Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopia 24

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopia_24 — Ethiopia 24 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopia_24 — Ethiopia 24
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopia_24
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.87K
የሰርጥ መግለጫ

2015/ 2023 አስተያየት መስጫ @Ethnewbot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 17

2022-08-30 07:36:00
የአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት ይፋ ሆኗል!

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር ም/ቤት ነሀሴ 20/2014 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በ2014 ዓ.ም በተሰጠው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ክተመዘገበው ውጤት አንፃር ዝቅተኛው የማለፊያ መቁረጫ ነጥብ አማካይ ውጤት ለወንዶች 39% ለሴቶች 38% እና ለአካል ጉዳተኞች (ለዓይነስውራንና መስማት ለተሳናቸው ብቻ 37% እንዲሆን ተወስኗል፡፡

ስለዚህ በዘመኑ በተመዘገበው አማካይ ውጤት መሰረት ፐርሰንታይል ቀጥሎ በቀረበው ሠንጠረዥ አጠናቅረን የላክን ሲሆን ውጤቱ በሮስተርና በሰርተፊኬት ላይ ተመዝግቦ በአስቸኳይ ለተማሪዎች እንዲገለጽ እናሳስባለን ሲል የክልሉ መንግስት አሳውቋል። ( የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ )

( ዝርዝሩን ከፎቶው ይመልከቱ )

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
 
3.4K views04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 19:51:03
#Wollo_University

በ2015 ዓ.ም በወሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ በሁለተኛና በሶስተኛ ዲግሪ በመደበኛና በተከታታይ እና ርቀት ፕሮግራም መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች በሙሉ! በወሎ ዩኒቨርሲቲ በሁለተኛና በሶስተኛ ዲግሪ በግልና በመንግስት ስፖንሰርነት ከላይ በተዘረዘሩት ፕሮግራሞች በመደበኛና በተከታታይ እና ርቀት ፕሮግራም መማር የምትፈልጉ የምዝገባ ጊዜ ከ17/12/2014 -10/01/2015 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
4.9K views16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 19:32:13
በአማራ ክልል የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 23 - ጳጉሜ 04 ይካሄዳል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። በዚህም በ2015 የትምህርት ዘመን ከ6 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለመመዝገብ ቢሮው ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።

ከነሐሴ 23/2014 ዓ.ም እስከ ጷጉሜን 04/2014 ዓ.ም ድረስ ተማሪዎችን ለመመዝገብ መታቀዱን የጠቆሙት የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ጌታቸው ቢያዝን፤ በዚኽም 895 ሺህ 404 የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ገልጸዋል።

እድሜያቸው 7 ዓመት የሞላቸው ተማሪዎች 714 ሺህ 518 ተማሪዎች እንደሚመዘገቡም አስረድተዋል። በአጠቃላይ 745 ሺህ 708 የአንደኛ ክፍል ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊው አንስተዋል።

በአጠቃላይ 4 ሚሊዮን 144 ሺህ 845 ተማሪዎች በ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲኹም 1 ሚሊዮን 219 ሺህ 301 ተማሪዎች በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተያዘላቸው ጊዜ እንደሚመዘገቡ አቶ ጌታቸው ገልጸዋል።

ምዝገባው አዲስ ተማሪዎችን ብቻ ሳይኾን በተለያየ ጊዜ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎችን የሚያካትት እንደኾነ አቶ ጌታቸው አስረድተዋል። በ2014 ዓ.ም 5 ነጥብ 3 ሚሊዮን ተማሪዎች ተመዝግበው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋልም ነው የተባለው። (አሚኮ)

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
4.3K views16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 13:25:13 የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በቀጣይ አመት እንደሚጀምር ተገለፀ።

የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት የሙከራ ትግበራ  ከሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በተመረጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ  በ2015 ዓ.ም ይጀምራል።

ለዚህም ይረዳ ዘንድ የሙከራ ትግበራ ከሚካሄድባቸው ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ መምህራን ስርዓተ ትምህርቱን የማስተዋወቅ የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

አዲሱ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት በርካታ ደረጃዎችን አልፎ ለሙከራ ትግበራ የደረሰ መሆኑን የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ቴዎድሮስ ሸዋይርገጥ ገልፀዋል ።

በስርዓተ ትምህርት ዝግጅቱ ላይ የተመረጡ የመማር ማስተማር  የልህቀት ማዕከላት ዩኒቨርሲቲዎች እና ካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ በአማካሪነት እንደተሳተፉበት ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች ስርዓተ ትምህርት ዴስክ ኃላፊ  ዛፏ አብርሃ በበኩላቸው ይህ ሥርዓተ ትምህርት ሀገር በቀል እውቀትን፣ ግብረ ገብነትን ፣ ሳይንስና  ቴክኖሎጂን የተላበሰ እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል ።

