Get Mystery Box with random crypto!

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የሰርጥ አድራሻ: @beteafework
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.70K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-07-01 09:49:58 ቅዱስ ሙሴ ጸሊም የሐሳብ ኃጢአቶች ያጠቁት ነበር፡፡ ሁልጊዜም ስለ እነዚህ ሐሳቦች ሊያማክረው ወደ ንስሐ አባቱ ወደ ቅዱስ ኤስድሮስ ይሔድ ነበር፡፡ ለአሥራ አራት ጊዜያት ከተመላለሰ በኋላ ቅዱስ ኤስድሮስ ከበአቱ በላይ ይዞት ወጣና ‹‹ወደ ምእራብ ተመልከትና ያየኸውን ንገረኝ›› አለው፡፡ ‹‹አጋንንት ወደ መነኮሳት የእሳት ጦሮችን ሲወረውሩ አየሁ›› አለው፡፡ ቀጥሎም ‹‹ወደ ምሥራቅ ተመልከት ፤ ምን ይታይሃል?›› አለው፡፡ ሙሴ ጸሊምም ‹‹መላእክት ጦሮቹን እየመከቱ ለመነኮሳቱ ሲከላከሉ አየሁ›› አለ፡፡ ‹‹እንግዲያውስ ማናቸው ይበልጣሉ ፤ የሚያጠቁን ወይስ የሚጠብቁን?›› ቅዱስ ሙሴ መለሰ ‹‹የሚጠብቁን!›› ወዲያውኑ ይኽን ሲናገር ክፉ ሃሳቦች እርሱን መዋጋት አቆሙ፡፡

1ኛ ጴጥ.5÷8 "በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤"

ዕብ.12÷1-2 "እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ"

ዜና መዋ. 3÷7 "ጽኑ፥ አይዞአችሁ ከእኛም ጋር ያለው ከእርሱ ጋር ካለው ይበልጣልና"

(ሰኔ 24 የቅዱስ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊው የእረፍቱ መታሰቢያ ነው ➛ የቅዱስ ምልጃ አይለየን)

@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
4.5K views06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 20:50:01
እንዳይፈረድብህ በባልንጀራህ ላይ አትፍረድ

በአንድ ወቅት በግብጽ ገዳማት አንድ ወጣኒ መነኩሴ “ጥፋት አጠፋ፣ ሥርዓተ ገዳም አፋለሰ” ተብሎ መናንያኑ ጉዳዩን እንዲያዩና እንዲወስኑበት ከየበአታቸው ተጠሩ፡፡ ከተጠሩት መነኮሳት መካከል አንዱ ጥቁሩ ኢትዮጵያዊው ሙሴ ጸሊም ነበር፡፡ እርሱም ሁሉም ከተሰበሰቡ በኋላ ዘግይቶ በተቀደደ አቁማዳ አሸዋ በጀርባው አዝሎ አሸዋውን ከኋላው እያፈሰሰ መጥቶ በመሃላቸው ተገኘ፡፡

የተሰበሰቡት መነኮሳትም አባ ሙሴን ይህን ስለምን አደረግከው ብለው በጠየቁት ጊዜ በሀዘን ተውጦ “በጀርባዬ የማላያቸውን ስፍር ቁጥር የሌላቸው ኃጢአቶቼን ተሸክሜ ሳለሁ በወንድሜ ለመፍረድ መጥቻለሁ” አላቸው፡፡ መነኮሳቱም እጅግ ተጸጸቱ፡፡ ጉባኤውም ፍርዱን ትቶ ተበተነ፡፡

“እንዳይፈረድብህ በባልንጀራህ አትፍረድ” የሚለውን የወንጌል ቃልም በተግባር አስተማራቸው፡፡ ልብን በሚነካ በዚህ በጎ ትምህርቱም መነኮሳቱን ከመፍረድ ሃጢአት ታደጋቸው፡፡

(ሰኔ 24 የቅዱስ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊው የእረፍቱ መታሰቢያ ነው ➛ የቅዱስ ምልጃ አይለየን)

@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
@beteafework    @beteafework
5.1K viewsedited  17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 18:34:42
#ሰኔ_25
#በሚሊኒየም_አዳራሽ
ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ

‹‹የፈረሰውንሞ አድሳለሁ፤ እንደቀደመውም ዘመን እሠራታለሁ፡፡›› ት.አሞ ፱፥፲፩

በጦርነቱ የተጎዳውን የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት መዋቅር ከመፍረስ ለመታደግና መንፈሳዊ አገልግሎቶች የተቋረጠባቸውን አብያተ ክርስቲያናትና የልማት ፕሮጀክቶች እንደገና ለማስቀጠል ብፁዓን አባቶች፣ ተጋባዥ እንግዶች፣ ሰባኪያነ ወንጌል እና መዘምራን የሚገኙበት ልዮ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር

