Get Mystery Box with random crypto!

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የሰርጥ አድራሻ: @beteafework
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.70K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-07-04 08:12:05 ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስምህ፡-

“ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! መንፈሳዊ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይገባል፡፡ ዋጋው የማይታወቅ ነጋዴ ገንዘቡን ሁሉ ሰጥቶ የተወዳጀው እውነተኛ ዕንቁ ደንጊያ አንተ ነህ፡፡ ይህንን የዕንቁ ደንጊያ በሰውነታችን ውስጥ ያበራ ዘንድ ደግሞ ዛሬ ለእኛ አድርግልን፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የተቀደሰው ስምህ የልባችን ደስታ የሰውነታችን ሽልማት ጌጥ ነው፡፡

አቤቱ ምድርንና ዓለሙን ሁሉ ዞርሁ ያለ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በቀር ጣፋጭ ስምን አላገኘሁም፡፡ በምድር ላይ የሚደረግ ረድኤትና ኃይል ሁሉ ያለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በቀር አይሆንም፡፡ እግዚአብሔርን ያገለገሉ የሰው ወገኖች ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኵል ነው፡፡ የከበረና የተመረጠውን እጅ መንሻ ሁሉ ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አልተቀበልንም፡፡ ሰማይና ምድር ያለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከሁከት አልጸኑም፡፡

የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከማር ከወለላና ከሦከር ይጥማል፡፡ ማርና ሦከር በሚበሉበት ጊዜ ይጠገባሉ፤ የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ግን አይጠገብም፡፡ የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በምጠራ ጊዜ ከንፈሮቼ ማርን ያንጠባጥባሉ፡፡ ማር፣ ስኳርና እንጀራ ቢሆኑም እንደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእኔ ዘንድ ጣዕም የላቸውም፡፡ የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሻለኛልና ከሰማይ በታች ካለ ፍጥረት ሁሉም ይበልጣልና፡፡

ቸርነትህ ብዙ ነው፤ አይነገርምም፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! በሚያምንብህና በሚወድህ አፍ ሁሉ ስምህ የታወቀ ነው፡፡ በሕግ ከታወቁ ምስጋናዎች ሁሉ ከውስጣቸው የሚመስልህ የለም፡፡ የዓይኖቼ ብርሃንና የሥጋዬ ብርታት ከከበረው ስምህ ወገን ነው፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! እስከ ሕይወቴ መጨረሻ የከበረ ስምህን በአንደበቴ ዘወትር የተሾመ አድርገው፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትያን ሰውነት ሁሉ የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአንድነት ያከብራሉ፤ ያመሰግናሉ፡፡

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ከኃጢአት ወገን የሚሆን የክፋት መንፈስን ሁሉ ከእኔ አስወግድ፡፡ መዳኛችን በሚሆን በዚህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ክርስቲያኖች ሁላችሁም ፈጽሞ ደስ ይበላችሁ፡፡

የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጣፋጭ ነው፤ በገነት ካለ ፍሬም ይልቅ ይጣፍጣል፡፡ አባታችን ዳዊት በአመሰገነበት በከበረ መዝሙር የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ስም ፈጽሞ እናመሰግናለን፤ እናከብራለን፡፡

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ብዙ የሆነ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በእኔ ላይ አሳድር፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! አንተን ደስ የማያሰኝህን ሓሳብ ሁሉ ከእኔ ታርቅ ዘንድ ወዳንተ እለምናለሁ፤ ከአንተም እሻለሁ፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! በጌትነትህ ከእኔ ጋር ቸርነትህን አድርግ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እንሰግድልሃለን! ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እንሰግድልሃለን! መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሰማያዊ ከሚሆን ከቸር አባትህ ጋራ ማኅየዊ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንሰግድልሃለን፡፡ አሜን!”

