Get Mystery Box with random crypto!

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የሰርጥ አድራሻ: @beteafework
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.70K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-07-19 18:11:08
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ባሕረ ምስጢራት የሆነ የሰውን ፊት አይቶ የማያደላ "መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ" (በርሱ ዘንድ ንጉሥ፣ ሐብታም፣ ደሃ፣ ነዳይ እኩል ነውና)፣ አፈ በረከት፣ አፈ መዐር (ማር)፣ አፈ ሶከር (ስኳር)፣ አፈ አፈው (ሽቱ)፣ ልሳነ ወርቅ፣ የዓለም ሁሉ መምሕር፣ ርዕሰ ሊቃውንት፣ ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)፣ የሐዲስ ኪዳን ዳንኤል፣ ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)፣ ጥዑመ ቃል... እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በረከቱ ይደርብን።
6.0K views15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-19 06:49:16 "ስለታሙ የሐሜት ጥርስህ የሚያርፈው በወንድምህ ሥጋ ላይ ሳይሆን ነፍስ ላይ ነው፡፡.በዚህም ጥርስህ ወንድምህን በእጅጉ ትጎዳዋለህ፡፡ እንዲህ በማድረግህ አንተም እርሱንም ሌሎችንም ብዙ ሺህ ጊዜ ትጎዳቸዋለህ፡፡ በሐሜትህ አንተን የሚሰማህ ባልንጀራህ የሐሜት ተባባሪ ይሆናል፡፡ በዚህም ምክንያት እርሱንም በደለኛ ታደርገዋለህ፡፡ እርሱም በእርሱ ላይ ከነገሠበት ኃጢአት የተነሣ ለሌላ ለወዳጁ ምን መርጦ ማውራት እንዳለበት ሳያውቅ ከሐሜተኞች ጎራ ይቀላቀላል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰው ጻድቅ ልንለው እንችላለንን? እንዲህ ዓይነት ሰው በመጦሙ ትልቅ የጽድቅ ሥራን እንደፈጸመ ቆጥሮ ይኩራራል፡፡ ሰዎችን ወደ ኃጢአት እየመራ ትልቅ ሥራን እንደሠራ ሰው ራሱን በከንቱ ያስኮፍሳል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ሊታይ የሚገባው ትልቁ ቁም ነገር ስለቤተክርስቲያን ጥቅም ሲባል የእንዲህ ዓይነቱን ሰው ንግግር ከመስማት መከልከል እንደሚገባ ነው፡፡ ምክንያቱም የዚህ ሐሜተኛ ወሬ እርሱን ብቻ ኃጢአተኛ የሚያሰኝ ጉዳይ ሳይሆን ቤተክርስቲያንንም ጭምር የሚያሰድብ ነውና፡፡

ስለዚህ በጦም ሰዓታችሁ ጊዜም ይሁን አይሁን ሦስት ነገሮችን በሕሊናችሁ ትይዙ ዘንድ እመክራችኋለሁ፡-
እነርሱም....
✟ ክፉ ከመናገር መከልከልን፣
✟ ማንንም ሰው እንደጠላት ከማየት መቆጠብንና
✟ እንደልምድ አድርጋችሁ ከያዛችሁት መሐላ ትርቁ ዘንድ እመክራቸኋለሁ፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
6.8K views03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-18 21:41:26 #ዕጣንና_ጽንሃ_በቤተክርስቲያን

#ዕጣን
ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ዕጣንን የተመላ ሰማያዊ ማዕጠንት በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት እየሰገዱ ለአለም ድህነት የሚለምኑበት ነዉ፡፡ በቤተክርስቲያን ካህናት መንፈቀ ሌሊት ፡ በነገህ ጊዜ በቅዳሴ ጊዜ በየማዕዘኑ ዕጣን ያጥናሉ ቅዳሴውን ጸሎቱንና ልመናዉን ወደ እግዚአብሔር ያሳርጉበታል ፡፡

