Get Mystery Box with random crypto!

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ beteafework — ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ beteafework — ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የሰርጥ አድራሻ: @beteafework
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.40K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-24 22:03:19 #ክፉ_አሳብ

ልጆቼ! ከመጀመሪያውኑ ክፉ አሳብ ባታስቡ መልካም ነው፡፡ ካሰባችሁ ግን ቢያንስ አትናገሩት፡፡ በዚያው በሕሊናችሁ ውስጥ እያለ ዝም አሰኙት፤ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላም ወዳለመኖር ይኼዳል፡፡

እኛ ሰዎች ነን፡፡ በመኾኑም ብዙውን ጊዜ ክፉ፣ ያልተገቡና ጸያፍ ነገሮችን እናስባለን፡፡ ነገር ግን ቢያንስ እነዚህን አሳቦች አንናገራቸው፤ ቢያንስ ወደ ቃል አንለውጣቸው፡፡ ወደ ውጭ እንዳይወጡ አምቀን እንያዛቸው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እየከሰሙና እየደከሙ እየጠፉም ይኼዳሉ፡፡ አንድን እንስሳ ወደ ጉድጓድ ብትጥሉትና ጉድጓዱንም በመክደኛ ብትከድኑት ያ ወደ ጕድጓድ የጣላችሁት እንስሳ የሚተነፍሰውን አየር አጥቶ ይሞታል፡፡ ምናልባት ጥቂት ቀዳዳ ካገኘ ግን በዚያች ቀዳዳ በምትገባው አየር በሕይወት መቆየት ይችላል፡፡ ሲጨንቀውም እናንተን ክፉኛ ለመጉዳት ይዝታል፤ ከወጣም በኋላ ይጎዳችኋል፡፡ ልክ እንደዚሁ እናንተም በልቡናችሁ የተመላለሰውን ኩላሊታችሁ ያጤሰውን ክፉ አሳብ መውጫ ቀዳዳ እንዳይኖረው አድርጋችሁ ብትከድኑት (ብታፍኑት) ይሞታል፤ ከመኖር ወዳለመኖር ይለወጣል፡፡ በአንደበታችሁ በመናገር ጥቂት ቀዳዳ ከከፈታችሁለትና እንደ እንስሳው እንዲተነፍስ ከፈቀዳችሁለት ግን ክፉው አሳብ ክፉ ግብርን ይወልዳል፡፡ ያቆጠቁጣል፡፡ በአሳብ ሳለ ከጎዳችሁ በላይም በገቢር ተወልዶና ተለውጦ ክፉኛ ይጎዳችኋል፡፡

(#የክርስቲያኖች_መከራ #በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ገጽ 7➛በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)
1.6K views19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 07:34:40 "በባልንጀራህ ላይ የምትቆጣ ከሆነ የአንተ ቁጣ በእግዚአብሔር ላይ ነው፡፡ በባልንጀራህ ላይ ቂምን በልብህ የያዝክ ከሆነ ቂምህ በጌታ ላይ ነው፡፡ ባልንጀራህን በከንቱ የምትቆጣው ከሆነ ኃጢአት በአንተ ላይ ይስለጠንብሃል፡፡ ልብህን የፍቅር ማደሪያ ካደረከው በምድር ላይ አንዳች ጠላት አይኖርህም፡፡"

ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
3.6K views04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 00:42:54 #ታላቅ_የበረከት_ጥሪ_ለፍልሰታ

የወልድያ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት የፊታችን ነሐሴ ፩ ለሚጀምረ #ፆመ_ፍልሰታ ለአገልግሎት መፈፀሚያ የሚሆን የመባ እጥረት ላለባቸው የገጠር አብያተ ክርስቲያናት የሚውል መባ የማሰባሰብ ሥራን በመሥራት ላይ ስለሆንን በዚህ የበረከት ሥራ መሣተፍ የምትችሉ ሁሉ ትሳተፉ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ጥሪ እናስተላልፋለን።

መሳተፍ የምትፈልጉ በውስጥ መስመር @natansolo ወይም በሚከተሉት ስልኮች በመደወል ማናገር የምትችሉ መሆኑን አሳውቃለሁ።

#ለበለጠ_መረጃ
0925009689 - ደህንነት አሻግሬ
0967292230 - ቤተልሔም አበበ

በውስጥ መስመር ➛
@natansolo     @natansolo
@natansolo     @natansolo
2.3K views21:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 19:15:49 አባታችን ሆይ እንዴት ትላለህ?

እንደ ልጅ ካልኖርህ እንዴት "አባት" ትለዋለህ? ሌላውን ጠልተህ ራስ ወዳድ ከሆንክ እንዴት አባት "አችን" ብለህ በአንድነት ትጠራዋለህ? ምድራዊ ነገር ብቻ እያሰብህ እንዴት "በሰማያት የምትኖር" ትለዋለህ? ልብህ ከእርሱ ርቆ በአንደበትህ ብቻ እየጠራኸው "ስምህ ይቀደስ" እንዴት ትለዋለህ?

ሥጋዊና መንፈሳዊውን እየቀላቀልህ "መንግሥትህ ትምጣ" ለምን ትለዋለህ? መከራን በጸጋ የማትቀበል ከሆነ "ፈቃድህ ይሁን" ለምን ትላለህ? ለራስህ ሆድ እንጂ ለተራቡት ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ለምን "እንጀራችንን ሥጠን" ትላለህ?

