Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ቡና የሸገር አርማ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopia_buna — ኢትዮጵያ ቡና የሸገር አርማ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopia_buna — ኢትዮጵያ ቡና የሸገር አርማ
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopia_buna
ምድቦች: ንግድ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.43K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያ ቡና የሸገር አርማ
የፌስቡክ ፔጃችንን በተጨማሪ ላይክ በማድረግ መረጃ ይከታተሉን ።👇👇👇👇👇👇👇👇
https://m.facebook.com/ኢትዮጵያ-ቡና-የሸገር-አርማ-2185919471692903/?ref_component=mbasic_bookmark&ref_page=/wap/home.php&refid=8&ref=opera_speed_dial
#አስተያየት_ካሎት

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 40

2022-09-02 22:24:31
የ6ተኛ ሳምንት የPSL ጨዋታ

ተጠናቀቀ

ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ 2–1 ሰንዳውንስ
አቡኪ 90+3

ሰንዳውንስን ከሽንፈት ያላዳነች ብቸኛውን ጎል አቡኪ ባለቀ ሰዐት አስቆጥሯል!
3.5K views𝓔𝓼𝓶𝓲𝔃, 19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 22:15:08
ቃልን በተግባር .....

የኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊዎች የመጀመሪያውን ጨዋታ ስፖንሰር አደረጉ

የኢትዮጵያ ቡና እራሱን በገንዘብ ለመደገፍ የተለያዩ ዕቅዶችን ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ከነዚህ ዕቅዶቹ አንዱ በሆነው በ2015 ዓ.ም የሚያደርጋቸውን 30 ጨዋታዎች እያንዳንዱን ጨዋታ ለስፖንሰሮች ለመሸጥ  ጥሪ በማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊዎች ጥሪ በመቀበል በዓመታዊው ደብረታቦር በዓል 'ሆያ-ሆዬ' በመጨፈር ያገኙትን ብር የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ዲቻ የሚያደርጉትን ጨዋታ በ250,000 ብር በመግዛት አጋርነታቸውን ያሳዩበትን ቼክ ለኢትዮጵያ ቡና የደጋፊዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ለአቶ መንግስቱ ታደሰ በዛሬው ዕለተ አስረክበዋል።

አቶ መንግስቱ ለክለቡ ስራ አስኪያጅ ለአቶ ገዛኸኝ ወልዴ ቼኩን አስረክበው
በቀጣይም ሴት የቡና ደጋፊዎችም በመጪው አዲስ ዓመት በተመሳሳይ  ገንዘብ በማሰባሰብ አንዱን ጨዋታ ስፖንሰር ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

@Ethiopian_Buna @Ethiopian_Buna
3.6K views𝓔𝓼𝓶𝓲𝔃, 19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 22:56:10
ክለባችን መለያዎቹና ቀለማቱ!!

ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና በታሪኩ እነዚህን መለያዎች ተጠቅሟል ሲጠቀም ግን ከቡናው ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው ሌላው ጋር ሄደህ ለምን የክለብህ መለያ ይህ ለምን ሆነ ብትለው ምላሽ ላይሰጥህ ይችላል!!

እኛ ደግሞ የምናውቀውን ለታናናሾቻችን ለሌላውም ማስተላለፍ ይገባናል!

1. አረንጓዴ የቡናን ቅጠልና እርጥቡን ፍሬ ይወክላል!

2/ነጭ የቡናን አበባ ይወክላል!

3/ ቡኒው ቡና ተፈልቶ የሚሰጠውን ከለር ይወክላል!

4/ ቢጫው ቡናው ሲያፈራ በዕርጥብነቱ ያለውን መሸፈኛውን ይወክላል!

5/ ጥቁሩ ደግሞ ቡናው ሲቆላ የሚያወጣውን ከለር ይወክላል!

እንወቅ እንረዳ የምንለብሰው እውነትን ነው የምንለብሰው ሀገር ነው የኔ ያንተ ያንቺ የእርስዎ ኢትዮጵያ ቡና ከለሩ ስላማረ ብቻ አይደለም!

ኢትዮጲያ ቡና ለዘላላም ይኑር!

@Ethiopia_buna @Ethiopia_buna
2.4K views𝓔𝓼𝓶𝓲𝔃, 19:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:11:58 የሰንዳውንስ ደጋፊዎች ስለ አቡኪ ምን እያሉ ነው?

"አቡበከርን ስለሰጣችሁን ለመላው ኢትዮጵያውያን እናመሰግናለን " [Bernett Moneri]

"እባካችሁ አቡኪን ተጠባባቂ ማድረግ አቁሙ "

" አሁን በሰንዳውንስ ምርጡ ተጫዋች ናስር ነው። አፍሪካዊው ፔሌን ያገኘን ይመስለኛል። በጣም ነው የወደድኩት " [Aobakwe Sekgothe]

" እኛ በአቡበከው ውስጥ ኔይማርን እናያለን "

" እኛ የአቡበከርን ምርጥ ብቃት ማየታችንን ቀጥለናል። ልጁ ሱፐርስታር ነው "

" ሰንዳውንስ ምርጥ ዝውውር አድርጓል። አቡበከር ናስር ትልቅ ተጫዋች ነው "

" ናስር ከአፍሪካውያን ተጫዋቾች ምርጫዬ ሆኗል "

" ናስር የጎል አይን አለው ፣ በጣም ፈጣን ፣ በክህሎት የተሞላ ፣ እስኪ አስቡት እሱ ቋሚ ሆኖ ቢሰለፍ " [Tcashmine]

