"ትህትና" ✞ ትህትና መድኅን ነው ከሰይጣን አሽክላ ያድንሃል። / አባ እንጦንስ/ ✞ ትህትና የሰው ዘመድ ነው። / አባ አሞን / ✞ ትህትና የማይናድ ደልዳላ መሬት ነው። /አባ አርሳንዮስ / ✞ ትህትና ክርስቲያናዊ ምልክት ነው። /አባ መቃርስ/ ✞ ትህትና የሰው ሁሉ ጋሻ ጦር ነው። /አባ በሐይ/ ✞ ትህትና ግድግዳን የምታስጌጥ የአፈር ወይዘሮ ናት። /አባ አጋቶን/ ✞ ትህትና የመንግስተ ሰማያት መመላለሻ በር ነው። /አባ ሚልኪ/ ✞ ትህትና ሕፀጽን የሚያስታውቅ መስታወት ነው። /አባ ጰርዬ / ✞ ትህትና የነፍሳት ወደብ ነው። /አባ ዮሐንስ/ ✞ ትህትና የወንጌል ትእዘዝ መጀመሪያ ነው። /አባ ዮሐንስ ሐፂር/ ✞ ትህትና ወደ ንፁሐ ልቡና ሰገነት የሚወጡበት ነው ✞ ትህትና ዕፀ ሕይወት ናት።/አባ መቃርስ / 3.8K views05:26