በወንድምህ ላይ ቂም ይዘህ "እኛም የበደሉልን ይቅር እንደምንል" እንዴት ትላለህ? የኃጢአትን አጋጣሚዎች ሳትሸሽ "ወደ ፈተና አታግባን" እንዴት ትላለህ? ክፉን ለመቃወም አንዳች ሳታደርግ "ከክፉ አድነን" እንዴት ትላለህ?
ጸሎቱን ከልብህ ሳትሰማውስ እንዴት አሜን ትላለህ?

#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ
4.9K views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 13:39:37 #ትዕቢት የነበረንን መልካም ምግባር ሁሉ የሚያሳምም ደግሞም የሚገድል ክፋ ደዌ ነው፡፡
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
4.0K views10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 09:37:03 እግዚአብሔር ሰዎችን ኹሉ ሲፈጥራቸው በመንፈሳዊ ማንነታቸው እኩል አድርጎ ነው፡፡ እንዲህም ስለ ኾነ እያንዳንዱ ሰው በጎም ኾነ ክፉ ግብር ለመሥራት እኩል ዝንባሌ አለው፡፡ እግዚአብሔርን ለመታዘዝም ኾነ ላለመታዘዝ እኩል የመምረጥ ዕድል አለው፡፡ ከዚህ ውጪ በኾነ ነገር ግን ሰው ኹሉ እኩል አይደለም፡፡ አንዳንዱ እጅግ አስተዋይ ነው፤ ሌላው ደግሞ ደከም ያለ ነው፡፡ አንዳንዱ በሰውነቱ ብርቱና ጤናማ ነው፤ ሌላው ደግሞ ደካማና ሕመም የሚበዛበት ነው፡፡ አንዳንዱ ሰው መልከ መልካምና ማራኪ ነው፤ ሌላው ደግሞ አይደለም፡፡

ይህ ኹሉ ቢኾንም ግን በኾነ ነገር ስጦታው ያለው ሰው ስጦታው የሌለውን ሌላውን ሰው ሊንቀው አይገባም፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ለእያንዳንዳችን የተለያየ ስጦታን የሰጠን አንዳችን አንዳችንን እንድንጠቅም ነውና፡፡ እግዚአብሔር እያንዳንዳችን ከሌላው ወንድማችን የምንፈልገው ጥቅም እንዲኖር ያደረገው በመካከላችን መጠላላትና መለያየት እንዳይኖር ነው፤ እንድንፋቀርና አንድ እንድንኾን አስቦ ነውና፡፡

ስለዚህ ወዳጄ ሆይ! ወንድምህ ከአንተ ይልቅ አስተዋይና ዐዋቂ፥ ብርቱም ቢኾን በዚህ ቅር አይበልህ፡፡ ከዚህ ይልቅ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ከወንድምህ አስተዋይነትና ዐዋቂነት ብርታትም ትጠቀማለህና፡፡ በዚህ ብቻ ሳታቆምም ራስህን፡- “ስጦታዬ ምንድን ነው? ወንድሜን እኅቴን በምን ልጠቅም እችላለሁ?” ብለህ ጠይቅ፡፡ ይህን ጥያቄ በትክክል ስትመልስ፥ እንደ መለስከው ምላሽም ስትተገብር በአንድ መልኩ በሚበልጥህ ሰው ቅር መሰኘትህን፥ በሌላ መልኩ ደግሞ የምትበልጠውን ሌላውን ወንድምህን መናቅህን ታቆማለህ፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
4.6K views06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 20:51:32 "እሳት ከእርሱ የወጣበትን እንጨት እንደሚያጠፋ ኃጥእም ከእርሱ የመነጨው ክፉ ንግግሩ እርሱን መልሶ ያጠፋዋል።" (#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ)
4.7K viewsedited  17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 06:17:27 ተሰምተው የማይጠገቡ #የዘማሪት_አዳነች_አስፋው የቆዩ ሙሉ መዝሙሮች

#ሰብስክራይብ






6.4K views03:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 19:51:32 "የተሳሳተ እምነት ይዘን መልካም ሕይወት ብንኖር ምንም ጥቅም የለውም፡፡ ልክ እንደዛውም ቀጥተኛ ሃይማኖት ይዘን የኃጢአት ኑሮ ብንኖር ምንም ፋይዳ የለውም፡፡ እምነት ብቻ ለመዳን በቂ አይምሰለን ንጹሕ ሕይወትም አስፈላጊና ወሳኝ ነው፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

@beteafework @beteafework
@beteafework   @beteafework
5.2K viewsedited  16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 16:19:46 #ታላቅ_የበረከት_ጥሪ_ለፍልሰታ

የወልድያ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት የፊታችን ነሐሴ ፩ ለሚጀምረ #ፆመ_ፍልሰታ ለአገልግሎት መፈፀሚያ የሚሆን የመባ እጥረት ላለባቸው የገጠር አብያተ ክርስቲያናት የሚውል መባ የማሰባሰብ ሥራን በመሥራት ላይ ስለሆንን በዚህ የበረከት ሥራ መሣተፍ የምትችሉ ሁሉ ትሳተፉ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ጥሪ እናስተላልፋለን።

መሳተፍ የምትፈልጉ በውስጥ መስመር @natansolo ወይም በሚከተሉት ስልኮች በመደወል ማናገር የምትችሉ መሆኑን አሳውቃለሁ።

#ለበለጠ_መረጃ
0925009689 - ደህንነት አሻግሬ
0967292230 - ቤተልሔም አበበ

በውስጥ መስመር ➛
@natansolo     @natansolo
@natansolo     @natansolo
1.6K views13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