Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Matric

የሰርጥ አድራሻ: @ethiomatric
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 33.87K
የሰርጥ መግለጫ

Ethio Matric ለ12ኛ ክፍል ኢንትራንስ ፈተና የሚያዘጋጅ የሞባይል አፕሊኬሽን ነው። አፕሊኬሽኑን ከዚህ ሊንክ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric ዳውንሎድ አድርጋቹ መጠቀም ትችላላቹ
ከአፕሊኬሽኑ ጋር ለተያያዘ ጥያቄ
@ethiomatric_support

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-04-16 10:46:13
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ፤ እንኳን ለብርሀነ ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳቹ
1.5K viewsedited  07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 20:49:48 Ethio Matric አፕሊኬሽን ላይ ያስቸገራቹ ነገር ወይም ከአፕሊኬሽኑ ጋር ተያይዞ ማንኛውም ጥያቄ ካላቹ
t.me/ethiomatric_support2 ላይ መጠየቅ ትችላላቹ፡፡
1.5K views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 21:17:45 ኢትዮ ማትሪክ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለኢንትራንስ ፈተና ጥሩ ዝግጅት ለማድረግ የሚረዳ አፕሊኬሽን ነው፡፡ አፕሊኬሽኑ አነስተኛ ክፍያ ያለው ቢሆንም ክፍያው ለአንዳንድ ተማሪዎች ሊያስቸግር እንደሚችል እንረዳለን። እነዚን ተማሪዎች ለመደገፍ ስልካቸው ከ1.5GB RAM እና ከዛ በታች ለሆነ ቢያንስ ለአንድ ዓመት ካለክፍያ የምናካትት ይሆናል።

ስልካቹ ከ1.5GB RAM እና ከዚያ በታች ከሆነ ከዛሬ(ቅዳሜ) ጀምሮ እስከ ማክሰኞ ባለው ጊዜ ከታች ባለው አጻጻፍ(format) @ethiomatric_support2 ላይ በነጻነት ይላኩልን፡

"በቅርቡ ቴሌግራም ቻናላቹ ላይ የተጻፈውን መስፈርት አሟላለሁ ፣ አፕሊኬሽኑ ላይ SIGNUP ያደረኩበት ስልክ ቁጥር _____________ ይሄ ነው "

ይበሉን ፤ ከዛ እኛ አይተን ከላይ የጻፍነውን የሚያሟሉ ከሆነ ትምህርቶቹን ካለክፍያ የምናካትት ይሆናል፡፡ እባክዎን ብዙ የስልክ ጥሪ እየደረሰን ስለሆነ ፤ ይሄን የምናስተናግደው ከላይ ባለው የቴሌግራም አካውንት ላይ ብቻ ነው። እናመሰግናለን
2.5K viewsedited  18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 18:33:54 ውድ የኢትዮ ማትሪክ ተጠቃሚዎች

በአሁኑ ጊዜ ብዙ የስልክ ጥሪዎች እየደረሱን ነው። በአብዛኛዎቹ በስልክ የምንጠየው ጥያቄዎች አፕሊኬሽኑ ፊት ለፊት በማየት ብቻ በቀላሉ ምላሽ ማግኘት የሚቻሉ ናቸው፡፡ ከዚህ ካለፈ ደግሞ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች (Frequently Asked Questions) በማየት መልስ ማግኘት የሚቻሉ ናቸው። ስለዚህ እኛን በስልክ ከማጠየቆ በፊት እራሳቹ ምላሽ ወይም መፍትሄ ለማግኘት እንዲሞክሩ በትህትና እንጠይቃለን።

መፍትሄ ማግኘት በማይችሉበት ጊዜ ብቻ በስልክ ቢደወሉ እንመርጣለን። ከፍተኛ የስልክ ጥሪዎች መቀበላችንን ከቀጠልን የምናስከፍለውን ክፍያ ለመጨመር ወይም ለስልክ ጥሪዎች ምላሽ መስጠትን ልናቆም እንችላለን።
1.3K views15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 20:21:49
#Update #UAE

