Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Matric

የሰርጥ አድራሻ: @ethiomatric
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 33.87K
የሰርጥ መግለጫ

Ethio Matric ለ12ኛ ክፍል ኢንትራንስ ፈተና የሚያዘጋጅ የሞባይል አፕሊኬሽን ነው። አፕሊኬሽኑን ከዚህ ሊንክ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric ዳውንሎድ አድርጋቹ መጠቀም ትችላላቹ
ከአፕሊኬሽኑ ጋር ለተያያዘ ጥያቄ
@ethiomatric_support

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-10-25 20:07:14
"ከሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት ይገለጻል።"

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)


የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አሰጣጥን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ሰጥቷል።

948 ሺህ 322 ተማሪዎች ተመዝግበው ከ937 ሺህ በላይ ወይም 98 በመቶ ፈተናውን መውሰዳቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች ፈተናውን ያልወሰዱና በተለያዩ አደጋዎች ፈተና ላይ ያልተቀመጡ እንዲሁም በወሊድ ምክንያት ፈተናውን ያልወሰዱ ተማሪዎች ከአንድ ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ፈተና እንደሚወስዱ ገልጸዋል።

በአራት ዩኒቨርሲቲዎች ከ12 ሺህ በላይ ፈተናውን አንፈተንም ያሉ ተማሪዎች በመደበኛው የፈተና አሰጣጥ በሚቀጥለው ዓመት ፈተና መውስድ #እንደማይችሉ የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ነገር ግን #በግል መፈተን ይችላሉ ብለዋል።

የ12ኛ ክፍል ውጤት ከሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ እንደሚገለጽ ተናግረዋል።

@tikvahuniversity
5.6K views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 15:40:35 ለ12ኛ ክፍል ናቹራል ተማሪዎች ተቃሚ ምክሮች :

1. ብር ፡ መጠነኛ ብር ይዛቹ ሂዱ፡፡ ግቢ ያሉት ነጋዴዎች አነስተኛ ስለሆኑ አንዳንድ ነገራቶች ላይ ሊያስወድዱ ይችላሉ፡፡ መሰረቅም ሊኖር ስለሚችል በጣምም አታብዙ፡፡
2. ምግብ ፡ ምግብ ብትይዙ ሃሪፍ ነው፡፡ በሶ / የሎዝ ኦቾሎኒ / ማርመለታ (በፕላስቲክ ብታደርጉት የተሻለ ነው ፤ በጠርሙስ አንዳንድ ፈታሾች ሊከለክሉ ይችላሉ) / ኩኪስ / ብስኩት ከቻላቹ ብትይዙ ጥሩ ነው፡፡
3. ሰልፍ/ወረፋ ፡ ለብዙ ነገር ወረፋ አለ፡ ገና ባስ ውስጥ ወረፋ አለ ከዛ ዩኒቨርስቲ ለመግባት ስትፈተሹ ረጅም ሰልፍ አለ ፤ በመቀጠል የዩኒቨርሲቲው ካፌ እና ከፍላቹ የምትበሉት ቦታ እራሱ ብዙ መጠበቅ ያስፈልጋችኋል፡፡
4. ዶርም ፡ ዶርም የምትመደቡት ከክፍላቹ ተማሪዎች ጋር ነው ግን አንዳንዴ ከሌሎች ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጋር ልትቀላቀሉ ትችላላቹ፡፡ ሌላ ደግሞ የፍራሽ እጠረት ስለሚኖር በሁለት ፍራሽ ላይ ሶስት ተማሪ ሊተኛ ይችላል፡፡
5. የፈተና ኮድ ፡ በሚዲያ የፈተና 12 ኮድ ነው ቢባልም ፤ ለሶሻሎች 6 ኮድ ነው የነበረው
9.8K viewsedited  12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 21:44:51 የ12ኛ ክፍል የ2014 ዓ.ም የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ተጠናቋል
--------------------

