Get Mystery Box with random crypto!

የሰንዳውንስ ደጋፊዎች ስለ አቡኪ ምን እያሉ ነው? 'አቡበከርን ስለሰጣችሁን ለመላው ኢትዮጵያውያ | ኢትዮጵያ ቡና የሸገር አርማ

የሰንዳውንስ ደጋፊዎች ስለ አቡኪ ምን እያሉ ነው?

"አቡበከርን ስለሰጣችሁን ለመላው ኢትዮጵያውያን እናመሰግናለን " [Bernett Moneri]

"እባካችሁ አቡኪን ተጠባባቂ ማድረግ አቁሙ "

" አሁን በሰንዳውንስ ምርጡ ተጫዋች ናስር ነው። አፍሪካዊው ፔሌን ያገኘን ይመስለኛል። በጣም ነው የወደድኩት " [Aobakwe Sekgothe]

" እኛ በአቡበከው ውስጥ ኔይማርን እናያለን "

" እኛ የአቡበከርን ምርጥ ብቃት ማየታችንን ቀጥለናል። ልጁ ሱፐርስታር ነው "

" ሰንዳውንስ ምርጥ ዝውውር አድርጓል። አቡበከር ናስር ትልቅ ተጫዋች ነው "

" ናስር ከአፍሪካውያን ተጫዋቾች ምርጫዬ ሆኗል "

" ናስር የጎል አይን አለው ፣ በጣም ፈጣን ፣ በክህሎት የተሞላ ፣ እስኪ አስቡት እሱ ቋሚ ሆኖ ቢሰለፍ " [Tcashmine]

" ልጁ ከኢትዮጵያ ከመውጣቱ በፊትም ለሰዎች ስነግራቸው አላመኑኝም ነበር ፣ ልጁ በጣም ተሰጥኦ አለው "

" አቡበከር የተሟላ ተጫዋች ነው። የኳስ ጋር ያለው ምቾት ልዩ ነው "

" ፍጥነት እና ክህሎት ስላለው ተከላካዮችን በቀላሉ ያልፋል። በክንፍ በኩል አቡበከር አስፈላጊ ነው " [Mokgonyana]

" አቡኪ ከጉዳት ነፃ የኮነ ሲዝን እንድታሳልፍ እፀልያለው " [Saka Unako]

ጋናዊውም ትላንት አቡኪን ካየ በኋላም በክለቡ ማህበራዊ ገፅ አስተያየት መስጫ ላይ ይህን አለ " ናስርን ማየት በጣም ያስደስታል። የአፍሪካ ኔይማር ነው

አቡበከር ናስር በሶስት ጨዋታ ተቀይሮ ገብቶ በድምሩ 52 ደቂቃ ብቻ ተጫውቶ 2 ጎል አስቆጥሮ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎቹ የሰንዳውንስ ደጋፊዎች ውዴታቸውን እና አድናቆታቸውን እያጎረፉለት ይገኛል።

አቡኪ_ይሳካልህ_ቅመም