Get Mystery Box with random crypto!

---------------------------- 'ቢፈልግባትም' በዘማሪ ቀሲስ ዳዊት ፋንታዬ ቢፈልግ | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

----------------------------
"ቢፈልግባትም" በዘማሪ ቀሲስ ዳዊት ፋንታዬ

ቢፈልግባትም መልካሙ ገበሬ
አልተገኘባትም ከበለስዋ ፍሬ፤
            
ለስልሶላት ነበር ሃይማኖት መሬቱ፤
ተቀጥሮላት ነበር አጥር ሥርዓቱ፤
ተነቅሎላት ነበር ድንጋይ ፈተናዋ፤
ፍሬ ግን ታጣባት በመጨረሻዋ፤
            
ፍሬ የሌለባት ቅጠል ስለኾነች፤
ተካይዋን በምግባር ስላላስደሰተች፤
መልካሙን ገበሬ ሊቆርጣት ተነሳ፤
ሌሎች እንዳይጠፉ በእርሷ የተነሳ፤
            
ለንስሐ የሚሆን እድሜ እንዲሰጣት፤
ጠባቂ መልአኳ ተማጸነላት፤
ምክር እና ተግሳጽ ይጨመርላት፤
ታፈራ እንደኾነ ለዓመት እንያት፤
              
ልመናውን ሰምቶ ጌታውም ፈቀደ፤
ጥቂት እድሜ ሊሰጥ ሊታገስ ወደደ፤
ዳግመኛ ሲመጣ ፍሬ ካላፈራች፤
ተቆርጣ ወደ ቶን እሳት ትጣላለች፤
----------------------------
ሉቃስ ፲፫ ÷ ፮
በዚህ ዓመት እንኳ ለማፍራት አስበን ይሆን!???
----------------------------


@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox