ሰኔ)
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
4.7K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-19 08:57:39 ረ ሊያጠፋው ምክንያት ይፈልግበት ነበር፡፡ ለዐፄ ገብረ ማርያም በእናትም በአባትም እኅት የምትሆነው ለላሊበላ ግን በአባት ብቻ እኅት የሆነችው ዮዲት ላሊበላን ለመግደል በማሰብ ቀን ከሌሊት አጋጣሚን ትጠብቅ ነበር፡፡ ቅዱስ ላሊበላም ጌታችን መራራ ሐሞት መጠጣቱንም እያሰበ ሁልጊዜ ዓርብ ዓርብ ከጾምና ጸሎት በኋላ መራራ ኮሶ ይጠጣ ነበርና ይህን አጋጣሚ በመጠቀም አንድ ቀን እንደጠማው አውቃ በጠላ ውስጥ መርዝ ጨምራ ሰጠችው፤ ቅዱስ ላሊበላም መርዝ የተቀላቀለበትን ጠላ ጠጣው፡፡ እርሱ ከመጠጣቱ በፊት ያገለግለው የነበረው ዲያቆን ቀምሶት ወዲያው ሲሞት አየ፡፡ ዲያቆኑ ያስመለሰውን የጠጣው ውሻም ወዲያው ሞተ፡፡ ቅዱስ ላሊበላም ይህን ሲመለከት በሐዘንና በፍጹም ፍቅር ሆኖ ‹‹አገልጋዬ ለእኔ የተዘጋጀውን መርዝ ጠጥቶ እንደሞተ ሁሉ እኔም መሞት ይገባኛል›› በማለት ያን መርዝ ስለወዳጁ ፍቅር ሲል ጠጥቶ ለመሞት ቆረጠና ጠጣው፡፡ ጌታችን በወንጌሉ ስለራሱ ‹‹ስለ በጐቹ ቤዛ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ የሚሠጥ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም›› (ዮሐ 15፡13) ብሎ የተናገረውን ቃል ቅዱስ ላሊበላም ስለ ወዳጁ ሞት ሲል ራሱን ለሞት አሳልፎ ሰጠ፡፡ ነገር ግን መርዙ እንኳን ሊጎዳው ይቅርና በሆዱ ውስጥ ከልጅነቱ ጀምሮ የነበረበትን የሆድ ሕመም ነቅሎ አወጣለት፡፡ በዚህም ጌታችን በወንጌሉ ‹‹የሚገድል መርዝም ብትጠጡ ምንም አትሆኑም›› (ማር 16፡18) ያለው ቃል ተፈጽሞለታል፡፡ መርዙ ለበጐ ሆኖለት ከሆዱም ውስጥ የነበረው ጥፍሮች ያሉት አውሬ መሰል ፍጡር ወጣለትና የሆድ ሕማሙ ፈጽሞ ተወው፡፡ ያን ጊዜም ቅዱስ ላሊበላ በወቅቱ ለሦስት ቀንም ያህል እንደሞተ ሆኖ የቆየ ቢመስልም ቅዱስ ገብርኤል ግን በመንፈስ ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶ ሰባቱ ሰማያትን ያሳየው ሲሆን በጌታችን ፊትም አቅርቦት አስባርኮታል፡፡ ጌታችንም ቅብዓ መንግሥት ቀብቶት ትልቅ ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡
ጻዲቁ ንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ ቅድስናን ከንግሥና፣ ክህነትን ከንጽሕና፣ ጥበብ መንፈሳዊን ከጥበብ ሥጋዊ ጋር አንድ አድርጐ አስተባብሮ የያዘ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ፣ ቅዱሳን መላእክትም ይራዱት እንደነበርና ጌታችንም ትልቅ ቃልኪዳን እንደሰጠው ከቅዱስ ገድሉ ላይ እናገኛለን፡፡ ከጌታችን ዘንድ የተሰጠውንም ቃልኪዳን በሦስት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ በዚህም መሠረት፡-
