Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበርን በማስመልከት መግለጫ ሰጡ | የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበርን በማስመልከት መግለጫ ሰጡ
***

ስከረም ፲፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም
""""""""""""""""""""""""""""""""
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
***

ፁዕ አቡነ አብርሃም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የ፳፻ ፲ወ፭ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል አከባበርን በማስመልከት ከመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ከአቢይ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን መግለጫ ሰጥተዋል።

መስቀል የሰላም ምልክትና አርማ መሆኑን በመግለጫቸው የጠቀሱት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ በዓላችንን ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቻችንን በሚገባ አጠናቀናል ብለዋል።

ቤተክርስቲያን የሰላምና የህግ ምንጭና ባለቤት ነች ያሉት ብፁዕነታቸው በዓላችንን በሰላም ለማክበር የምንችለው ወቅታዊውን የአገራችንን ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ከጸጥታ አካላት ጋር ተናበንና ተግባብተን መስራት ስንችል በመሆኑ በጋራ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

በበዓሉ ወቅት ህውከት ቀሰሰቃሽ መልዕክቶችን በቲሸረሰቶች ላይም ሆነ በባነሮች ላይ ይዞ መገኘት እንደማይፈቀድ የገለጹት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ የሚከተሉትን ዋና ዋና  ነጥቦች በመግለጽ መግለጫቸውን አጠቃለዋል።

ቤተክርስቲያን የህግና የሰላም ባለቤት እንደመሆኗ መጠን የመንግስትን ህጎችና መመሪያዎች ማክበርና ማስከበር የቤተክርስቲያን ተቀዳሚ ሥራዋ መሆኑን በመገንዘብ መንግስት በህገ መንግስቱ የደነገገውን የፌዴራል ሰንደቅ ዓላማ ወይም የቤተክርስቲያናችንን ዓርማ ብቻ በበዓሉና በዝግጅቶቻችን ላይ በመጠቀም ህግና ሥርዓት አክባሪነታችንን በተግባር  ማሳየት ይገባል። ከዚህ ውጪ የሆነ ምንም ዓይነት አርማም ሆነ ሰንደቅ አላማ መያዝ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

በቲሸርቶች፣በባነሮች እና በትርኢቶች ላይ ሁሉ ሌሎች ወገኖችን የሚያስከፉና ህውከት ቀስቃሽ የሆኑ ጥቅሶችን መጠቀም ከሥነ ምግባር ውጪ ከመሆኑም በላይ ለህውከትና ግርግር መፈጠር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

ወደ መስቀል አደባባይ በሚደረግ ጉዞ ሁሉ ተደጋጋሚ ፍተሻ የሚደረግ መሆኑን ማወቅና የሚደረገው ፍተሻም ለደህንነታችን ተብሎ የሚደረግ ፍተሻ መሆኑን በመገንዘብ መላው ህዝበ ክርሰቲያን ራሱን ለፍተሻ ዝግጁ ማድረግና ፍጹም በሆነ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ለፍተሻ መተባበር እንደሚገባው በመረዳት የጸጥታ አካላትን መተባበር እንዳለበት አሳስበዋል።

አጠራጣሪና ለጸጥታ ስጋት የሚሆኑ ነገሮች ሲያጋጥም በቦታው ለተመደቡ የሥነሥርዓትና የጸጥታ አስከባሪ አባላት ወይም ለፖሊስ አካላት በመጠቆም  ክርስቲያናዊ ኃላፊነታችንን መወጣት ይገባናል።

በቤተክርስቲያናችን ማዕከላዊ አሰሰተዳደርና በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ተዘጋጅቶ ከሚሰራጨው መጽሔትና ብሮሸር ውጪ ምንም ዓይነት የህትመት ውጤት ስለማይሰራጭ ከእነዚህ ውጪ የሆኑ የህትመት ውጤቶችንና በራሪ ወረቀቶችን ይዞ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነው።ይዞ የተገኘም በህግ ተጠያቂ ይሆናል።

ከመስቀል አደባባይ ውጪ በአድባራትና ገዳማት የሚከበሩ የመስቀል ደመራ በዓላትም በሰላማዊ መንገድ ተከብረው ማለፍ ይችሉ  ዘንድ ሁሉም ህዝበ ክርስቲያን ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር እና በመረዳዳት መሥራት እንደሚገባቸው  ተገንዝበው ህውከት ቀስቃሽ  ከሆኑ መልዕክቶች  በመታቀብ እና ህጋዊ ያልሆኑ ሰንደቅ ዓላማዎችን ባለመጠቀም ጭምር የበዓሉን ሰላማዊነትና የመስቀሉን ዓላማ መሰረት ያደረጉ  ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን የተላበሱ እንቅስቃሴዎች እንዲያደርጉ ብፁዕነታቸው አሳስበዋል።

በመጨረሻም ለመላው ኦርቶዶክሳዊያን በዓሉ የሰላም ፣የፍቅ፣የአንድነት፣የስምምነትና የደስታ በዓል እንዲሆን በመመኘት መግለጫቸውን አጠናቀዋል።

ኢኦተቤ-ሕ/ግ/መ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox