Get Mystery Box with random crypto!

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_orthodox — የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopian_orthodox — የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopian_orthodox
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 30.48K
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡
ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot
Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 38

2022-09-12 07:24:06 መስከረም ፪
ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ

መስከረም ሁለት በዚህች ቀን የካህኑ የዘካርያስ ልጅ የከበረ አጥማቂው ዮሐንስ ሕግን አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ ሰማዕት ሆነ።

ይህም እንዲህ ነው በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት ነቢዩ ዮሐንስ በገሠጸው ጊዜ ፊልጶስ ወንድሙ ስለሆነ ቅዱስ ዮሐንስም የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም ይለው ነበርና።

ቅዱስ ዮሐንስም ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሌላም ያደርገው ስለነበረ ክፉ ሥራ ሁሉ ይገሥጸው ነበር። ደግሞም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን ጨመረ። ስለዚህም ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው።

ሄሮድስም ዮሐንስን ይፈራው ነበር ጻድቅ ቅዱስ ሰው እንደሆነ ያውቅ ነበርና ብዙ ይጠባበቀውም ነበር። ሄሮድስ የተወለደባትን ቀን በዓል የሚያከብርባት ዕለት ነበረች መኳንንቱን አለቆቹን መሣፍንቱን ሹሞቹን በገሊላ አገር ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ግብር አገባ።

የሄሮድያዳ ልጅም ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው ከእርሱ ጋር በማዕድ የነበሩትንም ንጉሡም ያቺን ብላቴና የምትሺውን ለምኚኝ እሰጥሻለሁ አላት። እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ሊሰጣት ማለላት።

ወጥታም እናቷን ምን ልለምነው አለቻት እናቷም የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ አለቻት። ያን ጊዜም እየሮጠች ወደ ንጉሡ ገብታ የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን እንድትሰጠኝ እሻለሁ ብላ ለመነችው። ንጉሡም ስለ መሐላው አብረውት ስለ ነበሩትም ሰዎች አዘነ እምቢ ሊላት ግን አልወደደም።

ያን ጊዜም ባለወጎችን ላከ በእሥር ቤትም ሳለ የዮሐንስን ራስ ቆረጡ ራሱንም በወጭት አምጥተው ለዚያች ብላቴና ሰጡአት እርሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች። በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ከሄሮድያዳ ከእጆቿ ላይ ወደ አየር ስለ በረረች ታላቅ ድንጋፄ ሆነ።

ደግሞም ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም እያለች በመጮኽ ዘልፋዋለችና። ደቀ መዛሙርቱም በሰሙ ጊዜ መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት።

ስንክሳር

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
3.8K views04:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 23:03:33

"ወትባርክ፡አክሊለ፡ዓመተ፡ምሕረትከ፡ወይጸግቡ፡ጠላተ፡ገዳም"
             መዝ ፷፬÷፲፩    
 "በቸርነትህ ዓመታትን ታቀዳጃለህ  ምድረ በዳዎችም ጠልን ይጠግባሉ።"
            መዝ 64÷11         

እሰይ ደስ ደስ ይበላችሁ ደስ ደስ ይበላችሁ:
ቅዱስ ዮሐንስ መጣላችሁ ደስ ደስ ይበላችሁ።

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም አሸጋገራችሁ አሸጋገረን::                                  
 