#የመግቢያ_ትኬት ➛1ዐዐ ብር ብቻ
#የመግቢያ_ትኬት_የሚገኝበት_ቦታ፦
➛ በማኅበረ ቅዱሳን ሱቆች
➛ በአሐዱ ባንክ ቅርንጫፎች
➛ በአጥቢያ ቤተ ክርስትያናት ሰንበት ት/ቤት ሱቅ
➛ በመንፈሳዊ ንዋየ ቅዱሳት እና መጻሕፍት መሸጫ ሱቆች ታገኛላችሁ

#ድጋፍ_ለማድረግ
#ወገን_ፈንድ
➛ http://www.wegenfund.com/eotc-nw
#ጎፈንዲሚ
➛ http://GoFund.Me/7A32F37F
#ቡና_ባንክ ➛1516
#አዋሽ_ባንክ ➛1516
#ዳሽን_ባንክ ➛ 1516
#ወጋገን_ባንክ ➛ 1516
#አቢሲኒያ_ባንክ ➛ 1516
#በኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ➛3540

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር
➛ 0993-107080
➛ 0979-006834

➛ ሼር ይደረግ
6.3K views15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-30 15:45:17
4.0K views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 08:50:44 ኣባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ስለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፡-

ዮሐንስን በቤተ መቅደስ ፊት የእመቤታችን የማርያም ስእል ነበረችና አፈወርቅ ብላ ጠራችው፤ ስለዚህም ዮሐንስ አፈወርቅ ተባለ፡፡ ያእቆብ በእግዚአብሔር አንደበት እስራኤል እንደተባለ እንዲሁ ዮሐንስ በማርያም ስእል አንደበት አፈወርቅ ተባለ፡፡

እኔም ስለርሱ እላለሁ፦
በእውነት አፈወርቅ አፈ እንቁ ስለ አምላክ ከድንግል መወለድ ፍቅር የወር አበባ ያላትን ሴት አንቀፀ ስጋ ለመሳም ያላፈረ በእውነት አፈ ጳዚዮን ነው፡፡

በድርሰቶቹ ቤተክርስቲያንን የሚያስጌጣት አፈ ባሕርይ በእውነት አፈ መአር በቃሉ ጣፋጭነት ምእመናንን የሚያለመልማቸው አፈ ሶከር (ስኳር) በእውነት በትምህርቱ መአዛ የምስጢር በጎችን ደስ የሚያሰኛቸው አፈ ሽቱ አፈ ርሄ ነው፡፡

በእውነት በውግዘቱ ስልጣን ከሃዲወችን የሚቆርጥ አፈ ሰይፍ አፈ መጥባህት ነው፡፡

በእውነት የማይነዋወጥ አምድ የማይፈርስ መሰረት በእውነት ከሞገዶች መነሳት የተነሳ የማይሰበር መርከብ በሃይማኖት ባሕር ውስጥ የሚዋኝ ዋናተኛ ነው፡፡

በእውነት የማይፈርስ ግንብ በጠላት ፊት የሚፀና አዳራሽ ነው፡፡
796 viewsedited  05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 13:28:57 #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ከቅዱሳን_ባሕታውያ_ጋር

በአንድ ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡-ከዕለታት አንድ ቀን በሀገረ ስብከቴ ሥር በነበሩ በሜዲትራኒያን ባሕር በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ምእመናንን ለመጎብኘት አሰብሁ፡፡ ከእኔ ጋር ቀሳውስትንና ዲያቆናትን አስከትዬ በጀልባ ተሳፍሬ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዝሁ፡፡ በደሴቱ ውስጥ ስንዘዋወር የሰው ዱካ ብንመለከትም ምንም ሰው ማየት አልቻልንም ነበር፡፡ በአሸዋው ላይ ታትሞ የነበረውን የሰው ዱካ ተከትለን ስንጓዝ ካልተፈለፈሉ ዐለቶች የተሠራ ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ዋሻ ላይ ደረስን፡፡

ዋሻው በርም ሆነ መስኮት የለውም፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ ልክ እንደ ሰባቱ ደማቅ ከዋክብት እጅግ በጣም አንጸባራቂ ብርሃን ቆመው ከሚጸልዩ ሰባት አባቶች ዘንድ ሲወጣ ተመለከትን፡፡ እኛም ከእነርሱ ጋር ለመጸለይ ባለንበት ቆምን። አባቶች ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ እኛ ዞሩና በፊቴ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ። በመቀጠልም ሰላምታ ሰጡን፡፡ እኔ ዮሐንስም ‘እኔ አባታችሁና ፓትርያርካችሁ ዮሐንስ ነኝ’ አልኳቸው፡፡ ቅዱሳኑ እንደገና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በፊቴ ሰገዱ እና እኔን ደካማውን እንዲህ አሉኝ፡- “የምንወደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትባርከንና እኛም አንተን በማየት እንድንበረታ ወደዚህ አመጣህ” አሉ። እኔም “እባካችሁ ታሪካችሁን ንገሩኝ” አልኋቸው፡፡

