Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ቡና የሸገር አርማ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopia_buna — ኢትዮጵያ ቡና የሸገር አርማ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopia_buna — ኢትዮጵያ ቡና የሸገር አርማ
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopia_buna
ምድቦች: ንግድ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.43K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያ ቡና የሸገር አርማ
የፌስቡክ ፔጃችንን በተጨማሪ ላይክ በማድረግ መረጃ ይከታተሉን ።👇👇👇👇👇👇👇👇
https://m.facebook.com/ኢትዮጵያ-ቡና-የሸገር-አርማ-2185919471692903/?ref_component=mbasic_bookmark&ref_page=/wap/home.php&refid=8&ref=opera_speed_dial
#አስተያየት_ካሎት

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 37

2022-09-29 19:29:55
በትላንትናው እለት በባህር ዳር የሚገኙ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ለተጫዋቾች ያረፉበት ሆቴል ድረስ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል አድርገዋል።

@ethiopia_buna
1.8K viewsSamuel Getaye, 16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 21:52:30
በአርቲስ ማዲጎ አፈወርቅ ህልፈተ ህይወት የተሰማን ጥልቅ ሀዘን በኢትዮጵያ ቡና የሸገር አርማ ድረገፅ እና በተከታዮቻችን ስም ስንገልፅ በልባዊ ጥልቅ ሀዘን ነው

ለቤተሰቦቹ ለስራ ባልደረቦቹ እና ለድናቂዎቹ መፅናናትን እንመኛለን

ነፍስ ይማር
2.0K viewsSamuel Getaye, 18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 20:17:00
#ገብተዋል
#ቡናማዎቹ የ2015 የቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ #የመጀመሪያው ዙር አምስት ሳምንታት ወደ ሚካሄዱበት #ባህር_ዳር ከተማ ገብተዋል።
#መልካም_የውድድር_አመት_ለኢትዮጵያ_ቡና
2.5K viewsSamuel Getaye, 17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 19:17:25
#የኢትዮጵያ_ቡና_ስፖርት_ክለብ_ተጫዋቾቹን_አበረታታ
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድሩን ለመጀመር
ነገ ወደ ውቢቱ ባህር ዳር ከተማ ጉዞውን ያደርጋል።

ይህንን በማስመልከት ዛሬ ለቡ በሚገኘው የተጫዋቾች የመኖሪያ ካንፕ የክለባችን የስራ አመርር ቦርድ አባላት እና የደጋፊዎች ማህበር አመራሮች በመገኘት አጋርነታቸውን አሳይተዋል።
"ዛሬ እዚህ የተገኘነው የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የፅ/ቤት ሰራተኞች፣ የደጋፊዎች ማህበር አመራሮች ፣ የክለባችን የክብር ስፖንሰሮት እና ደጋፊዎቻችን በአንድነት ከጎናችሁ መሆናችንን ለመግለፅ ነው። በዚህ የውድድር ዓመት በዕድሜም ይሁን በችሎታ የተሻለ ስብስብ ይዘናል። ከዚህ አንፃር እናንተ ከመጀመሪያው ጨዋታ ጀምሮ ሙሉ ትኩረታችሁን ጨዋታው ላይ አድርጉ። እኛም በሁሉም መልኩ ከጎናችሁ መሆናችንን እንገልፅላችኋለን።"
የመ/አለቃ ፈቃደ ማሞ
" እኛ አቅማችን በቻለው ሁሉ ሜዳ ላይ ያለንን ለመስጠት ዝግጁ ነን። ክለባችን እያደረገልን ባለው ነገር ሁሉ ደስተኞች ነን። በዚህ የውድድር ዓመት ከምንም በላይ ክለባችንን ሻምፒዮን ለማድረግ ጠንክረን እንሰራለን"
አማኑኤል ዮሐንስ
ነገ መስከረም 18/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉዟቸውን የሚያደርጉት ቡናማዎቹ መቀመጫቸውን አባይ ምንጭ ሎጅ በማድረግ ፤ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን መስከረም 22/2015 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ከወላይታ ዲቻ ጋር የመጀመሪያ የውድድር ዓመቱን ጨዋታ ያደርጋሉ።
መልካም የውድድር ጊዜ..... ድል እና ስኬት ለታላቁ የኢትዮጵያ ቡና
1.9K viewsSamuel Getaye, 16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 20:44:08
የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ

ጨዋታው ተጠናቀቀ

ኢትዮጲያ ቡና 1–0 ለገጣፎ ለገዳዲ
አብድልሀፊዝ (P)55‘
አበበ ቢቂላ ስታድየም (አአ)

ኢትዮጲያ ቡና የአዲስ አበበ ከተማ ዋንጫን 3ተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቋል!

@Ethiopia_Buna @Ethiopia_Buna
1.9K views𝓔𝓼𝓶𝓲𝔃, edited  17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 16:30:35 "ለኢትዮጵያ ቡና የፈረምኩት ራሴን በትልቅ ደረጃ ላይ ማየት ስለፈለግኩኝ ነው"

ሄኖክ ደልቢ /ኢትዮጵያ ቡና/

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮና ለኢትዮጵያ ቡና ለመጫወት በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ፊርማውን አኑሯል፤ ተወልዶ ያደገው በሐዋሳ ከተማ ውስጥ ነው፤ ሄኖክ ደልቢ ይባላል፤ በእዛም የውልደት እና የእድገት ቆይታው ለሐዋሳ ከተማ ክለብ ተጫውቶ ካሳለፈ በኋላ ነው ወደ ኢትዮጵያ ቡና ያመራው። ኢትዮጵያ ቡናን በመቀላቀሉ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው የሚናገረው የአማካይ ስፍራ ተጨዋቹ ከሊግ ስፖርት ጋዜጠኛው መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ጋር በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ ቆይታን አድርጓል።

ሄኖክ ለሊግ ስፖርት የሰጠው ቃለ-ምልልስም በሚከተለው መልኩም ቀርቧል፤ ተከታተሉት።

ሊግ፦ በቅድሚያ ለቃለ-ምልልሱ ፈቃደኛ ስለሆንክ ከልብ እናመሰግናለን?

