Get Mystery Box with random crypto!

ቃልን በተግባር ..... የኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊዎች የመጀመሪያውን ጨዋታ ስፖንሰር አደረጉ | ኢትዮጵያ ቡና የሸገር አርማ

ቃልን በተግባር .....

የኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊዎች የመጀመሪያውን ጨዋታ ስፖንሰር አደረጉ

የኢትዮጵያ ቡና እራሱን በገንዘብ ለመደገፍ የተለያዩ ዕቅዶችን ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ከነዚህ ዕቅዶቹ አንዱ በሆነው በ2015 ዓ.ም የሚያደርጋቸውን 30 ጨዋታዎች እያንዳንዱን ጨዋታ ለስፖንሰሮች ለመሸጥ  ጥሪ በማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ቡና የልብ ደጋፊዎች ጥሪ በመቀበል በዓመታዊው ደብረታቦር በዓል 'ሆያ-ሆዬ' በመጨፈር ያገኙትን ብር የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ዲቻ የሚያደርጉትን ጨዋታ በ250,000 ብር በመግዛት አጋርነታቸውን ያሳዩበትን ቼክ ለኢትዮጵያ ቡና የደጋፊዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ለአቶ መንግስቱ ታደሰ በዛሬው ዕለተ አስረክበዋል።

አቶ መንግስቱ ለክለቡ ስራ አስኪያጅ ለአቶ ገዛኸኝ ወልዴ ቼኩን አስረክበው
በቀጣይም ሴት የቡና ደጋፊዎችም በመጪው አዲስ ዓመት በተመሳሳይ  ገንዘብ በማሰባሰብ አንዱን ጨዋታ ስፖንሰር ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

@Ethiopian_Buna @Ethiopian_Buna