          
መልካም አዲስ ዓመት!
       እንቁጣጣሽ                                         
         
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox                              
2.5K views20:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 07:27:34
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
3.2K views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 07:27:34 ይህች ቤተ ክርስቲያንም ከመሰረቷ አናወጻት፡፡ ያን ጊዜ ትልቁም ትንሹም ወንዱም፣ ሴቶችም፣ የተሾሙ ዲያቆናት፣ ካህናት፣ ሕዝቡም ሁሉ ደነገጡ ታወኩ፡፡ አሣ አንበሪው ግን መንቀሳቀሱን አልተወም፡፡ በመንቀሳቀሱም የቤተ ክርስያኗ ሕንፃ እኩሌታ ይሰነጠቅ ዘንድ ጀመረ፣ ምድርን ተናወፀች፣ ንጉስና፣ ሊቀ ጳጳሳቱም፣ ካህናቱም፣ ዲያቆናቱም፣ ህዝቡም፣ ሁሉም ካሉበት በባህሩ ወደብ ከተሰራች ከዚህች ቤተ ክርስቲያን መናወጥ የተነሳ ፍርሃት መንቀጥቀጥ በላያቸው ወረደ፡፡ ያ አንበሪ ግን በባህሩ ውስጥ ወደፊት መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗም በጀርባው ላይ ነበረች፡፡ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የሉትም ሁሉ ያ አሳ አንበሪ ወደ ባሕሩ ውስጥ ሊያሰጥመን ነው ሲሉ አሠቡ፡፡ ያን ጊዜም በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ስዕል ፊት በጽኑ አለቀሱ፡፡ በአንድ ቃልም "ገናናው የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ሆይ ርዳታህ ፈጥኖ ይደርስልን ዘንድ በቅድስት ቤተክርስቲያን ወደተሰበሰብን ወዳጆችህ ተመልከት" እያሉ ይጸልዩ ጀመር፡፡ ያንጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከሰማይ ወርዶ ያችን ቤተክርስቲያን በብሩሃት ክንፎቹ እንደደመና ጋረዳት፡፡ በእጁ በተያዘ የብርሃን በትረ መስቀሉ ያን ኣሣ አንበሪ ወገቶ "በኢየሱስ ክርስቶስ ሃይል ከቦታህ ሳትንቀሳቀስ እስከትውልድ ፍፃሜ ዘመን ለዘለአለም ትኖር ዘንድ አዝዝሃለሁ" አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ሊቀመላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያኗን ከነመዓዘኗ ከግርግዳዎቿ ከመሠዊያዋ በውስጧ ተተክለው ካሉት ሁሉ ጋር ከጀርባው ላይ እያለች ያንን አሳ አንበሪ ወግቶ በያዘበት ብርሃናዊ በትረ መስቀሉ ወደቀድሞው የባሕሩ ወደብ ጎተተው፡፡ ያንጊዜም ግንቡ ቦታውን ሳይለቅ እርስ በእርሱ ተጣበቀ፡፡

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ዓሣ አንበሪውን በቀድሞ ሥፍራው ያቺን ቤተክርስቲያን በቀደመ መሠረቷ ላይ አጽንቷቸዋልና፡፡ ሊቀመላእክት ቅዱስ ሩፋኤልም አዳኝ የሆነ የጌታው የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ጠርቶ ከሞት እንዳዳናቸው ሁሉም አስተዋሉ፡፡ በድንቅ ተዓምራቱ የዳኑ ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ በሊቀመላእክቱ ቅዱስ ሩፋኤል ላይ አድሮ ድንቅ ተዓምራቱን ስለገለጸላቸው የቅዱስ ሩፋኤልን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ የዚህች ቤተክርስቲያን ታሪክም በዓለም ሁሉ በየአውራጃዎቹም ተሰማ፡፡ የቅርብም የሩቅም ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው ታላቁ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል የለመኑትን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ የነገሩትን ያማልዳቸው ዘንድ በውስጧ ይጸልያሉ፡፡ በዚችም ቤተክርስትያን ብዙ ውስጥ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተደረጉ፡፡ ታኅሣሥ 13 ቀንም ተአምራቶቹ ከተፈጸመባቸው ዕለታት አንዷ ናት፡፡ ቅዳሴ ቤቱም በዚሁ ዕለት ተከናውኗል፡፡

በዚኽች ዕለት ታስበው የሚውሉት ቅዱሳን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል፣ የካህኑ መልከጼዴቅ፣ የአቡነ ሰራጵዮን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
3.1K views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 07:27:34 ጳጉሜ ፫
ቅዱስ ሩፋኤል