በመሆኑም በዚህ የሙከራ ትግበራ ወቅት ከመምህራንና ከባለድርሻ አካላት ብዙ ግብዓቶች እንደሚሰበሰቡ ጠቅሰው ወላጆችና ሌሎችም አስተያየት እዲሰጡበት በድረ ገፅ ይለቀቃል ብለዋል።

በሙከራ ትግበራው ወቅት የሚመጡ አስተያየቶች ተካተው በ2016 ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባም በመድረኩ ተገልጿል ።

የሚሰጠው ስልጠናም መምህራን የመምህሩን መምሪያና የተማሪውን መጽሐፉ እዲተዋወቁ ይረዳቸዋል ተብሏል ። ( MoE )

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
4.7K views10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 08:48:50
የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የደቡብ ክልል እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑ ዛሬ ተገልጿል።

በሁለቱ ክልሎች ውሳኔ መሰረት የማለፊያ ነጥብ ፦

ለወንዶች 41፣
ለሴቶች 40 እና
ለአይነ ስውራን 39 ሆኖ ተወስኗል።

በዚህ መሰረት ፦ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁለቱም ክልሎች ለፈተና ከተቀመጡ ከ257 ሺህ በላይ ተማሪዎች 187 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል የሚያሳልፋቸውን ውጤት አምጥተዋል።

ለፈተና ከተቀመጠው አጠቃላይ ተማሪ ቁጥር ሲታይ ከ73 በመቶ በላይ ተማሪዎች አልፈዋል።

በተለየ መልኩ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በአሉታዊ ጫና ውስጥ ሆነው የተማሩና ለፈተና የተቀመጡ የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎችን ውጤት በተለየ መልኩ ታይቷታ።

በዚህም መሰረት ፦

ለወንዶች 39፣
ለሴቶች 38 እና
ለአይነ ስውራን 37 ሆኖ ተወስኗል።

የሁለቱ ክልሎች ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።

የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎች ግን ውጤታቸው በእጅ የሚሰራ በመሆኑ የ1 ሳምንት ጊዜ ዘግይቶ ይደርሳል እስከዛው በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት ተላልፏል። ( ENA , ኢዜአ )

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
5.0K viewsedited  05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 19:33:48
#ለጅማ_ዩንቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

የ2014 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በዩንቨርሲቲ እንዲሰጥ መወሰኑን ተከትሎ ሁሉም ተማሪ ከዶርም መዉጣት ስላለበት

1ኛ. እረፍት ላይ ያላችዉ ንብረታችሁን ዶርም አስቀምጣቹ የሄዳቹ ተማሪዎች እስከ ጳጉሜ 05/13/2014 ዓ.ም ድረስ እንድታወጡ፤

2ኛ. ትምህርት ላይ ያለቹ ተማሪዎች ከግቢ ስትወጡ ንብረታችሁን ይዛችዉ እንድትወጡ እያሰሰብን፤ በተጠቀሰው ቀን ዉስጥ ንብረቱን የማይወስድና ይዞ በማይወጣ ተማሪ ለሚፈጠረዉ ችግር የመኝታ ክፍሉ ተጠያቂ እንደማይሆን በጥብቅ እናሳስባለን ።
( ጅማ ዩኒቨርሲቲ , ATC )

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
5.1K views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 17:34:21 #ለአርባ_ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ትምህርት ዘመን በመደበኛ ፕሮግራም ለተመረቃችሁ ተማሪዎች በሙሉ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር ለተመረቁ ተማሪዎች ወንድ 3.5 እና ከዚያ በላይ፣ ሴት 3.25 እና ከዚያ በላይ ውጤት ላስመዘገቡ በ2015 የትምህርት ዘመን ነፃ የ2ኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል ለ18 ተማሪዎች (AMIT 2፣ AWTI 2፣ CBE 2, CSSH 2, CMHS 2, CAS 2, CNS 2, School of Law 1, school of PBS 1, Sawula campus 2)  አወዳደሮ ለመስጠት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን የሚትፈልጉ የ2014 ተመራቂ ተማሪዎች ( መስከረም 29/30 እና ሰኔ 25/26 2014 ዓ.ም የተመረቃችሁ) ከነሐሴ 18-27/2014 ዓ/ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት እንድትመዘገቡ እየገለጽን፡-