በመጀመሪያው ዙር ከ586 ሺህ በላይ ተማሪዎች በ133 ማዕከላት ተፈትነዋል።

ፈተናው በተጀመረበት ወቅት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የደረሰው አደጋ እና በአማራ ክልል በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህርዳር እና ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ስርዓቱ ባፈነገጠ ሁኔታ አንፈተንም በማለት 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ግቢውን ለቀው መውጣታቸውን አስታውቋል።

በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በደረሰው ክስተትም የመጀመሪያው ቀን ተፈታኞች ያልተፈተኑ መሆኑንና ያልተፈተኗቸውን ፈተናዎች በቀጣይ ዙር እንደሚፈተኑ ነገር ግን በአንድ አንድ ዩኒቨርስቲዎች ፈተናውን ጥለው የወጡ ተማሪዎች ከፈተና ውጪ መሆናቸውንና ዳግም የማይፈተኑ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ከሌሎቹ በተለየ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ሃይል በተቀላቀለበት መልኩ በደረሰ ግርግር የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ በፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት ደርሷል።

ሚኒስቴሩ የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን ላደረጉ አካላትም ምስጋናውን አቅርቧል።

Via Ministry of Education
10.3K views18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 14:36:59
#Update

የሲዳማ ክልል ሠላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ጥዋት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፤ በዋናው ግቢ እና በቴክኖ ግቢ መካከል ያለው የተማሪዎች መሸጋገሪያ ድልድልይ #በመደርመሱ የደረሰውን ድንገተኛ አደጋ በተመለከተ አሁናዊ ሁኔታ ላይ ለደ/ሬ/ቴ/ድ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እንደ ኃላፊው ማብራሪያ ፦

- አራት መቶ አስራ አምስት (415) ተማሪዎች በድልድዩ ላይ ሆነው ድልድዩ ተደርምሷል።

- የአንድ ተማሪ ህይወት በአደጋው አልፏል።

- በድልድዩ መደርመስ አደጋ ከደረሰባቸው መካከል 310 ተማሪዎች ቀላልና 110 ተማሪዎች ላይ መካከለኛና ከባድ ጉዳት ደርሷል። 20 ተማሪዎች የአጥንት ስብራት ያጋጠማቸው ሲሆን 85 በሚሆኑት ላይ ቀላል አካላዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- ተጎጂዎች  በሪፌራል፣ ያኔት፣ አዳሬ እና ሞቲቴ ፉራ ሆስፒታሎች ህክምና እየተሰጣቸው ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል ፤ የሲዳማ ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ተማሪዎች ተረጋግተው ወደ ግቢው እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ፈተናውን አስመልክቶ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን መመሪያ እንዲከታተሉ አሳስቧል።

የተማሪ ወላጆችም ተማሪዎችን በማረጋጋት ሂደት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን የክልሉ መንግስት በጸጥታው ረገድ የሚጠበቅበትን ሁሉ እየተወጣ መሆኑን አስታውቋል።

በተጨማሪ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ የተመደቡ ተማሪዎች በጥዋቱ አደጋ ምክንያት ለዛሬ የታቀዱትን ፈተናዎች መፈተን እንዳልቻሉ ገልጾ ፤ በሁኔታው ተደናግጠው ከግቢ የወጡም ሆኑ ግቢ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ተረጋግተው ወደነበሩበት እንዲመለሱና ለነገ ፈተና እንዲዘጋጁ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
413 views11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 10:54:34
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች መሰጠት ተጀምሯል
1.5K views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 09:45:45
ዛሬ ጠዋት መስከረም 30/2015 ዓም በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዉን ሁለት ካምፓሶች የሚያገናኝ ድልድይ በመፍረሱ ምክንያት ድልድዩን ሲሻገሩ በነበሩ የተወሰኑ ተማሪዎች ላይ በደረሰዉ ጉዳት እናዝናለን፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ ይገኛል፡፡ ሁኔታቸዉንም መላዉ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ እና የትምህርት ሚኒስቴር ግብረሀይል በቅርበት እየተከታተለ በመሆኑ ወላጆች እንዳይደናገጡ እንጠይቃለን፡፡

