Get Mystery Box with random crypto!

#የኢትዮጵያ_ቡና_ስፖርት_ክለብ_ተጫዋቾቹን_አበረታታ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የ2015 ዓ.ም | ኢትዮጵያ ቡና የሸገር አርማ

#የኢትዮጵያ_ቡና_ስፖርት_ክለብ_ተጫዋቾቹን_አበረታታ
የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድሩን ለመጀመር
ነገ ወደ ውቢቱ ባህር ዳር ከተማ ጉዞውን ያደርጋል።

ይህንን በማስመልከት ዛሬ ለቡ በሚገኘው የተጫዋቾች የመኖሪያ ካንፕ የክለባችን የስራ አመርር ቦርድ አባላት እና የደጋፊዎች ማህበር አመራሮች በመገኘት አጋርነታቸውን አሳይተዋል።
"ዛሬ እዚህ የተገኘነው የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የፅ/ቤት ሰራተኞች፣ የደጋፊዎች ማህበር አመራሮች ፣ የክለባችን የክብር ስፖንሰሮት እና ደጋፊዎቻችን በአንድነት ከጎናችሁ መሆናችንን ለመግለፅ ነው። በዚህ የውድድር ዓመት በዕድሜም ይሁን በችሎታ የተሻለ ስብስብ ይዘናል። ከዚህ አንፃር እናንተ ከመጀመሪያው ጨዋታ ጀምሮ ሙሉ ትኩረታችሁን ጨዋታው ላይ አድርጉ። እኛም በሁሉም መልኩ ከጎናችሁ መሆናችንን እንገልፅላችኋለን።"
የመ/አለቃ ፈቃደ ማሞ
" እኛ አቅማችን በቻለው ሁሉ ሜዳ ላይ ያለንን ለመስጠት ዝግጁ ነን። ክለባችን እያደረገልን ባለው ነገር ሁሉ ደስተኞች ነን። በዚህ የውድድር ዓመት ከምንም በላይ ክለባችንን ሻምፒዮን ለማድረግ ጠንክረን እንሰራለን"
አማኑኤል ዮሐንስ
ነገ መስከረም 18/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉዟቸውን የሚያደርጉት ቡናማዎቹ መቀመጫቸውን አባይ ምንጭ ሎጅ በማድረግ ፤ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን መስከረም 22/2015 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ከወላይታ ዲቻ ጋር የመጀመሪያ የውድድር ዓመቱን ጨዋታ ያደርጋሉ።
መልካም የውድድር ጊዜ..... ድል እና ስኬት ለታላቁ የኢትዮጵያ ቡና