Get Mystery Box with random crypto!

* የቤተ ክርስቲያንን ክብር ለመጠበቅ ይቻል ዘንድ በአዲሱ ዘመን ነቅፈው ለነቃፊ ከሚያሰጡን ተ | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

* የቤተ ክርስቲያንን ክብር ለመጠበቅ ይቻል ዘንድ በአዲሱ ዘመን ነቅፈው ለነቃፊ ከሚያሰጡን ተግባራት ራሳችንን ማራቅ፤ ሃይማኖቱና ፖለቲካ ተቀላቅሎበት ግራ የተጋባ ካለም ለሃይማኖቱ ብቻ ግንባር ቀደም ጠበቃ በመሆን ሃይማኖቱንና ቤተክርስቲያንን ጠብቆ ማስጠበቅ የሚችልበትን ሥራ መስራት ይኖርበታል።

*አዲሱ ዓመት ከፖለቲካ ጋር ከተቀላቀሉ ጉዳዮች ርቀን፤ ሴራ፣አድማ፣ተንኮልና ምቀኝነትን የመሳሰሉ ተግባራት ሁሉ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ተጠርጎ ወጥቶ በምትኩ ሰላምና ፍቅር ነግሶ በአንድነት ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን እድገት የምንረባረብበት ጊዜ መሆን ይገባዋል።

*የአብነት ትምህርት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወሳኝ ምዕራፍ በመሆኑ የአብነት መምህራን በሥራ እጦት የሚንገላቱበት ጊዜ አብቅቶ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል የሚደረጉ ቅጥሮች ለአብነት መምህራን ቅድሚያ የሚሰጡ መሆን ይገባቸዋል።

*ሃይማኖትን ከፖለቲካ ፖለቲካን ከሃይማኖት
መቀላቀል አይቻልም።

*እኛ የቤተክርስቲያን ወታደሮች ነን፤

*ከዛሬ ጀምሮ በዘር በጎሣ በነገድ በክፋት በሴራ
ቤተክርስቲያንዋን ዝቅ ማድረግ አይቻልም።ቤተክርስቲያን ትናትም ዛሬም ታላቅ ናት ነገም ታላቅ ትሆናለች ፤

EOTCDPR

@Ethiopian_Orthodox