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ሙሉ ስኮላርሺፕ መስጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መናገራቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወስደው ከግማሽ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች ውስጥ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 273 ተማሪዎች እውቅና በሰጡበት ወቅት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተማሪዎቹ " እንኳን ደስ ያላችሁ " ካሉ በኋላ የተሰጣቸውን ፈተና በአግባቡ መስራት በመቻላቸው " ኢትዮጵያን የሚያግዙ 273 ተማሪዎች ተገኝተዋል በዚህም ደስታ ይሰማናል" ብለዋል፡፡

ተማሪዎቹ እጅግ ዘመናዊ በሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉና ለኢትዮጵያ እና አፍሪካ የሚደርሱ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተማሪዎቹ በርትተው ተምረው ሀገራቸውን ሳይረሱ የሚጠቅሙ እንዲሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

ዶ/ር ዐቢይ ሁሉም ተማሪ ጥበብን እንዲሻ እና ሀገሩን ለመለወጥ እንዲሰራ ጠይቀዋል፤ በተለይ " ለእውነት የቆመ ተማሪ ነገ ሃገሩን ይለውጣል፤ እናንተ የላቀ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎችም እውነትን የምትሹ መሆን አለባችሁ እንደዛ ሲሆን ደግሞ ሀገርን የምትገነቡ ትሆናላችሁ " ብለዋል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
1.3K views17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 22:01:27
#ማስታወቂያ

የRemedial ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑንና በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋሞች በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ እንገልፃለን ።

ማሳሰቢያ :-
የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን።

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

Website:

https://placement.ethernet.edu.et
SMS: 9444

ትምህርት ሚኒስቴር
1.3K views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 16:49:08 #ማስታወቂያ የአቅም ማሻሻያ (Remedial )ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያ ጊዜ መራዘሙን ስለማሳወቅ

በ 2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 15/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንድትችሉ ቀኑ የተራዘመ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ መሆኑን እንገልጻለን።

ትምህርት ሚኒስቴር!
2.1K views13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 11:30:22 በ2015 ትምህርት ዘመን ከትምህርት መስክ እና ተቋም ምደባ ጋር ተያይዞ የቀረቡ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች ምላሽ በ

https://placement.ethernet.edu.et

ማየት የምትችሉ መሆኑንና ከዚህ በኋላ ከምደባ ጋር የተያያዘ ምንም አይነት ቅሬታ የማናስተናግድ መሆኑን እንገለጻለን።

ተማሪዎች የትምህርት ጥራትን ለማረጋጋጥ የጀመርናቸው የሪፎርም ሥራዎች እንዲሳኩ የበኩላችሁን እንድትወጡ እያልን በተመደባችሁበት የትምህርት መስክ እና ተቋም ህልማችሁ እንዲሳካና በቀጣይ ጠንካራ አገር ለመገንባት እንደ ህዝብ ለጀመርነው ተግባር ተገቢውን እውቀትና አስተውሎት የምትይዙበት ዘመን እንዲሆንላችሁ ከወዲሁ እንመኝላችኋለን።

ትምህርት ሚኒስቴር!
2.2K views08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 15:01:14
#ማስታወቂያ አቅም ማሻሻያ (Remedial )ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫን በተመለከተ

በ 2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 10/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ መሆኑን እንገልጻለን።

ትምህርት ሚኒስቴር!
1.3K views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 10:31:11 የዩኒቨርስቲ ምደባ ቅሬታ ማመልከቻ እየሰራልን አይደለም (Connection Error) ላላቹ፡፡ አሁን በ placement.ethernet.edu.et ድህረገጽ ደጋግማቹ ሞክሩት ይሰራል፡፡ ቅሬታ የሚያበቃው ዛሬ ከቀኑ 6፡00 ላይ ነው፡፡
2.3K viewsedited  07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