ሰባቱ አባቶችም “ከብዙ ዓመታት በፊት ሰባታችንም ከቍስጥንጥንያ ወጥተን በአንድነት ተሰባስበን ሕይወታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና በአምልኮ ብቻ ለማሳለፍ ወደዚህ ደሴት መጣን፡፡ ከዚህ ደሴት በደረስንበት ዕለት ከባሕሩ ከሚመጣው አስቸጋሪ ነፋስ ራሳችንን ለመከላከል ዋሻዎችን ለመገንባት ዐለቶችን ሰበሰብን፤ በሁለተኛው ቀን ደግሞ ይህን ቤተ ክርስቲያን መሥራት ጀመርን፡፡ በዐለቶች መካከል ከሚበቅለው ሣር እንበላለን፤ ውኃም ከባሕሩ እንጠጣለን፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን የከበቡትን እነዚህን የአሸዋ ክምሮች ለማስወገድ ፈልገን ነበር፤ ግን አእምሯችንና አሳባችን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ስለተያዘ ጊዜ አጣን” በማለት ታሪካቸውን ነገሩኝ።

እኔም “መንፈሳዊ አባታችሁ የት ነው?” ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ ይህን ጥያቄ ከመጠየቄ ወዲያውኑ አንድ ሽማግሌ በትሩን ተደግፎ ወደ እኔ ቀረብ አለና “እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ” አለኝ፡፡ አረጋዊው ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ራቁቱን ነበረና “ሰውነትህን የምትሸፍንበት ትንሽ ልብስ ትፈልጋለህ?” ስለው እሱም “ጌታ ከክረምቱ ቅዝቃዜ፣ ከበጋው ሙቀት ይከላከልልናል፤ ይጠብቀናልም” በማለት መለሰልኝ፡፡ “ምግብ ያስፈልጋችኋል?” ብዬ ስጠይቀው እርሱም “የሚበቃንን ያህል ከእነዚህ ዕፅዋት እንመገባለን ከዓለም የሆነ ምንም ነገር አያስፈልገንም” በማለት መለሰልኝ፡፡

እኔም “አባቶቼ እባካችሁ ለእኔ እና ስለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ጸልዩ” አልሁት። የእነዚያን ቅዱሳን ባሕታውያን አባቶች በረከት ከተቀበልን በኋላ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም ምሥጋና የሚገባውን የምንወደውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገንን ወደ መጣንበት ተመለስን” ይለናል ቅዱሱ አባታችን ዮሐንስ አፈ ወርቅ።

ምንጭ፦ ግሑሣን አበው
2.5K views10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 09:28:51 ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ማን ነው?
ሕይወቱስ?
እኛስ ከቅዱሱ ሕይወት ምን እንማራለን?

share and Subscribe






2.9K viewsedited  06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 06:58:12 ስለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ John chrysostom ልፅፍ አስቤ መፃፍ አልቻልኩም አቅም አጠረኝ፡፡ በርግጥ ስለሱ መናገር አልችልም ቅድስናው ሊቅነቱ ትህትናው ክርስቲያናዊ ፍልስፍናው የሰባክያን መለኪያነቱ መግለፅ ይከብደኛልና፡፡
ለኔ ከሐዋርያትም ይልቅብኛል ቅዱስ ያሬድ እንዳለው አፈ ጳዝዮን ነው ከቅዱሳን ማንን ማየት ትሻላችሁ ብንባል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ማየት ሁሉንም ከማየት ጋር እኩል ነውና እሱን ብቻ አሳየኝ እለው ነበር፡፡
በረከቱ ዕረፍቱ በሚታሰብበት ግንቦት12 በእጥፍ ይደርብን ፡፡
3.1K views03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 19:39:47 #ግንቦት_12

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ባሕረ ምስጢራት የሆነ የሰውን ፊት አይቶ የማያደላ "መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ" (በርሱ ዘንድ ንጉሥ፣ ሐብታም፣ ደሃ፣ ነዳይ እኩል ነውና)፣ አፈ በረከት፣ አፈ መዐር (ማር)፣ አፈ ሶከር (ስኳር)፣ አፈ አፈው (ሽቱ)፣ ልሳነ ወርቅ፣ የዓለም ሁሉ መምሕር፣ ርዕሰ ሊቃውንት፣ ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)፣ የሐዲስ ኪዳን ዳንኤል፣ ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)፣ ጥዑመ ቃል... እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እረፍቱ ነው።

ምልጃውና የከበረች ጸሎቱ ከእኛ ጋር ትሁን!






4.8K viewsedited  16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 18:19:48
3.3K views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