(ምንጭ፡ ግብረ ሕማማት)
3.8K views05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 15:15:22 "ወዳጆች ሆይ! ማፈር የሚገባን ኃጢአት ስንሠራ እንጂ ንስሐ ስንገባ አይደለም፡፡ ኃጢአት ሕመም ነው፤ ንስሐ ደግሞ መድኃኒቱ ነው፡፡ ከኃጢአት ቀጥሎ ሐፍረት አለ፤ ከንስሐ ቀጥሎ ግን በጌታ የኾነ ደስታ አለ፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ይህን ቅደም ተከተል አዛብቶብን በኃጢአት ስንደሰት በንስሐም እናፍራለን፡፡"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

"በንስሐ ሕይወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ኃጢአት ምክንያት መደርደር እና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብንም።"
#አቡነ_ሽኖዳ_ሣልሳዊ
4.3K views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 21:28:19 በቅርብ ቀናት በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ ልዑክ ወደ መቐለ እንደሚጓዝ ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ዓርብ ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ/ም ባካሔደው መደበኛ  ስብሰባ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራ የልዑካን ቡድን በሚቀጥሉት ቀናት ወደ ክልል ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ እንዲጓዝ ውሳኔ አስተላልፏል።

ልዑካን ቡድኑ ወደ መቐለ የሚጓዘው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለትግራይ ክልል እንዲሰጥ የተወሰነውን የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስና በትግራይ ከሚገኙ ብፁዓንሊቃነ ጳጳሳት ጋር በሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር  መሆኑ ታውቋል።

ወደ መቐለ በሚደረገው ጉዞ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው የሰላምና አቀራራቢ ኮሚቴ አባላት ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር አብረው ይጓዛሉ።

መረጃው የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።
4.8K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 16:23:06 ከሚሊኒየም አዳራሽ መርሐግብሩን በሚከተሉት አማራጮች በቀጥታ ይከታተሉ
➛በሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ሚዲያ
https://www.youtube.com/live/rCg7yH7TyFc?feature=share
5.3K views13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 15:52:13
ከሚሊኒየም አዳራሽ መርሐግብሩን በሚከተሉት አማራጮች በቀጥታ ይከታተሉ

➛ በማኅበረ ቅዱሳን ዩቲዩብ
https://www.youtube.com/live/pkjwwiKUf_k?feature=share

➛ በኢኦቲሲ ዩቲዩብ
https://www.youtube.com/live/iZQ7BOI7cP8?feature=share

➛ በማኅበር ሚዲያ
https://www.youtube.com/live/PQcOWeUhxdw?feature=share

➛ በመንክር ሚዲያ
https://www.youtube.com/live/AGT0rE9V7w8?feature=share

➛ ET ART MEDIA በፌስቡክ ላይቭ
https://fb.watch/lxaBs0LqbF/?mibextid=ZbWKwL
5.7K views12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 13:10:22 ቀጥታ ከሚሊኒየም አዳራሽ !
መርሐ ግብሩን በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ዩቲዩብ https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia
በቀጥታ ይከታተሉ።

https://www.youtube.com/live/Q-VI3uBwk3w?feature=share
4.7K viewsedited  10:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 08:20:02 ትሕትና

በትክክል ትሑት የኾነ ሰው ማን እንደ ኾነ ማወቅ ትወድዳለህን? በእውነት ያለ ሐሰት ትሑት የነበረውን ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስን ተመልከት፡፡ መምህረ ዓለም፣ መንፈሳዊ አንደበተ ርቱዕ፣ ንዋይ ኅሩይ፣ ወጀብ የሌለበት ወደብ፣ የማይናወጽ ግንብ፣ በአካለ ሥጋ ትንሽ ሲኾን አክናፍ እንደ ተሰጡት ኾኖ ምድርን ኹሉ ያካለለውን ጳውሎስን ተመልከት፡፡ ያልተማረው ግን ደግሞ የተራቀቀውን፣ ድኻ ግን ደግሞ ባለጠጋ የኾነውን ይህን ቅዱስ ሰው ተመልከት፡፡ እልፍ ጊዜ መከራዎችን የተቀበለው፣ አእላፋት ጊዜ ዲያብሎስን ድል የነሣው፣ “ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም፤ ከኹላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ” ብሎ የተናገረው ተወዳጅ ጳውሎስን በእውነት ያለ ሐሰት ትሑት ነው ብዬ እጠራዋለሁ (1ኛ ቆሮ.15፡10)፡፡ ብዙ ጊዜ መታሰርን፣ ብዙ ጊዜ መገረፍን፣ ብዙ ጊዜ በድንጋይ መወገርን፣ [ከበረኻ አራዊት ጋር መጋደልን፣ በባሕር ውስጥ ለሦስት ቀናት ሲዋኝ ውሎ ሲዋኝ ማደርን፣ ቀንና ሌሊት ብዙ ጦምን፣ በብርድና በራቁትነት መኾንን] የታገሠ የተቀበለ፣ በመልእክታቱ ዓለምን በወንጌል መረብነት ያጠመደ፣ ከሰማያት በመጣ ሰማያዊ ቃል የተጠራው እርሱ ራሱን ዝቅ አድርጎ፡- “እኔ ከሐዋርያት ኹሉ የማንስ ነኝ” ያለውን ብፁዕ ጳውሎስ አማን በአማን ትሑት ነው ብዬ እጠራዋለሁ (2ኛ ቆሮ.11፡23-27)፡፡