ሰማያውያን ከሆኑ ከመላአክት አለቆች ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል ቀጥሎ 3ተኛ ነው፡፡ "ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል፡፡ ጦቢት 12፡15፡፡ ሩፋኤል የሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል መልአከ የሰላምና የጤና መልአክ ይባላል፡፡ በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ሆነ ቁስል ይፈወስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” መጽሐፈ ሄኖክ 6፡3፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ “በበሽታ ሁሉ ላይ በሰው ልጆችም ቁስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡” በማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል፡፡ ሄኖክ 10፡13፡፡ ለሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ በማኅፀን ላለ ችግርና ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም፡፡ ሕፃኑ ዐርባ ቀን ሞልቶት በማሕፀን እያለ ማለትም በሥላሴ አርአያ መልኩ መሳል ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል አይለየውም፡፡ በመውለጃቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀላል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነት ያለን ረቂቅ ርኩስ መንፈስ ያውቃል፡፡ አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ጭን ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሠቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል ጦቢት 3፡8-17፡፡
ይኽም ጻድቅ ጦቢት በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ዕውነትና ቅን በሆነ ሕግ ጸንቶ የሚኖር ነው፡፡ ከወገኖቹ ጋራ ከመማረኩ በፊት ለችግረኞች ብዙ ምጽዋትን ይሰጥ ነበር፣ ብዙ ጊዜም የበጎቹን ጠጉርና ከእህሉም ዓሥራት በኩራቱን ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ይወጣ ነበር፡፡ ከገንዘቡም ከሦስት አንዱን ለድኆች ይሰጣል፡፡ በዚያን ጊዜም ሕዝቡ ሁሉም ክደው በዓልና ደማሊ ለሚባሉ ጣዖታት ይሰው ነበር፡፡
የቅዱስ ጦቢት ወገኖቹ ነነዌ በተማረኩ ጊዜ ሁሉም የአሕዛብን እህል በሉ እርሱ ግን ሰውነቱን ይጠብቅ ነበር፡፡ የአሕዛብንም መብል እንዳይበላ እግዚአብሔርን ያስበው ነበርና፡፡ በአንዲት ዕለትም በአደባባይ የወደቀ በድን አግኝተው ነገሩት፡፡ እርሱም እህል ሳይቀምስ ተነሥቶ ሔደ፡፡ ፀሐይም እስከሚገባ ወደ አንድ ቤት ውስጥ አስገብቶ አኖረውና ፀሐይ ሲገባ ቆፍሮ ቀበረው፡፡ በዚያችም ሌሊት እንደኃጢአተኛ ሆኖ በእድሞ ሥር ተኝቶ አደረ፡፡ በእድሞውም ላይ ወፎች መኖራቸውን ስላላወቀ ፊቱን ገልጦ ሳለ ወፎች እርኩሳቸውን ዐይኖቹ ላይ ጣሉበትና ዐይኖቹ ተቃጠሉ፡፡ ከዐይኖቹም ጢስ ወጣ፡፡ ታወሩም፡፡ ባለ መድኃኒትም ሊያድነው አልቻለም፡፡ መልአኩን ልኮ ነፍሱን እንዲወስዳት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ በዚያችም ዕለት የራጉኤል ልጅ የሣራ እና የጦቢት ጸሎታቸው ተሰማላቸው፡ ይህችም ሣራ አስማንድድዮስ የሚባል የሚባል ጋኔን በጭኗ አድሮ ሰባት ባሎቿን በየተራ የገደለባት ናት፡፡

ጦቢትም በገባኤል ዘንድ በአደራ ያስቀመጠውን ገንዘብ ያስመጣለት ዘንድ ልጁን ጦቢያን አሽከር እንዲፈልግ ነገረው፡፡ ጦቢያም ለአባቱ ታዥ ሆኖ አሽከር ሲፈልግም መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ስሙን አዛርያ ነኝ ብሎ በሰው አምሳል ተገለጠለትና ጦቢት አንድ ላይ ላካቸው፡፡ ጤግሮስ ወንዝ በደረሱ ጊዜ ጦብያ ሊታጠብ ባለ ጊዜ ታላቅ ዓሣ ሊውጠው ሲል መልአኩ ‹‹አትራው ያዘውና ጉበቱንና ልቡን አውጣ›› አለው፡፡ እንዳዘዘውም አደረገ፡፡ ጦቢያም ‹‹አንተ ወንድሜ አዛርያ ሆይ! ይህ የዓሣ ሐሞት፣ ጉበትና ልቡ ምን ይሠራል?›› አለው፡፡ አዛርያ ጠባለው ቅዱሱ ምአክም ‹‹ጉበቱና ልቡ ከደቀቀ ዕጣን ጋራ ቢያጤሱት ጋኔን ያደረበትን ጢሱ ያድነዋል፤ ሐሞቱም ዐይኖቹ የታወሩበትን ሰው ቢኩሉት የታወረ ዐይኖቹ ይበራሉ›› አለው፡፡
ዳግመኛም አዛርያ የራጉኤልን ልጅ ሣራን እንዲያገባት ነገረው፡፡ እንዳይፈራም አጽናናው፡፡ ወደ ራጉኤል ቤት በደረሱም ጊዜ ሣራ ተቀብላ ደስ አሰኘቻቸው፡፡ ጦቢያም ሣራን ወደዳትና እርሷን ይሰጠው ዘንድ አባቷን ጠየቀው፡፡ አበቷም ካሁን በፊት ለሰባት ባሎች ሰጥቷት ሰባቱም እንደሞቱ ቢነግረው ጦቢያም ‹‹የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን›› አለው፡፡ አባቷም ሣራን ሰጠውና ወደ ጫጉላ ቤት ባገቧቸው ጊዜ ጦቢያ አዛርያ የነገረውን አስታወሰ፡፡ የዓሣውን ጉበትና ልብ ከደቀቀ ዕጣን ጋራ ቢያጤሰው ጋኔኑ አስማንድድዮስ ሸሸ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤልም ይዞ ለዘለዓለም አሠረው፡፡ ከዚህም በኋላ ጦቢያ ሚስቱን ሣራን ወስዶ ወደ አባቱ ቤት ተመለሰ፡፡ የአባቱንም ዐይኖች በኳለ ጊዜ እንደ ጭጋግ ሆኖ ከዐይኖቹ ተገፈፈ፡፡እርሱም ዳነና ማየት ቻለ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤልም ራሱን ገለጠላቸውና ብዙ ምሥጢርን ከነገራቸው በኋላ ዐረገ፡፡

ከዚህም በኋላ ጦቢት ከወገኖቹ ጋራ ታላቅ የደስታ በዓል አደረገ፡፡ ስለ ጌታችንም መከራ ትንቢት ሲናገር ‹‹እርሱ በኋጢአታችን ይገርፈናል፣ ደግሞ እርሱ ይቅር ይለናል፣ ይፈውናልም፡፡ ሁለተኛም መከራህን የሚያስቡ የተመሰገኑ ናቸው፣ እነርሱ ክብርህን ባዩ ጊዜ በአንተ ደስ ይላቸዋልና›› አለ፡፡ ከዚህም በኋላ ጦቢት ብዙ ትንቢቶችን ተናገረ፡፡ ስለ ኢየሩሳሌም መታነጽና የእስራኤል ምርኮኞች ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመለሱ ትንቢትን ተናገረ፡፡ ልጁን ጦቢያንም ‹‹ልጄ ሆይ! ምጽዋት እንደምታድንና እንደምታጸድቅ ተመልከት›› አለው፡፡ ይህንንም ተናገሮ በአልጋው ላይ ሳለ በ158 ዘመኑ በሰላም ዐረፈ፡፡
ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው” ሄኖክ 3፡5-7፡፡ በዚህ መሠረት ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሄኖክ 2፡18፡፡ ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠብቃቸው እግዚአብሔር እንዳዘዘዉ የሚከፍታቸዉ የሚዘረጋቸዉ ይህ ታላቅ መልአክ ነዉ፡፡
የምህረትና የረድኤት መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከሥራዎቹ አንፃር በተለያየ ስም ይጠራል፡፡ "ፈታሄ ማህጸን" ይባላል-እናቶች ሲወልዱ ምጥ እንዳይበዛባቸዉ የሚራዳ መልአክ ስለሆነ አያሌ ክርስቲያኖች ማርገዛቸዉን ካወቁ ጀምሮ ድርሳኑን በማንበብ መልኩን በመድገም ጠበሉን በመጠጣት ሰዉነታቸዉን በመቀባት ይለምኑታል፡፡ እንደ እምነታቸዉ ጽናት ይደረገላቸዋል፡፡ ዳግመኛም "ዐቃቤ ኖኀቱ ለአምላክ" ይባላል-ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠበቅ ስለሆነ ነው፡፡ ዳግመኛም "መራሔ ፍኖት" ይባላል-ጦቢትን በቀና መንገድ መርቶታልና ነው፡፡ እንዲሁም "መላከ ክብካብ" ይባላል-ጦቢያና ሣራን ያጋባ ጋብቻቸዉን የባረከ በመሆኑ ነው፡፡

