2022-05-13 15:59:36
#MizanTepiUniversity
ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ የመጀመሪያ አመት አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ ዩኒቨርሲቲው መቀበል የሚጀምርበት ጊዜ ግንቦት 17 እና 18/2014 ዓ/ም መሆኑን እያስገነዘብን ተማሪዎቻችን ወደ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መንቀሳቀስ ከመጀመራችሁ በፊት ሪፖርት ማድረጊያና የመመዝገቢያ ቦታ እንደሚከተለው ይሆናል፡-
1ኛ. በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት መስክ ለተመደባችሁ ተማሪዎች - ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ፣
2ኛ. በማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስክ ለተመደባችሁ ተማሪዎች- ሚዛን- አማን ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ መሆኑን እየገለጽን ለምዝገባ ስትመጡ፡
- የ10ኛና 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪብት ኦሪጂናልና ሦስት ኮፒ፣
- የቅርብ ቀን ሦስት በአራት (3x4) የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ (ብዛት = 9)
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡
#ማሳሰቢያ፣ ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot
➹share &Join Us
@ethiopia_24 @ethiopia_24
@ethiopia_24 @ethiopia_24
910 views12:59