እንግዲህ የቅዱስ ጳውሎስን የትሕትናው ታላቅነት ታያለህን? ራሱን ዝቅ አድርጎ ታናሽ ነኝ ሲል ትመለከታለህን? “እኔ” አለ ቅዱስ ጳውሎስ፥ “ከሐዋርያት ኹሉ የማንስ፤ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ ነኝ፡፡” በትክክል ትሕትና ማለት ይህ ነው - በኹሉም ረገድ ራስን ዝቅ ማድረግ! ራስን እንደ ታናሽ መቊጠር! እነዚህን ኃይላተ ቃላት የተናገራቸው ማን እንደ ኾነ በነቂሐ ልቡና በሰቂለ ሕሊና ኾነህ አድምጥ! የሰማይ ሰው የምድር መልአክ የሚኾን ጳውሎስ፣ የአብያተ ክርስቲያናት ዓምድ የሚኾን ጳውሎስ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስን እጅግ አብልጬ የምወደውም ለዚህ ነው፡፡ ምግባር ትሩፋት ሥጋ ለብሳ ሥግው ኾና ተውባ ተሞሻሽራ የማያት በእርሱ በብፁዕ ጳውሎስ ዘንድ ነውና፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ፊት በዓይነ ሕሊናዬ ተቀርፆ የሚሰጠኝን ተድላ ደስታ ያህል የብርሃን ጮራዋን የምትለግሰው ፀሐይ ለዓይኖቼ ደስታን አትሰጠኝም፡፡ ምክንያቱም ይህቺ ፀሐይ የሥጋ ዓይኖቼ በብርሃን እንዲያዩ ታደርጋቸዋለች፤ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ ግን ዓይነ ልቡናዬ አክናፍ ኑሮት ወደ ሰማየ ሰማያት እንድወጣ ያደርግልኛል፡፡ ነፍስን ከፀሕይ ይልቅ ጽድልት፣ ከጨረቃም ይልቅ ልዕልት እንድትኾን ያደርጋል፡፡ የምግባር የትሩፋት ኃይሏ ሥልጣኗ ይህን ያህል ነውና - ሰውን መልአክ ታደርገዋለች ፡፡ ነፍስ አክናፍ አውጥታ ወደ ሰማየ ሰማያት እንድትበር ታደርጋለች፡፡ ተወዳጅ ጳውሎስም የሚያስተምረን ይህንን ነው - ምግባርን ! ስለዚህ ነቅተን ተግተን በምግባሩ አብነት እናደርገው፤ እርሱን እንምሰል፡፡

(ከገብረ እግዚአብሔር ኪደ "#ንስሓና_ምጽዋት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው " መጽሐፍ የተቀነጨበ)