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ያደረገው ተዓምር ይህ ነው፡፡ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በዓል እስኪፈፀም ድረስ በከበረ ሊቀ ጳጳስ አባ ቴዎፍሎስ ዘመን በምድረ ግብጽ ውስጥ ከእስክንድርያ ውጭ በታናፀች አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን ከአሳ አንበሪ ላይ የታነፀች ነበር፡፡ ነገር ግን በወደቡ አጠገብ ከነበረ ግዙፍ አንበሪ ጀርባ ላይ መታነጿን ቀድሞ ያነጿት ሰዎች ቢሆኑ ከካህናትም ቢኾን ያወቀ አልነበረም፡፡
ያ አንበሪም የቤተክርስቲያኑ ህንጻ በከበደው ጊዜ ፈጽሞ ተንቀሳቀሰ፡፡ ከአሸዋማው መሬት ላይ በባህሩ ዳርቻ የታነፀች
2.6K views04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 08:38:57
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አቀባበል በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም፡፡

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
1.8K views05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 08:07:39
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
1.6K views05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 08:01:54 ጳጉሜ/ጳጉሜን

በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከነሐሴ በኋላ ጳጉሜን የምትባል አምስት ቀን አለች፡፡ ወር እንዳትባል አቅም ያንሳታል፡፡ ሳምንት እንዳትባል አምስት ቀን ብቻ ኾናለች፡፡ ጳጉሜን የሚለው ስያሜዋ ግን “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ መኾኑ በአበው ቃል ተነግሯል፡፡
“ኤፓጉሜኔ” ማለት ጭማሪ ማለት ነው ፡፡ በግእዝ ቋንቋችን ተውሳክ ማለት ነው፡፡ ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ኤውሮፓዎች ጳጉሜን የወር ተጨማሪ አድርገዋታል፡፡ ይኸውም ይታወቅ ዘንድ እኛ የወርን ቁጠር ሠላሳ ስናደርግ እነርሱ ሠላሳ አንድ ብለው የሚቆጥሩት ወር አላቸው፡፡ ይኹን እንጂ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ጳጉሜን የወር ተጨማሪ ሳያደርጉ የዓመት ተጨማሪ አድርገዋታል፡፡ የዓመቱንም ቀን ቁጥር ሦስት መቶ ስድሳ አምስት ቀን ቀነስኩ ብለው ደምረውታል፡፡

ጳጉሜ ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ዮሐንስ(በአቡሻክር/ህር ትምህርት ጳጉሜን ከመስከረም ቀድማ የተፈጠረች እንደሆነች ሊቃውንት ይናገራሉ ያንን በመያዝ በሉቃስ መጨረሻ የሆነችውን ለዮሐንስ መጀመሪያ አድርገው ጳጉሜን 6 በዮሐንስ ይላሉ) ጳጉሜ ስድስት ቀን ይሆናል፡፡ በዚህም ሐገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ / Thirteen months of sunshine / በመባል ትታወቃለች ፡፡ ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት /የገና ጾም/ ህዳር 14 ቀን ይገባና ታህሳስ 28 ቀን ጾሙ ተፈቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡

በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም ጾመ ዮዲት በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም /ጽጌ ጾም/ በብዙዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት እንዳልሆነች ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ዮዲ 2፡-2-7፡፡
እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ 12ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ 12ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋ በመድረሱ የእስራኤል ልጆች አለቀሱ፡፡ ዮዲት ባሏ ሞቶባት ከወንድ ርቃ ንጽሕናዋን ጠብቃ በጾም በቀኖና በሀዘን ተወስና ትኖራለች በተፈጠረው ጥፋት ህዝቡ ላይ ለመጣው መከራ ማቅ ለብሳ በራስዋ ላይ ትብያ ነስንሳ ወደ እግዚአብሔር አለቀሰች፡፡ የፍጥረቱን ጥፋት የማይሻ እግዚአብሔር አምላክም ሕዝቡን የሚያድኑበትን መንገድ ለመጠየቅ ሱባኤ በገባች በሦስተኛው ቀን ገለፀላት፡፡ ዮዲ 8፡-2 ፡፡ ከዚህ በኋላ ጠላታቸውን በዮዲት ምክንያት እስራኤላውያን እስከ ዮርዳኖስ እየተከተሉ አጥፍተዋቸዋል፡፡
ዮዲት ጠላቷን ለማጥፋት የቻለችው በጾምና በጸሎት ከእግዚአብሔር አምላክ ኃይል አግኝታ ነው፡፡ ስለዚህ ምዕመናን ጥንተ ጠላታችን ሰይጣንን ፈቃደ ሥጋን ለማሸነፍ በጾም ከፈጣሪያችን ኃይልን መጎናጸፍ አለብን ብለው ጳጉሜን በፈቃድ ይጾማሉ፡፡
የጳጉሜ ወር ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበትም ወር ነው፡፡ ይህም ጳጉሜ የዓመታት መሸጋገሪያ ጨለማው የክረምት ወቅት ወደ ማብቂያው የምናልፍባት እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ነውና ነው፡፡ ክርስቲያኖች ሁሉ በየዓመቱ በጳጉሜ ወር ሁሉም ተሰብስበው ከሌሊት ጀምረው በቤተክርስቲያን ተገኝተው ጸበል ይጠመቃሉ፡፡ ይህንን የምናደገውም እግዚአብሔር የተባረከ ዓመት እንዲሰጠን፣ ባሳለፍነው ዓመት የሰራነውን ኃጢአት ይቅር እንዲለን ነው፡፡ የምንጠመቀውም ንስሐ ገብተን ነው፡፡ በእግዚአብሔር ስም የተቀደሰው ጸበል ደግሞ ከበሽታችን ያድነናል፣ የተቀደስንም ያደርገናል፣ መጪውንም ህይወታችን የተባረከ ያደርግልናል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
መልካም የአዲስ ዓመት ዋዜማ (ጷጉሜ) ይሁንልን፡፡

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
1.9K viewsedited  05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 10:37:04 " ሰንበት ከሁሉ ዕለት ትበልጣለች ሰውም ከሁሉ ፍጥረት ይበልጣልና በታቦት(በመርከቡ) ውስጥ ከፍ ከፍ አደረጋት አብርሀምም በመሰሠዊያው አከበራት ሙሴ ደግሞ ሕዝበ እስራኤልን ሰንበትን በአንድነት ሆነው በእውነት እንዲያከብሯት አዘዛቸው።"
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ

መልካም ዕለተ ሰንበት!

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
951 viewsedited  07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:04:46 ለተክለሃይማኖት ጻድቅ መጠነ በዝኀ ህማሙ:
ትዌድሶ ደብረሊባኖስ ገዳሙ።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
1.0K viewsedited  10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