1ኛ. መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ላሊበላን እየመራው ከላስታ ወደ አክሱም ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም አድርሶ በዚያ የሚገኙትን ቅዱሳት መካናት ሁሉንም ካሳየው በኋላ ‹‹ወደ ሀገርህ ሮሐ ተመልሰህ በእነዚህ ምሳሌ ታንጻለህ›› ብሎታል፡፡ ወደ ሀገሩም ተመልሶ በአሽተን ማርያም ተራራ ላይ ሱባኤ ይዞ በጾም ጸሎት ተወስኖ ሳለ እግዚአብሔር የሚሠራቸውን መቅደሶች በግልጽ በራእይ አሳይቶታል፡፡

2ኛ. ከላይ እንዳየነው ለሞት ተብሎ የተሰጠው መርዝ ለሕይወት ሆኖለት በመሬት ላይ ወድቆ ሳለ በነፍስ መልአክ ነጥቆት እስከ ሰባተኛው ሰማይ ጽርሐ አርያም ድረስ ደርሶ በጌታ ፊት ቀርቦ ከጌታ ዘንድ ‹‹እኔ አከበርኩህ ቃሌ አይታበይም፣ ከአንድ ቋጥኝ እነዚያን በራእይ ያሳየሁህን አብያተ ክርስቲያናት ታንጻለህ›› የሚል ቃልኪዳን ተቀብሏል፡፡

3ኛ. ከኢየሩሳሌምም ተመልሶ የንግሥናውን ዙፋን ከቅዱስ ገብረ ማርያም ከተረከበ በኋላ በተሰጠው መንፈሳዊ ሀብትና ባየው ራእይ መሠረት አብያተ ክርስቲያናቱን አንጾ ከጨረሰ በኋላ በቀኝና በግራው ዓሥር ዓሥር ኪሎ የሚመዝን የዓለት ድንጋይ ተሸክሞ ለ7 ዓመት ሲጾም ሲጸልይ ጌታችን ተገልጦለት ‹‹…ያነጽካቸውን ቤተ መቅደሶች የተሳለመውን ኢየሩሳሌምን እንደተሳለመ አድርግለታለሁ›› የሚለውን የመጨረሻውን ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡ (ይህን ቃልኪዳኑን መጨረሻ ላይ በዝርዝር እናየዋለን) እነዚህን ሦስት ዋና ዋና ቃልኪዳኖቹን በቅድሚያ ማንሳት የፈለኩበት ምክንያት ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት ስለ ቅዱስ ላሊበላ ድንቅ ሥራዎች ከማሰባችንም ሆነ ከመናገችን በፊት በቅድሚያ ስለ ራሱ ስለ ቅዱስ ላሊበላ የቅድስና ሕይወቱና ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን ግንኙነት ማወቁ የግድ አስፈላጊ መሆኑን ለመጠቆም ነው፡፡ አሁን አሁን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሆን ተብሎ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ውቅር አብያተ ክርስቲያናቶቹ በቱሪስት መስህብነታቸው ብቻ እየታዩ የቅድስና ታሪካችንም እየተጨፈለቀና መንፈሳዊ እሴቶቻችንንም ለማጥፋትም ጥረት እየተደረገ ስለሆነ እውነተኛውን ነገር በደንብ ማወቅና በእጅጉ መጠንቀቅ ስላለብን ነው ይህን የማነሳው፡፡ ስለዚህ የቅዱስ ላለበላን የቅድስና ሕይወትና ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን ግንኙነት ስንረዳ እነዚያ እጅግ ድንቅ የሆኑ ሥራዎቹ በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና በሰማያውያን መላእክት እርዳታ የተሠሩ መሆናቸውን እንረዳለን፤ እግዚአብሔርም ለእኛ የሰጠንን ድንቅ የምሕረትና የቃልኪዳን ስጦታዎቻችን መሆናቸውን እንረዳለን፡፡ ያንጊዜም