ስለ እጣን የመፅሀፍ ቅዱስ ማስረጃ

ዘጸ 30፥1 የዕጣን መሰዊያዉን ስራ ከግራር እንጨት አድርገው።

ዘጸ 30፥35 በቀማሚ ብለሀት እንደተሰራ፥ በጨዉም የተቀመመ ንጹህና ቅዱስ እጣን አድርገው፡፡

ዘጸ 30፥34 እግዚአብሄርም ሙሴን አለዉ፦ ጣፋጭ ሽቱ ዉሰድ የሚንጠባጠብ ሙጫ በዛጎል ዉስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸትትም ሙጫ፥ ጥሩም ዕጣን ዉሰድ የሁሉም
መጠን ትክክል ይሁን፡፡

ዘፀ 40፥5 ለዕጣንም የሚሆነዉን የወርቅ መሠዊያ በምስክሩ ታቦት ታኖራለህ፥ በማደሪያዉም ደጃፍ ፊት መጋረጃዉን ትጋርዳለህ፡፡ ዘጸ 40፥27 የጣፋጩን ሽቱ ዕጣን አጠነበት፡፡

ዘሌ 10፥1 የአሮንም ልጆች ናዳብና አብድዩድ በየራሳቸዉ ጥናዉን ወስደዉ እሳት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት በእግዚአብሔር ፊት እሱ ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት አቀረቡ፡፡

ዘሌ 16፥12 በእግዚአብሔር ፊት ካለዉ መሠዊያ ላይ የእሳት ፍም አምጥቶ ጥናዉን ይሞላል፥ ከተወቀጠውም ከጣፋጭ እጣን እጁን ሙሉን ይወስዳል ወደ መጋረጃውም
ዉስጥ ያመጣዋል፡፡

ዘኁ 16፥7 ነገም በእግዚአብሔር ፊት እሳት አድርጉባቸው፥ ዕጣንም ጨምሩባቸው እንዲህም ይሆናል እግዚአብሔር የሚመርጠው እርሱ ቅዱስ ይሆናል እናንተ የሌዊ ልጆች
ሆይ እጅግ አብዝታችኀል ብሎ ተናገራቸው፡፡

ዘዳ 33፥10 ፍርድህን ለያዕቆብ፥ ህግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ ፤ በፊትህ ዕጣንን፥ በመሰዊያህም የሚቃጠል መስዕዋት ይሠዋሉ፡፡

መዝ 140፥2 ጸሎቴን በፊትህ እንደ እጣን ተቀበልልኝ ፥ እጅ መንሳቴም እንደሰርክ መስዕዋት ትሁን፡፡

ማቴ 2፥11 ወደ ቤትም ገብተው ህጻኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር እዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት ሣጥኖቻቸዉንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤን አቀረቡለት፡፡

ሉቃ 1፥10 በዕጣንም ጊዜ ህዝቡ ሁሉ በዉጭ ቆመውዉ ይጸልዩ ነበር፡፡

ራእ 5፥8 መጽሀፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንሰሶችና ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳዳቸም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ፡፡

ራእ 8፥3 ሌላም መለአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለዉ በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ
እጣን ተሰጠዉ

#ጽንሃ

ጽንሃ የእጣን ማሳረጊያ ወይም ማጠኛ ነው። ሦስት ሰንሰለቶች አሉት። ሰንሰለቶቹ ሶስት መሆናቸው የሚስጢረ ሥላሴ ምሳሌ ነው። በሰንሰለቶቹ ላይ ቢያንስ አስራ ሁለት (12) ቢበዛም ሃያ አራት (24) ሻኩራዎች ይኖሩታል።
‘’ሻኩራ’’ ማለት ሶስቱ ሰንሰለቶች ላይ ያሉት ክብ ነገሮች ናቸው። የሻኩራዎቹ ቁጥር አስራ ሁለት (12) መሆኑ የሐዋሪያት ምሳሌ ነው። ሃያ አራት (24) መሆኑ ደግሞ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ምሳሌዎች ናቸው ። ከስሩ እጣኑ የሚቀመጥበት ሙዳይ የመሰለ ክፍል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ሲሆን: መለኮት ከሥጋዋ ሥጋ ነፍሱዋ ነፍስ ነስቶ ሰው መሆኑን ያመለክታል። ፍሙ የጌታችን የመለኮትነቱ ምሳሌ ሲሆን እጣኑ እንደሚቃጠልና መዓዛው ሁሉን እንደሚያውድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ብዙዎች ኃጢያት ራሱን መስዋዕት በማድረግ አቅርቦ ዓለሙን ሁሉ ማዳኑን ያሳያል።
5.8K viewsedited  18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-18 15:36:53
#ታላቅ_የበረከት_ጥሪ_ለፍልሰታ

