Get Mystery Box with random crypto!

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የሰርጥ አድራሻ: @beteafework
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.70K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 65

2022-08-17 05:39:37 የረቡዕ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ

“እንተ በአማን ንጹሕ ዝናም” የተባለ፣ የነፍሳትን ጥም ያበረደ የሕይወት ዝናም፣ የሕይወት ጠል፣ የሕይወት ውሃ ክርስቶስን ቋጥረሽ (በድንግልና ፀንሰሽ፣ በድንግልና ወልደሽ) የታየሽልን እውነተኛ ደመና አንቺ ነሽ፡፡ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊሥ ዘጋሥጫም፡- “ንዑ እንከ ከመ ናልዕላ ለዛቲ ደመና ብርሃን እንተ ጾረቶ ለማየ ዝናም ንጹሕ" "ንጹሑን የዝናም ውሃ የተሸከመችውን የብርሃን ደመና ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት” ብሎ ጋብዞናል /አርጋኖን ዘሠሉስ ፮፡፪7። ስትወልጂው ማኅተመ ድንግልናሽ አለመለወጡ፤ አካላዊ ቃል ሰው ሲኾን አምላክነቱ  ላለመለወጡ፣ ድንግል ወእም (ድንግልም እናትም) ስትባዪ  መኖርሽም ልጅሽ አምላክ ወሰብእ (ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው) ሲባል ለመኖሩ ምሳሌ ነውና አብ የልጁ ምልክት አደረገሽ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቢያድርብሽ፣ ኀይለ ልዑል ወልድም ሥጋሽን ቢለብስ፤ አንድም መንፈስ ቅዱስ ከሦስቱ ግብራት (ማለትም ከሩካቤ፣ ከዘር፣ ድንግልናን ከመለወጥ) ቢከለክልሽ፣ ኀይለ ልዑል ወልድም ከሦስቱ  ግብራት ቢከልልሽ ለዘላለሙ የሚኖር አካላዊ ቃልን ወለድሽልን  /ሃይ.አበ.፻፲፡፳፱/። እርሱም ሰው ኾኖ ከኃጢአት አንድም ከኃጢአታችን ፍዳ አዳነን።

ደስ ያለህ ባለ ምሥራች ገብርኤል ሆይ! ወደኛ የመጣ የጌታን ልደት ነግረኸናልና ላንተ የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ አንድም “ወነዋ ተወልደ ፍስሐ ዘይከውን ለክሙ ወለኩሉ  ዓለም" "እነሆ ለሕዝቡ ኹሉ የሚኾን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁ” ብለህ /ሉቃ.፪፡፲/የጌታን ልደት ለኖሎት (ለእረኞች) ነገርኻቸዋልና ለአንተ የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ “እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ  ካንቺ ጋራ አንድ ይሆናልና ደስ ይበልሽ” ብለህ /ሉቃ.፩፡፴/ ለእመቤታችን ነግረኻታልና ለአንተ የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ እንዲህ ካለ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳነሣን ለምኚልን፡፡

https://mekrez.blogspot.com/2013/08/blog-post_13.html?m=1
4.9K views02:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 23:36:25 #ለጾመ_ፍልሰታ_አስቸኳይ_መድረስ_ያለበት

ሰላም #የቤተ_ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ቤተሰቦች ለሶስት ቤተ መቅደሶች ለጾመ ፍልሰታ አልግሎት የሚውሉ ንዋዬ ቅድሳት ማለትም የመቀደሻ አልባሳት (ልብሰ ተክህኖ) ያስፈልጋልና ከዚህ በረከት መሳተፍ የምትችሉ @natansolo በውስጥ መስመር አናግሩኝ ባልኩት መሰረት እስከ አሁን ስድስት በጎ ፈቃደኞችን አግኝቻለሁ። ሌሎች በዚህ የበረከት ሥራ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ አሁንም በውስጥ መስመር (@natansolo) ታናግሩኝ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም በድጋሚ እጠይቃለሁ።
2.6K viewsedited  20:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 11:14:12 #በእንተ_ምጽዋት

"ከዕለት ጉርስኽ የተረፈኽ ቢኖር ለደኻ ስጠው። . . . ክብር ይግባውና ወደ ፈጣሪ ለመቅረብ እንደ ምጽዋት ክሂል የሚሰጥ የለም። ከሥራም ወገን ወድዶ ሰጥቶ እንደመቸገር በልቡና ኅድዓት (ፀጥታ ፣ ዕረፍት ፣ ሠላም) የሚያደርግ የለም። ሰጥተኽ መጽውተኽ አጥተኽ 'አላዋቂ' ቢሉኽ ይሻልኻል። ጨብጠኽ ይዘኽ አስተዳደር ዐዋቂ ከሚሉኽ።. . . ኅብስቱን ከውሃ ጣለው ብሎ ተናግሯልና። ከውሃ የጣሉት እንዳይመለስ ፣ 'ይ 'ሰጠኛል' ብለኽ አትስጥ ሲል ነው። አንድም ኀብስቱን ከእግዚአብሔር ፊት አኑረው ሲል ነው። በፍጻሜ ዘመንኽ ዋጋኽን ታገኛለኽ።

ባለጸጋውን ለይተኽ ለድኻ አትስጥ። 'ይኽ ይገባዋል ይኽ አይገባውም' አትበል። አላ ኩሉ ሰብእ ይኩኑ ዕሩያነ በኅቤከ -በምትመጸውትበት ጊዜ አስተካክለኽ መጽውት እንጂ! አስተካክለኽ በመስጠትኽ ወደ በጎ ሥራ ለማቅረብ ትችላለኽ። ምንም የበቁ ባይኾኑ ነፍስ በመብል በመጠጥ ምክንያት ወደ ክቡር እግዚአብሔር ትሳባለችና! በምጽዋት ጊዜ 'ይኽ አይሁዲዊ ነው። ይኽ ከሀዲ ነው' አትበል። 'ይኽ ነፍሰ ገዳይ ነው' አትበል። ይልቁንስ ብታስታውለው ወንድምኽ ነው እንጂ። አእምሮ አጥቶ ከሃይማኖት ተለየ እንጂ።ከበጎው ነገር ወገን ለሰው ያደረግኽ እንደኾነ መክፈልን አትውደድ።. . .

መጽውተኽ ብትቸገር ክብር ይግባውና በእግዚአብሔር ቸርነት ከትካዝ ሥጋዊ ትድናለኽ! ከኹሉ በላይ ትኾናለኽ! ሰው ኹሉ ለገንዘቡ ሲገዛ እሱ ለእግዚአብሔር ይገዛልና። . . . 'በዝናም ያበቀለው በፀሓይ ያበሰለው የእግዚአብሔር ገንዘብ ነው' ብለኽ ምጽዋትኽን በትሕትና መጽውት። ጻድቃን በሚከብሩበት ጊዜ ይቅርታን ታገኛለኽ"

(መጽሐፍተ መነኮሳት (ማር ይስሐቅ) ፣ አንቀጽ ፩ ፣ ምዕ.፲፪፣ ገጽ ፳፩ - ፳፫)
3.8K views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 03:28:34 "የንስሀ አባት ማለት እርሱን ስትመለከት እግዚአብሔርን እና ትዕዛዛቱን የምታስታውስበት ሰው ማለት ነው።"

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
3.9K views00:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 12:54:04 እንኳን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት ለተገለጡበት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን

#የቤተ_ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ቤተሰቦች ለሶስት ቤተ መቅደሶች ለጾመ ፍልሰታ አልግሎት የሚውሉ ንዋዬ ቅድሳት ማለትም የመቀደሻ አልባሳት (ልብሰ ተክህኖ) ያስፈልጋልና ከዚህ በረከት መሳተፍ የምትችሉ @natansolo በውስጥ መስመር አናግሩኝ ባልኩት መሰረት እስከ አሁን ስድስት በጎ ፈቃደኞችን አግኝቻለሁ። ሌሎች በዚህ የበረከት ሥራ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ አሁንም በውስጥ መስመር (@natansolo) ታናግሩኝ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም በድጋሚ እጠይቃለሁ።
4.1K views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 06:24:34 " ሃሌሉያ እምርት ዕለት እንተ ርዕያ አብርሃም መዘምራኒሃ ለደብረ ብርሃን አርያም እንዘ ይብሉ ይዜምሩ በልሳን ዘኢያረምም አማን መንግሥተ ሥላሴ ዘለዓለም።

"ሃሌሉያ በዚያች ዕለት በብርሃን በተመላች (በተከበበች) ተራራ ላይ ያለድካምና በማያቋርጥ አንደበት የሥላሴ መንግሥት ዘለዓለማዊ ናት እያሉ ሲዘምሩ (ሲያመስግኑ) ብርሃም አየ።"

ምልጣን ዘሐምሌ ፯

እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ!!!
4.4K views03:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:24:39
4.8K views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 21:24:31 #ሐምሌ_7

#ቅድስት_ሥላሴ

ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡

አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡

ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡

እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት ይርዳን!

(ስንክሳር ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ፔጅ)
5.7K views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 09:19:40 "እስከ አሁን ያልወደቅነው ስላልተገፈተርን ወይም ስላልተገፋን ሳይሆን እግዚአብሔር ደግፎ ስላቆመን ብቻ ነው።"
4.5K views06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 11:19:31 እንኳን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕት ለሆኑበት ዕለት በሰላም አደረሰን

#የቤተ_ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ቤተሰቦች ለሶስት ቤተ መቅደሶች ለጾመ ፍልሰታ አልግሎት የሚውሉ ንዋዬ ቅድሳት ማለትም የመቀደሻ አልባሳት (ልብሰ ተክህኖ) ያስፈልጋልና ከዚህ በረከት መሳተፍ የምትችሉ @natansolo በውስጥ መስመር አናግሩኝ ባልኩት መሰረት እስከ አሁን አምስት በጎ ፈቃደኞችን አግኝቻለሁ። ሌሎች በዚህ የበረከት ሥራ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ አሁንም በውስጥ መስመር (@natansolo) ታናግሩኝ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ።
4.9K viewsedited  08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