ውቅር አብያተ ክርስቲያናቶቹን ዓለም ከሚመለከትበት የተለየ መንፈሳዊ ዐይን ይኖረናል፡፡ የቃልኪዳኑም ተጠቃሚዎች ለመሆን መንፈሳችን ይነሳሳል፡፡ በዚህ ደግሞ አሁን ያለውም ሆነ ወደፊት የሚመጣው ትውልድ ታሪኩን ከማጉደፍና ከጥፋት ይጠበቃል፣ አኩሪ ታሪኩንም ጠንቅቆ ለማወቅ መንፈሳዊ ቅናትም ስለሚያድርበት ራሱንም ከውጪው የባሕል ወረራና ጥቃት ይጠብቃል፡፡ በሀገራችን ያሉትን እጅግ ጥልቅ የሆኑ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ ምሥጢሮችን ጠንቅቀው የተረዱት እነ ፕሮፌሰር ፓንክረስት ‹‹ክርስቶስ ከነጮች ይልቅ ለኢትዮጵያውያን ቅርበት አለው›› በማለት ምስክርነታቸውን እየሰጡ ባለበት ወቅት የዘመኑ የሀገራችን ወጣት ማንነቱን ጠንቅቆ ቢያውቀው ኖሮ የእነርሱን (የነጮቹን) ባሕል ለመከተል ባልዳዳው ከዘመናዊ ባርነትም ራሱን በጠበቀ ነበር፡፡

4.መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለቅዱስ ላሊበላ ስለ ቤተመቅደሶቹ አሠራር በዝርዝር እንዳስረዳው፡- በተራ ቁጥር ሁለት ላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በቅዱስ ገድሉ ላይ ከገጽ 117-127 ድረስ በጣም በስፋትና በዝርዝር እንደተጠቀሰው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ላሊበላን እስከ ሰባተኛው ሰማይ ድረስ በመላእክት ተነጥቆ በፊቱ እንዲቆም ካደረገው በኋላ ቤተ መቅደሶቹን እንዴት እንደሚያንጽ ቃል በቃል ነግሮታል፡፡ እግዚአብሔር ለኖህ መርከቡን እንዴት እንደሚሠራ ከነልኬቱ ጭምር በዝርዝር እንደነገረው ሁሉ ለቅዱስ ላሊበላም ዝርዝር ሁኔታዎችን ጭምር እንዲህ በማለት ትእዛዝ ሰጥቶታል፡- ‹‹መልአኩም ክብሩ ከሰማያት ሁሉ ክብር ወደሚበልጥ ወደ ሰባተኛው ሰማይ አደረሰው፣ ቅዱስ ላሊበላም ይህንን አይቶ በግንባሩ ተደፋ፣ ከኪሩቤል ዘንድ ይነሳ የሚል ቃል ተሰማና አንዱ ሱራፌል መጥቶ አነሣው፡፡ ልቡንም አጽንቶ አቆመው…እግዚአብሔርም ተናገረው፡- ‹በምድር ላይ ቤተመቅደስ ትሠራልኝ ዘንድ የማሳይህን አስተውል፤ እዝነ ልቡናህንም ግለጥ፡፡ ከሰው ጋር ስለምኖር በሰማያት የምትኖር አባታችን እያሉ ከሚጠሩኝ በሃይማኖት ከተጐናፀፈኝ ስሜን ከሚያመሰግኑ ከመረጥኳቸው ከሕዝብ አንደበት በምመሰገንበት ገንዘብ እኔ ፈጥሬያቸዋለሁና፡፡

ከመጀመሪያይቱ ድንኳን ውስጥ በተሣለው ላይ ምስላቸው የተሠራ ከሚንቀሳቀሱ ከኪሩቤል አምሳል ለሙሴ እንደተናገርኩት አይደለም፡፡ ወዳጄ ሙሴ የመጀመሪያይቱን ድንኳን አርአያ በደብረ ሲና እንዳሳየሁት ድንኳንን እንደሠራ ሁሉ እንደሁ አንተም እንዳሳየሁህ ትሠራ ዘንድ ዕወቅ፣ አስተውል፣ ተጠንቀቅም፡፡ የማሳይህ ግን ለሙሴ እንዳሳየሁት አይደለም፤ መቅደሴን የምትሠራልኝም ሙሴ እንደሠራው አይደለም፤ ሙሴስ ከተፈተለ ልብስና ከእንጨት ድንኳን ሠራ፤ አንተ ግን ለምሰሶውም ሆነ ለመቀኑ ለመድረኩ እንጨትን
3.5K viewsℍ𝖆𝕭𝖎𝖗, 05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