ጉዳት የደረሰባቸዉ ተማሪዎች በቀጣይ በሚሰጠዉ ፈተና የሚፈተኑ መሆኑን እየገለጽን ሌሎች ተማሪዎች በአጋጣሚዉ ሳይረበሹ ተረጋግተዉ እንዲፈተኑ እናሳስባለን፡፡

ሁኔታዉን በሚመለከት ዝርዝር መረጃዎችን በቀጣይ የምናሳዉቃችሁ ይሆናል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር!
1.8K views06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 21:43:26 ማሳሳቢያ፡-
ተፈታኞቻችን ወደ መፈተኛ ማዕከላት ገብተዋል፡፡ የተከለከሉ ነገሮችን ማንም ተፈታኝ ይዞ እንዳይገባ ከወረዳ ጀምሮ ገለጻ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም አካላዊ ፍተሻ ተደረጓል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተለያየ የማጭበርበሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም የተከለከሉ ነገሮችን በተለይም ተንቀሳቃሽ ስልክን ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ይዘው የተገኙ ተፈታኞች በህግ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ፡፡ ድርጊቱ ከፍተኛ የፈተና ደንብ ጥሰት በመሆኑ ውሳኔው ከሁሉም ፈተና የሚሰረዙ ይሆናል፡፡
በተመሳሳይ ከዚህ በኃላም የተከለከሉ ነገሮችን መፈተኛ ማዕከላት (የኒቨርሲቲ) ግቢ ውስጥ ማንኛውም ተፈታኝ ይዞ ቢገኝ ከሁሉም ፈተና የሚሰረዝ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ገለጻውን ባለመቀበልና አካላዊ ፍተሻዎችን በማጭበርበር ስለፈጸመው ጉዳይ ተጨማሪ ህጋዊ ምርመራ የሚካሄድ ሲሆን እንደግኝቱም ተመጣጣኝ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል፡፡

ፈተና የሁሉም ማህበረሰብ ሀብት በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለፈተና ደህንነትና ፍትኃዊነት የበኩሉን አዎንታዊ ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፌስቡክ ፔጅ የተወሰደ
939 viewsedited  18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 14:48:55
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች(የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች) ከዛሬ ጀምሮ ፈተናውን ወደ ሚወስዱበት ዩኒቨርስቲ እየገቡ ይገኛሉ።

የሰመራ፣ጎንደር፣ ዋቸሞ፣ቦንጋ እና ደብረታቦር ዩኒቨርስቲዎች በከፊል
393 views11:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 10:32:22 ውድ የኢትዮማትሪክ ተጠቃሚዎች ትናንት ከሌሊት 5፡30 ጀምሮ እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሲስተም ችግር ምክንያት ለአዲስ ተጠቃሚዎች ፤ SIGN IN እና DOWNLOAD ለሚያደርጉ እየሰራ አይደለም ፤ በትንሽ ደቂቃ ውስጥ የምናስተካክለው ይሆናል፡፡ አብዛኞቻቹ ዳውንሎድ አድርጋጁ የምትጠቀሙ ስለሆነ እንደበፊቱ መስራቱን የሚቀጥል ይሆናልን ያለምንም ችግር ፤ ይሄ እናንተን አያጠቃልልም፡፡
1.2K views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 09:20:38 ውድ የኢትዮማትሪክ ተጠቃሚዎች ትናንት ከሌሊት 5፡30 ጀምሮ እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሲስተም ችግር ምክንያት ለአዲስ ተጠቃሚዎችSIGN IN እና DOWNLOAD ለሚያደርጉ እየሰራ አይደለም ፤ በትንሽ ደቂቃ ውስጥ የምናስተካክለው ይሆናል፡፡

አብዛኞቻቹ ዳውንሎድ አድርጋጁ የምትጠቀሙ ስለሆነ እንደበፊቱ መስራቱን የሚቀጥል ይሆናልን ያለምንም ችግር ፤ ይሄ እናንተን አያጠቃልልም፡፡
1.5K viewsedited  06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