Get Mystery Box with random crypto!

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የሰርጥ አድራሻ: @beteafework
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.70K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-16 20:06:47
ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ)
3.4K views17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 07:48:41 እግዚአብሔርን የሚያምንና የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡ ብልህ አገልጋይ ቢኖር፥ እርሱ ወደ ጌታው ሐሴት ገብቶ ዕልል ይበል፡፡

በጾም የደከመ ቢኖር፥ አሁን ደመወዙን ይቀበል፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት ወደ አምላኩ የቀረበ ቢኖር፥ ዛሬ ሽልማቱን ይውሰድ፡፡ በሦስተኛው ሰዓት የመጣ ቢኖር፥ እርሱ በዓሉን በምስጋና ያክብር፡፡ በስድስተኛው ሰዓት የደረሰ ቢኖር፥ አይጎድልበትምና አይጠራጠር፡፡ እስከ ዘጠነኛ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ሳይጠራጠር ይቅረብ፡፡ እስከ ዐሥራ አንደኛዋ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ስለ መዘግየቱ አይደንግጥ፡፡ ጌታ ቸር ነውና፤ በመጨረሻ የመጣውንም እንደ መጀመሪያው አድርጐ ይቀበሏልና፡፡ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ለመጣው ከመጀመሪያው ሰዓት አንሥቶ ሲደክም ከነበረው ጋራ እኩል ይሰጧልና፡፡

መጨረሻ ለመጣው ጌታ ምሕረቱን ይለግሰዋል፤ መጀመሪያ ለመጣውም ያስብለታል፡፡ ለአንደኛው ይሰጠዋል፤ ለሌላኛውም ጸጋውን ያድለዋል፡፡ ለአንደኛው መልካም ምግባሩን ይቀበልለታል፡፡ ለሌላኛውም መልካም ፍቃዱን ይቀበልለታል፡፡ ለአንዱ ምግባሩን ያከብርለታል፤ ለሌላኛውም በቅን ልቡና የሚያደርገውን ጥረት ያደንቅለታል፡፡ ስለዚህ ኹላችሁም ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ፡፡

ፊተኞች ኋለኞችም ሆይ! እኩል ደመወዛችሁን ተቀበሉ፡፡ ባለጸጐች ድኾችም ሆይ! በአንድነት ዘምሩ፡፡ እናንተ ብርቱዎች ደካሞችም ሆይ! በዓሉን አክብሩት፡፡ እናንተ የጾማችሁ መጾም ያልቻላችሁም ሆይ! ዛሬ ላይ ደስ ይበላችሁ፡፡

መሠዊያው ሙሉ ነውና ኹሉም በማዕዱ ደስ ይበለው፡፡ ፍሪዳው የሰባ ነውና አንድ ሰው ስንኳ እንደ ተራበ እንዳይሔድ፡፡ ኹላችንም የእምነት በዓሉን እንካፈል፤ ከቸርነቱና ከፍቅሩ ሀብትም እንቋደስ፡፡

ማንም ስለ ድኽነቱ አይዘን፥ ኵላዊቷ መንግሥት ተገልጣለችና፡፡ ማንም በኃጢአቱ አያንባ፥ ከመቃብሩ የይቅርታ ብርሃን ተንቦግቧልና፡፡ ማንም ሞትን አይፍራ፥ የመድኃኒታችን ሞት ከዚህ ነጻ አውጥቶናልና፡፡ ለእርስዋ በመታዘዝም ጌታ አጥፍቷታልና፡፡ በሞቱ ሞትን ገደለው፡፡ ወደ ሲዖል በመውረድ ሲዖልን በዘበዘው፡፡

ኢሳይያስም አሰምቶ እንደ ተናገረ ሲዖል ከጌታችን ጋር ፊት ለፊት ተገናኘች፤ መረራትም! ከንቱ አድርጓታልና መረራት! ሸንግሏታልና መረራት! ሽሯታልና መረራት!
ነፍሳትን ይዛ እንዳታስቀር አስሯታልና መረራት!
[መቃብር የዕሩቅ ብእሲ] ሥጋ አገኘሁ ብላ ዋጠችው፤ ስትውጠው ግን እግዚአብሔር ኾኖ አገኘችው - መረራትም!

ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ)
1.1K views04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 03:49:30 ትንሳኤከ ለእለ አመነ
በወልድያ መድኃኔዓለም

ሰብስክራይብና ሼር እያደረጋችሁ





https://yt6.pics.ee/4whxlq
https://yt6.pics.ee/4whxlq
2.3K viewsedited  00:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 01:30:56 ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዕዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም
2.6K views22:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 19:26:54
"ከሙታን ተነሥቶ ሲኦልን ረግጦ በሞቱ ሞትን ደመሰሰው” (መጽሐፈ ኪዳን)

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሰን!

@beteafework       @beteafework
3.5K viewsedited  16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 16:32:00 ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት መልእክት





https://yt6.pics.ee/4tlnhk
3.6K viewsedited  13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 13:12:44 በውጊያ ላይ የቆሰለ ወታደር ቁስሉ ይድንለት ዘንድ ለሐኪም ማሳየትን አያፍርም፡፡ ንጉሡም ቢሆን ከቁስሉ የዳነን ወታደር ወደ ሰራዊቱ መልሶ ይቆጥረዋል እንጂ አይተወውም፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ጠላታችን ሰይጣን ያገኘው፣ በኃጢአት የጣለው ሰውም ኃጢአቱን በመናዘዝ የንስሐን መድኃኒት ተቀብሎ መዳንን ማፈር የለበትም፡፡

ቆስሎ ቁስሉን መናገር ያፈረና በቶሎ መድኃኒት ያልተደረገለት ወታደር ቁስሉ ወደ ካንሰር ይለወጥና አመርቅዞ መላ ሰውነቱን በመምታት ይጎዳዋል፡፡ ጉዳቱን ቶሎ የተናገረ ታማሚ ግን ታክሞ በመዳን ወደ ጦር ሜዳው ይመለሳል፡፡ ቁስሉን ባለመታከሙ ወደ ካንሰር የተለወጠበትና ያመረቀዘበት ሰው ግን ሊድን አይችልምና ወደ ጦር ሜዳው ሊመለስ አይችልም፡፡

እንደዚሁ ሁሉ በተጋድሎ ውስጥ ያለ ሰው እንደ ወታደር ነው። በተጋድሎ ውስጥ ያለ ሰው በኃጢአት ወድቆ "በኃጢአት ወድቄአለሁ" ብሎ የተናዘዘ የንስሓን መድኃኒት ያገኛል፡፡ ኃጢአቱን የደበቀ ግን ሊድን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ታማሚው መድኃኒት አግኝቶ ከቍስሉ ሁሉ ይድን ዘንድ በሽታውን ሁለት ዲናር ወስዶ ለሚያክመው ባለ መድኃኒት አልተናገረምና።"

(ቅዱስ አፍርሐት ዘሶርያ - በእንተ ንስሐ ገጽ 52)
719 views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 23:19:35
2.6K views20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 23:19:27 #ቀዳም_ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ)

የዐቢይ ጾም የመጨረሻዋ ቅዳሜ ብዙ ስያሜዎች አሏት፦

#ቀዳም_ሥዑር፡-
በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡

#ለምለም_ቅዳሜ፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡

(የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡)

#ቅዱስ_ቅዳሜ፡-
ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡

(ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም)

@beteafework       @beteafework
@beteafework       @beteafework
2.7K views20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 22:06:34 የመቶ፡ አለቃውና፡ ባለጦሩ ከሕይወት ይልቅ፡ ሞት፡ ይገባሃል፤ እያሉ፡ ያንን ሊቀ ካህናት፡ ይዘልፉት፡ ነበር። በአንድነት፡ ከዘለፉትም፡ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ፡ ይዘውት፡ ሄዱ፤ ወደ ንጉሥም ይወስዱት፡ ዘንድ፡ ተስማሙ።

የድንግል፡ ማርያም፡ በረከት የተወዳጅ ልጅዋም፡ ምሕረት፡ ከእኛ፡ ጋራ፡ ለዘላለም ይደርብን፤ አሜን።

(#ግብረ_ሕማማት)
2.2K views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