@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
4.5K views05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 21:56:59 ነገ ከ 6 ሰዓት ጀምሮ
በሚሊኒየም አዳራሽ እንገናኝ!
መርሐ ግብሩን በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ዩቲዩብ
https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia
በቀጥታ ይከታተሉ።
4.5K viewsedited  18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 21:03:46
በአንድ ወቅት አንድ ወንድም አባ ሙሴ ጸሊምን "አንድን አገልጋይ ባጠፋው ጥፋት የተነሣ ጌታው መታው፡፡ አገልጋዩ ምን ማለት አለበት?" ብሎ ጠየቀው፡፡ አባ ሙሴም "አገልጋዩ ብፁዕ ከሆነ፣ አጥፍቻለሁና ይቅር በለኝ ማለት አለበት፡፡" አለው፡፡ "ሌላ አይጠበቅበትምን?" ሲል ያ ወንድም ጠየቀው፡፡ "አይጠበቅበትም፣ ለጊዜው ለጥፋቱ ሓላፊነቱን ወስዶ አጥፍቻለሁ ካለ ጌታው ይቅር ይለዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ዓለማው በባልጀራ ላይ ላለመፍረድ ነው፡፡ በእውነቱ ጌታችን የግብጽን በኩራት ሁሉ ሲመታ ሰው ያልሞተበት አንድም ቤት አልነበረም" አለና መለሰለት፡፡ ያም ወንድም "ምን ማለት ነው?" አለው፡፡ "ሁላችንም የየራሳችንን ጥፋቶች ካየን የባልንጀራችንን ለማየት ዕድል አንሰጥም፡፡ በራሱ ቤት ሰው የሞተበት በጐረቤቱ ልቅሶ ለማልቀስ አይሄድም፡፡ ለባልንጀራ መሞት ማለት ለራስ ጥፋት ትኩረት በመስጠት፣ የሌላውን ጥፋት ከቁም ነገር አለመቁጠር ነው፡፡ ማንንም አትጉዳ፣ በማንም ላይ ክፉ አታስብ፣ ክፉ የሚሠራውን ሰው አትናቀው፣ በባልንጀራው ላይ ክፉ በሚሠራ ሰው ላይ አትተማመን፣ በባልንጀራው ላይ ክፉ ከሚሠራ ሰው ጋር አትደሰት፣ ለባልንጀራ መዋቲ መሆን ማለት ይህ ነው፡፡ በማንም ላይ አትማረር፣ ነገር ግን 'ሁሉንም እግዚአብሔር ያውቃል'በል፡፡ ከሚያማ ሰው ጋር አትተባበር፣ በሐሜቱም አትደሰት፣ ወንድሙን የሚያማውን ሰውም አትጸየፈው፡፡ አትፍረድ ማለት ትርጉሙ ይህ ነው፡፡ በማንም ላይ የጥላቻ ሐሳብ አይኑርህ፣ ጥላቻ ልብህን እንዲያሸንፈውም አትፍቀድለት፡፡ ባልንጀራውን የሚጠላውን አትጥላው፣ ሰላም ማግኘት ማለት ይህ ነው፡፡"

@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
4.7K viewsedited  18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-01 16:03:10 #በአንድ_ወቅት_እንዲህ_ሆነ

እግዚአብሔር #በአባ_ሙሴ_ጸሊም ላይ አድሮ ከአደረጋቸው ተአምራት መካከል ያለ ወቅቱ ዝናብ እንዲዘንብ ማድረጋቸው አንደኛው ነው፤ ከዕለታት አንድ ቀን በበዓታቸው ምንም ውኃ በሌለበት ቀን አረጋውያን በእንግድነት መጡባቸው፡፡ ውኃ የሚቀዳበት ቦታ በጣም ሩቅ ነበርና የሚያደርጉትን አጡ፡፡ እንግዶቹን ወደ በዓታቸው ካስገቡ በኋላም እግዚአብሔርን "ውኃ ካልሰጠኸኝ ቅዱሳን አገልጋዮችህን ምን አጠጣቸዋለሁ?" እያሉ በጸሎት ይጠይቁት ጀመሩ፡፡ በስሙ ለሚታመኑ ድንቅ ሥራውን መግለጥ ልማዱ የኾነው እግዚአብሔር ጸሎታቸውን ሰምቶ ዝናብ አዘነበላቸውና የውኃ ጉድጓዶችን ሞላላቸው፡፡

እንግዶቹንም እንደ ሥርዓቱ እግራቸውን አጥበው፣ ምግብና ውኃ ሰጥተው አስተናገዷቸው፡፡ አረጋውያኑም በዝናቡ መጣል እየተገረሙ አባ ሙሴን "ብዙ ጊዜ ትወጣ፣ ትገባ የነበረው ለምንድን ነው?" ብለው ጠየቋቸው፡፡ እርሳቸውም "እግዚአብሔርን ውኃ እንዲሰጠኝ እየተማጸንኩት ነበር፡፡ በቸርነቱም ዝናምን ልኮልን ውኃን አገኘን" አሏቸው፡፡ በዚህ ጊዜ በቅዱሳኑ አድሮ ድንቅ ድንቅ ተአምራቱን የሚገልጠውን እግዚአብሔርን አመሰገኑት፤ በአባ ሙሴ ቅድስናም ተደነቁ፡፡

(ሰኔ 24 የቅዱስ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊው የእረፍቱ መታሰቢያ ነው ➛ የቅዱስ ሙሴ ጸሊም በረከቱ አይለየን!!!)

@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
4.3K viewsedited  13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