ሄኖክ፦ እኔም የጋዜጣችሁ አምድ እንግዳ አድርጋችሁኝ ስለጋበዛችሁኝ ከልብ አመሰግናችኋለሁ።

ሊግ፦ በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ከሐዋሳ ከተማ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ዝውውርን አድርገሃል፤ የተሰማህ ስሜት ምን ይመስላል?

ሄኖክ፦ ኢትዮጵያ ቡና ትልቅ ቡድን ነው፤ በብዙዎቹ ዘንድም የሚወደድ ነው። ወደዚህ ቡድን በመምጣቴ የተሰማኝ ስሜት የተለየ ነው። ምክንያቱም ብዙ ደጋፊ ባለው ክለብ ውስጥ መጫወት መቻል መታደል ስለሆነና ከእዛም ባሻገር በኳሱም ራስህን አንድ ደረጃ ከፍ ወደምታደርግበት ቡድን ስትመጣና ብዙም ያላሳካካቸውን ድሎችንም ለማግኘት የምትመኘው ቡድንም ስለሆነ ወደ ቡና በመምጣቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ በሐዋሳ ከተማ ክለብ ውስጥ ነው ቆይታን ያደረግከው፤ በእስካሁኑ የቡድንህ ጉዞ ስኬታማ ነበርኩ ማለት ትችላለህ?

ሄኖክ፦ በፍፁም፤ ያም ሆኖ ግን እንደ አንድ ቤቱ ውስጥ ከስር እንዳደገ ተጨዋች ደግሞ ጉዞዬ በዋንጫ ድሎች ባይታጀብም ጥሩ ቆይታ ነበረኝ። ቆይታዬ ጥሩ ቢሆንም የሊጉን ዋንጫ ባለማንሳታችን ደግሞ በጣም ነው የሚቆጨኝ።

ሊግ፦ ለወጣት ቡድኑ ስትጫወት ደግሞ ቆይታህ በዋንጫ የታጀበ ነበር?

ሄኖክ፦ አዎን፤ ያኔ ጠንካራና ምርጥ ቡድን ነበረን። የእኛ ቡድን ደግሞ ወጣቶች ላይ ብዙ ጊዜም ነው ውጤታማም የሚሆነው።

ሊግ፦ ወደ ኢትዮጵያ ቡና የተዛወርክበት መንገድ ምን ይመስላል? ከሌሎች ክለቦችስ ጥያቄ አልቀረበልህም?

ሄኖክ፦ ቀርቦልኛል፤ ያም ሆኖ ግን ጥያቄን ካቀረቡልኝ ቡድኖች ውስጥ የእኔ ምርጫ የሀገሪቱ ትልቅ ክለብ የሆነው ኢትዮጵያ ቡና ነው። ኢትዮጵያ ቡና ሁሌም ልጫወትለት የምመኘው ቡድን ነው ከእዛም ውጪ የሚመጡብኝን ፈተናዎችንም በእዚሁ ክለብ ውስጥ መጋፈጥን ስለፈለግኩና ነገም ላይ ራሴን በትልቅ ደረጃ ላይ ማየትንሞ ስለፈለግኩኝም ነው በምንም ነገር ወደ ኋላ ሳልል ጥያቄያቸውን ተቀብዬ ልፈርምላቸው የቻልኩት።

ሊግ፦ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ከማምራትህ በፊት ስለ ክለቡ ምን አይነት እውቀቱና ግንዛቤው አለህ?

ሄኖክ፦ ብዙም ግንዛቤውና እውቀቱ ባይኖረኝም ክለቡ ከእኔ አጨዋወት ጋር ይሄዳል የሚለውን ነገር ግን በሚገባ ተመልክቼበታለሁ።

ሊግ፦ ኢትዮጵያ ቡናን በተቃራኒነት የተፋለምክባቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሉ?

ሄኖክ፦ አዎን፤ ከእነሱም ጋር ሆነ ከቅ/ጊዮርጊሶች ጋር ተቃራኒ ሆነህ ስትጫወት በኢትዮጵያ ውስጥ የምንገኝ አጠቃላይ ተጨዋቾች ሁለቱ ቡድኖች ብዙ ደጋፊዎች ያላቸው ስለሆኑና ትልቅም ቡድን ስለሆኑ ራሳችንን በደምብ ለማሳየትና ያለንንም አቅም አውጥተን ለመጫወት ወደ ሜዳም ስለምንገባም እኔም ቡናን በተቃራኒነት በገጠምንበት ጨዋታዎች ላይ ደስ ብሎኝና ጥሩም ሆኜ የተጫወትኩባቸው ጊዜያቶች ነበሩ።
1.4K viewsSamuel Getaye, 13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-25 16:30:31
1.4K viewsSamuel Getaye, 13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 18:27:48 አለቀ ተሸነፍን
3.1K viewsSamuel Getaye, 15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 18:25:38 ሳቱት
3.1K viewsSamuel Getaye, 15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