የወልድያ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የፈለገ ሰላም ሰ/ት/ቤት የፊታችን ነሐሴ  ፩ ለሚጀምረ #ፆመ_ፍልሰታ ለአገልግሎት መፈፀሚያ የሚሆን የመባ እጥረት ላለባቸው የገጠር አብያተ ክርስቲያናት የሚውል መባ የማሰባሰብ ሥራን በመሥራት ላይ ስለሆንን በዚህ የበረከት ሥራ መሣተፍ የምትችሉ ሁሉ ትሳተፉ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ጥሪ እናስተላልፋለን።

መሳተፍ የምትፈልጉ @natansolo በውስጥ መስመር ማናገር የምትችሉ መሆኑን አሳውቃለሁ።

@natansolo     @natansolo
@natansolo     @natansolo
8.2K views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-18 06:43:31 «ወዳጄ ሆይ! እግዚአብሔር ነዳያንን የሚልክልህ መስጠትን እንድትለማመድ ነው፡፡ ዛሬ በነዳያኑ አድሮ የሚለምንህ ለኋለኛይቱ ቀን ስንቅ እንዲያስቀምጥልህ ወድዶ ነው፡፡ ታድያ ንጉሥ ወደ ቤቱ መጥቶ የሚያባርር ሰው እንደምን ያለ ጎስቋላ ሰው ነው? እንግዲያውስ ነዳያንን ስታይ ወደ አንተ የመጣው ንጉሠ ሰማይ ወምድር ክርስቶስ እንጂ ሰው አይደለምና አትግፋው፡፡ በረከትህንም ከቤትህ አውጥተህ አትሸኘው፡፡»

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
7.4K views03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-17 23:11:46 ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች

ይህንን #የቤተ_ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅን ቻናል ለወዳጆቻችሁ በማጋራት ቤተሰብ ይሆኑ ዘንድ ጋብዙልን!

(በተለያዩ ግሩፖችና ቻናሎች ያጋሩ)

https://t.me/beteafework
8.2K viewsedited  20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-17 06:21:08 “እኔ ክርስቲያን ነኝ፡፡ ለሚጠይቁት እንደዚህ ብሎ የሚመልስ ሰው በአንድ ጊዜ በኹሉም ነገሮቹ ላይ ማወጁ ነው፡፡ ሀገሩ የት እንደ ኾነ፣ ሥራው ምን እንደ ኾነ፣ ቤተሰቡ እነማን እንደ ኾኑ መመስከሩ ነው፡፡ ክርስቲያን የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ነዋሪ እንጂ በምድር ላይ ካሉት ከተሞች የአንዲቱም አይደለምና፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
9.8K views03:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 14:59:37
ቅዱስ ሲኖዶስ የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫን ያካሄደ ሲሆን በሕገወጥ መልኩ ተሹመው የነበሩ መነኮሳት መካተታቸው ተስተውሏል !

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው ልዩ ስብሰባ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች በተደራቢነት ተይዘው ለቆዩ ክፍት በኾኑና አንገብጋቢ ችግር ባለባቸው ዘጠኝ አህጉረ ስብከት ላይ የሚመደቡ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጰሳትን ምርጫ ማካሄዱ ተረጋግጧል፡፡

በዚህም መሠረት፡- ለኦሮሚያ ክልል 7 አህጉረ ስብከት
1. አባ ሣህለ ማርያም ቶላ - ምዕራብ አርሲ - (ሻሸመኔ) ሀገረ ስብከት
2. አባ ወልደ ገብርኤል አበበ - ምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት
3. አባ ጥላሁን ወርቁ - ምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት
4. አባ ዓምደ ሚካኤል ኀይሌ - ሆሮ ጉድሩ ወለጋ - ሻምቡ ሀገረ ስብከት
5. አባ ኀይለ ማርያም ጌታቸው - ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት
6. አባ ዘተክለ ሃይማኖት ገብሬ - ምዕራብ ወለጋ ሀገረ ስብከት
7. አባ እስጢፋኖስ ገብሬ - ቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት

ለደቡብ ኢትዮጵያ 2 አህጉረ ስብከት፤
8. አባ ክፍለ ገብርኤል ተክለ ሐዋርያት - ጌዴኦ አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት
9. አባ ስብሐት ለአብ ወልደ ማርያም - ዳውሮ እና ኮንታ ሀገረ ስብከት ሆነው መመረጣቸው የተረጋገጠ ሲሆን ከእነዚህ ተመራጮች መካከል 3ቱ
➛ አባ እስጢፋኖስ ገብሬ
➛ አባ ኃይለማርያም ጌታቸው
➛ አባ ዐምደሚካኤል ኃይሌ በጥር 14ቱ ሕገወጥ "ሢመት" የተሳተፉ ናቸው።

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
2.9K views11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 08:26:02 "ትህትና"

✞ ትህትና መድኅን ነው ከሰይጣን አሽክላ ያድንሃል። / አባ እንጦንስ/
✞ ትህትና የሰው ዘመድ ነው። / አባ አሞን /
✞ ትህትና የማይናድ ደልዳላ መሬት ነው። /አባ አርሳንዮስ /
✞ ትህትና ክርስቲያናዊ ምልክት ነው። /አባ መቃርስ/
✞ ትህትና የሰው ሁሉ ጋሻ ጦር ነው። /አባ በሐይ/
✞ ትህትና ግድግዳን የምታስጌጥ የአፈር ወይዘሮ ናት። /አባ አጋቶን/
✞ ትህትና የመንግስተ ሰማያት መመላለሻ በር ነው። /አባ ሚልኪ/
✞ ትህትና ሕፀጽን የሚያስታውቅ መስታወት ነው። /አባ ጰርዬ /
✞ ትህትና የነፍሳት ወደብ ነው። /አባ ዮሐንስ/
✞ ትህትና የወንጌል ትእዘዝ መጀመሪያ ነው። /አባ ዮሐንስ ሐፂር/
✞ ትህትና ወደ ንፁሐ ልቡና ሰገነት የሚወጡበት ነው
✞ ትህትና ዕፀ ሕይወት ናት።/አባ መቃርስ /
3.8K views05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 11:07:22 ቆየት ያለ መዝሙር
#ሐዋርያት_የሰበኩሽ

ሐዋርያት የሰበኩሽ
ሰማዕታት የሞቱልሽ
ጻድቃንም የከበሩብሽ
ተዋሕዶ ርትዕት ነሽ (2)

መንፈስ ቅዱስ ወዶ ፈቅዶ
ፊልጶስን ጋዛ ሰዶ
ለጃንደረባው ያሰበከሽ
ተዋሕዶ ሃይማኖት ነሽ (2)

የቀደመች ጽኑ መንገድ
የሰማዕታት የጽድቅ እምነት
በሰማይና በምድር ያለሽ
የቅዱሳን ሃይማኖት ነሽ (2)

ጠላት ዲያብሎስ ቢቃወምም
ቀስቱን ቢጨርስ ቢፋለምም
የጸናችውን በጌታ ደም
የሚረታሽ ማንም የለም (2)

የአትናትዮስ ልዩ ግርማ
የቄርሎስ የሰላማ
የአበው ቅርስ የሊቃውንት
ተዋሕዶ ቅድስት እምነት (2)

የቅዱስ ያሬድ ጥዑም ዜማ
የተክለ ሃይማኖት የገሪማ
የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
የጽድቅ የሰላም ነሽ እንግጫ (2)

በቅዱስ ጴጥሮስ መሠረት ላይ
መሥርቶሻል አዶናይ
የኑፋቄ ጦር ቢከፈትም
የገሃነም ደጆች አይችሉሽም (2)

አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት
ወልድ ዋሕድ ሁለት ልደት
ቤተ ክርስቲያን ተሕዋዶ
የሠራልን አምላክ ፈቅዶ (2)
የሰው ልጅ ሁሉ በአንቺ አምኖ
ዘለዓለም ኑሪ ግርማሽ ገኖ (2)
(ዘማሪት አዳነች አስፋው)
#subscribe





5.0K views08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