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎች፡-
1. ሙሉ የትምህርት መረጃ ኦርጅናልና ሁለት(2) ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ሁለት(2) ጉርድ ፎቶግራፍ
2.  የድጋፍ ደብዳቤ /Recommendation Letter/
3.  በተለያዩ የተማሪ አደረጃጀቶች አገልግሎት የተሰጠበት የምስክር ወረቀት
4. የማመልከቻ ቦታ፡- የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት የተማሪዎች
    ምዝገባና ቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210፣ 211
5.  ለፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽበት
     ከጳጌሜ1-3/2014 ዓ.ም

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፡- መስከረም 5/2015 ዓ.ም፤

ፈተና የሚሰጥበት ቦታ፡-
1. የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂና የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች፣ የማኅበራዊ ሳይንስ፣ የቢዝነስና 
     ኢኮኖሚክስ፣ የሕግ እና የሥነ-ትምህርትና ሥነ-ባህሪ ተማሪዎች - ዋናው ግቢ
2. የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች - ነጭ ሳር ካምፓስ
3. የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች - ዓባያ ካምፓስ
4. የግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች - ኩልፎ ካምፓስ
5. የሳውላ ካምፓስ ተማሪዎች - በሳዉላ ካምፓስ

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
5.2K views14:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 14:06:47
#Gambella_University ማስታወቂያ
ለድህረ-ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በመደበኛው መርኀ-ግብር ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች ፍላጎት ያላቸው አዲስ አመልካቾችን ተቀብሎ በሁለተኛ ዲግሪ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴርን የመግቢያ መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች በሙሉ ከነሐሴ 23/2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 06/2015 ዓ.ም ድረስ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም https://portal.gmu.edu.et ላይ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

የምዝገባ ቦታ፡- በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ጽ/ቤት ወይም ‘Online’ https://portal.gmu.edu.et
የምዝገባ ጊዜ፡- ከነሐሴ 23/2014 ዓ.ም እስከ መስከረም 13/2015 ዓ.ም
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፡- መስረም 20/2015 ዓ.ም *ዝርዝር መረጃው ከላይ ተያይዟል

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
4.7K views11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 13:42:43
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዝግጅት ከደህንነት ስጋት ነፃ እንዲሆን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የፈተናው ቅድመ ዝግጅት ሥራ በመጠናቅ ላይ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ለፈተና አሰጣጡ ውጤታማነት ከመፈተኛ ቦታ መረጣ ጀምሮ የፈተና ኮዶችን ብዛት ከፍ የማድረግ ሥራ መከናወኑን ገልጸዋል።

ይህንንም ተከትሎ ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ የራሳቸው ጥረት ውጤት ለማግኘት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የተሳሳቱ መረጃዎችን የሚለቁ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያሳሰቡት ዋና ዳይሬክተሩ፤ እነዚህን አካላት በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
4.2K viewsedited  10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 13:38:36
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ፕሬዝዳንት አወዳድሮ ለመቅጠር የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል።

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ ተቋሙን ለሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የሚመራ ኃላፊ ለማወዳደር ፍላጎቱን አሳውቋል፡፡

አመልካቾች የትምህርት ደረጃቸው ሁለተኛ ዲግሪ ከረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ጋር እና ከዚያ በላይ መሆን እንዳለበት ተገልጿል።

አመልካቾች በቀጣይ የተዘረዘሩ ማስረጃዎችን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፦

• Curriculum Vitae (CV)

• የትምህርት ደረጃን የሚገልጽ ሰርተፊኬት

• የአካዳሚክ ማዕረግ የሚገልጽ ደብዳቤ

• በዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ወይም በምርምር ተቋም በተመራማሪነት ያገለገሉበትን ጊዜ የሚገልጽ ደብዳቤ

• በዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉበትን የሚገልጽ ደብዳቤ

• በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትነት ቢመደቡ የዘርፉን ሥራ ውጤታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂክ ዕቅድ

አመልካቾች ከነሐሴ 23 እስከ ጳጉሜ 4/2014 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት በዋናው ግቢ አስተዳደር ሕንጻ በቢሮ ቁጥር 209 በአካል ቀመቅረብ ወይም በኢ-ሜይል አድራሻ amu2022pcc@gmail.com መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ዳምጠው ዳርዛ (ዶ/ር) ላለፉት ዓመታት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመሆን ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል።

SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24

አስተያየት ለመስጠት @Ethnewbot

➹share &Join Us
                  
@ethiopia_24     @ethiopia_24
@ethiopia_24     @ethiopia_24
3.9K views10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