" ልጁ ከኢትዮጵያ ከመውጣቱ በፊትም ለሰዎች ስነግራቸው አላመኑኝም ነበር ፣ ልጁ በጣም ተሰጥኦ አለው "

" አቡበከር የተሟላ ተጫዋች ነው። የኳስ ጋር ያለው ምቾት ልዩ ነው "

" ፍጥነት እና ክህሎት ስላለው ተከላካዮችን በቀላሉ ያልፋል። በክንፍ በኩል አቡበከር አስፈላጊ ነው " [Mokgonyana]

" አቡኪ ከጉዳት ነፃ የኮነ ሲዝን እንድታሳልፍ እፀልያለው " [Saka Unako]

ጋናዊውም ትላንት አቡኪን ካየ በኋላም በክለቡ ማህበራዊ ገፅ አስተያየት መስጫ ላይ ይህን አለ " ናስርን ማየት በጣም ያስደስታል። የአፍሪካ ኔይማር ነው

አቡበከር ናስር በሶስት ጨዋታ ተቀይሮ ገብቶ በድምሩ 52 ደቂቃ ብቻ ተጫውቶ 2 ጎል አስቆጥሮ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎቹ የሰንዳውንስ ደጋፊዎች ውዴታቸውን እና አድናቆታቸውን እያጎረፉለት ይገኛል።

አቡኪ_ይሳካልህ_ቅመም
3.6K views𝓔𝓼𝓶𝓲𝔃, 17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 22:01:59
የአቡበከር ናስር ጎል . . . .
4.4K viewsSamuel Getaye, 19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:54:34
እንኳን ደስስስ አለንንንንንን!!!!

ጨዋታው ተጠናቀቀ

ሰንዳውንስ 2–0 ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ
አቡኪ 88‘

አቡኪም በዛሬው ጨዋታ በምርጥ እንቅስቃሴ ታጅቦ በጨዋታው አንድ ጎል ማስቆጠር ችሏል!
4.8K views𝓔𝓼𝓶𝓲𝔃, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 13:54:20
#የኢትዮጵያ_ቡና_ለኢትዮጵያ_ብሔራዊ_ቡድን_U_23_በተመረጡ_ተጫዋቾች_ዙሪያ_መልስ_ሰጠ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቁጥር 2/ኢ.እ.ፊ.አ.2/2948 በቀን ነሐሴ 18/2014 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ከ 23 ዓመት በታች የኢ/ብ/ቡድን በአፍሪካ ካኘ ኦፍኔሽን (AFCON) እንደሚሳተፍ ገልጾ ከክለባችን ስድስት ተጨዋቾች ጥሪ አድርጓል፡፡ ነገር ግን ክለባችን ለ 2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ ውድድር ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ ሲሆን ተጨዋቾችን በአሁኑ ሰዓት መልቀቅ በአጠቃላይ የቡድኑ ዝግጅት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር የጨዋታው ቀን ሲቀርብ በፊፋ መመሪያ መሰረት የተመረጡ ተጨዋቾችን እንደሚለቅ ገልፁዋል፡፡
6.9K views𝓔𝓼𝓶𝓲𝔃, 10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 11:26:20
#ስም ፦ አንተነህ ተፈራ
#ቀድሞ_የተጫወተበት_ክለብ፦
አዶላ ወዩ (2013)
ሻኪሶ ከነማ (2014)
#በውድድር_ዘመኑ_ያሳካቸው
የኢትዮጵያ ክልል ሻምፒዮና ፦ ሻምፒዮን(2014)፣ ኮከብ ተጫዋች እና ኮከብ ግብ አግቢ
የመላው ኦሮሚያ ሻምፒዮን ፦ ኮከብ ግብ አግቢ
#የሚጫወትበት_ቦታ፦ አጥቂ
#ቁመት፦ 1.78m
#ኪሎ፦ 62 kg
# ዕድሜ፦ 19
በኢትዮጵያ ቡና የሚቆየው፦ 3 ዓመት
እንኳን ወደ ታላቁ የኢትዮጵያ ቡና መጣህ
6.6K views𝓔𝓼𝓶𝓲𝔃, 08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 12:59:56
#ስም ፦ Kwaku Duah
# ዜግነት፦ ጋና
#ቀድሞ_የተጫወተበት_ክለብ፦
New Edubiase United FC (2015- 2017)
King Faisal Babies FC(2019-20)
Bibiani Gold Starts FC (2021-22)
#የሚጫወትበት_ቦታ፦ የመሐል ተከላካይ
#ቁመት፦ 1.80m
#ኪሎ፦ 70kg
# ዕድሜ፦ 24
በኢትዮጵያ ቡና የሚቆየው፦ 2 ዓመት
እንኳን ወደ ታላቁ የኢትዮጵያ ቡና መጣህ
5.4K viewsSamuel Getaye, 09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 22:29:42 ክለባችን ኢትዮጲያ ቡና የወዳጅነት ጨዋታ ዛሬ አድርጓል!

ሐዋሳ ላይ መቀመጫውን በማድረግ የቅድመ ውድድር ዝግጅትን በማድረግ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቡና ዋናው ቡድን ዛሬ ሐዋሳ አካባቢ ካለ ቡድን ጋር በሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ አከናውነው ሰፊ በሆነ የጎል ልዮነት አሸንፈዋል።

በቀጣይ ቀናት በይፋ ከሌሎች የሊጉ ክለቦች ጋር ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል!

መልካም የዝግጅት ጊዜ!
4.9K views𝓔𝓼𝓶𝓲𝔃, 19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