Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Matric

የሰርጥ አድራሻ: @ethiomatric
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 33.87K
የሰርጥ መግለጫ

Ethio Matric ለ12ኛ ክፍል ኢንትራንስ ፈተና የሚያዘጋጅ የሞባይል አፕሊኬሽን ነው። አፕሊኬሽኑን ከዚህ ሊንክ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric ዳውንሎድ አድርጋቹ መጠቀም ትችላላቹ
ከአፕሊኬሽኑ ጋር ለተያያዘ ጥያቄ
@ethiomatric_support

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-10-05 23:09:41
የዩኒቨርሲቲ እና ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች አድራሻ ከዚህ ማግኘት ትችላላችሁ!

ምንጭ፡ የትምህርት ምዘና ኤጀንሲ
2.5K views20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 12:53:39 ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ባለፉት 6 ዓመታት ከፈተና ስርቆትና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ጋር ተያይዞ ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ችግር ገጥሞት የነበረ መሆኑን ገልጾ ዘንድሮ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ተፈታኞች ከቀጣይ ሰኞ ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲፈተኑ እንደሚደረግ ገልጿል።

ይሁን እንጂ ዘንድሮ ከ900,000 በላይ ተማሪዎች ለፈተና የሚቀመጡ በመሆኑ ይህንን ቁጥር በአንድ ጊዜ ማስተናገድ ባለመቻሉ በሁለት ዙር ፈተናው እንደሚሰጥ አስረድቷል።

በ1ኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከመስከረም 26-28 ወደሚፈተኑባቸው ዩንቨርሲቲዎች የሚገቡ ሲሆን ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 02 ፈተና ወስደው ከጥቅምት 03 ጀምሮ ወደመጡበት እንደሚመለሱ ተጠቅሷል።

በ2ኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከጥቅምት 5 አስከ ጥቅምት 6 ወደ ዩንቨርሲቲዎች የሚገቡ ሲሆን ከጥቅምት 8 እስከ ጥቅምት 11 ፈተና የሚወስዱ ይሆናል።

ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን እና ሌሎችም ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ ቁሶችን መያዝ እንደማይችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በተለያዩ አካባቢዎች ከሰላምና ፀጥታ ጋር ተያይዞ መፈተን የማይችሉና ከሀገር የወጡ የኮሚኒቲ ተማሪዎች በአጠቃላይ 56,000 ተማሪዎች ሲሆኑ በቀጣይ ሁለተኛ ዙር ፈተና እንደሚዘጋጅላቸው ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁን ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
1.6K viewsedited  09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 13:49:14
ትምህርት ሚኒስቴር በሁለት ዙር የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል።

ፈተናው ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 13/2015 ዓ.ም ቆይታ ይኖረዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 04/2015 ዓ.ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ከጥቅምት 05/2015 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 14/2015 ዓ.ም ፈተናውን ይወስዳሉ።

(ሙሉ መረጃው ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
4.1K views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-27 10:26:42 እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳቹ፡፡

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እየደረሰ ስለሆነ EthioMatric አፕሊኬሽን ለተማሪዎች ከየትኛውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ ነው፡፡ የአፕሊኬሽኑ ክፍያ ምንም እንኳን አንስተኛ ነው ብንልም ለአንዳንድ ተማሪዎች ሊያስቸግር ይችላል፡፡ ስለዚህም ለአንዳንድ ተማሪዎች ዛሬ እስከ ማታ ድረስ አፕሊኬሽኑን ካለክፍያ ከዚህ ቀጥሎ በምንስቀምጠው መስፈርት የምታሟሉ ከሆነ ቢያንስ እስከ ጥቅምት ፈተና ድረስ ካለከፍያ እንዲሰራላቹ የምናደርግ ይሆናል፡፡

እኛ ይህን በነጻ ልንከፍታላቹ የምንችለው ስልካቹ አነስተኛ ከሚባሉት ውስጥ ከሆነ ማለትም ስልካቹ 2GB RAM እና ከዛ በታች ከሆነ ብቻ ነው፡፡ የትኛው ተማሪ መክፈል ያስቸግረዋል ፤ የትኛው አያስቸግረውም ብለን መለየት አስቸጋሪ ነው ግን እንደዚህ ማድረግ የተሻለ ግምት ይሰጠናል፡፡

መስፈርቱን የምታሟሉ ከታች ያለው መመሪያ ይከተሉ
ወደኛ ቴሌግራም አካውንት @addis_support ሄዳቹ በዚህ format በነጻነት መልእክት ላኩልን
"ዛሬ የተጻፈውን አሟላለው ፤ አፕሊኬሽኑ ላይ SIGNUP ያደረኩበት ስልክ ቁጥር _____________ ይሄ ነው ብላቹ ላኩልን"፡፡
ከዛ እኛ ሲስተማችን ላይ አይተን መስፈርቱን ያሟላሉ ወይስ አያሟሉም የሚለውን ለይተን ፤ በተወሰነ ሰዓት ውስጥ ካለክፍያ የምናካትትላቹ ይሆናል፡፡
1.3K viewsedited  07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 13:02:15 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የተፈታኞችን መብትና ግዴታዎች እንዲሁም ለተፈታኞች የተፈቀዱ እና የተከለከሉ ነገሮች ያቀረቡ ሲሆን በዚህም
የተፈታኞች መብቶች የሆኑት፡-
ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት
በየኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽና ትራስ የማግኘት መብት
ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መጽሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች፣ የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት
የኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት
. በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበር፣ መጻፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት
ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት
የተፈታኞች ግዴታ የሆኑት፡-
. ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልም ይሁን መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ
ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት
ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ
ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ቁሳቁሶችን/ዕቃዎችን መያዝ የለበትም
ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት
ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ
ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል ውስጥና በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት
ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት
ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት
ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ አንሶላ፣ ብርድልብስና የትራስ ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት
ዩኒፎርም ለብሶ መገኘት አለበት
ለተፈታኞች የተፈቀዱ ነገሮች
አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማርና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበሩ ማስተወሻ ደብተር ፣ የትምህርት መጽሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መጽሐፍት፣ ባዶ ወረቀት
ደረቅ ምግቦች ወይም ሰንዱች ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)
ገንዘብ (ብር)
የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ
የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ የገላ ማድረቂያ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)
ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች
ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡
ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው
ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ /ቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣ ሲጋራ፣ በሓኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት (በሽሮፕም ይሁን በታብሌት፣ ህክምና መስጫ መርፌ)) መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀረ)
ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡
ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡
በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡
የሚሉት ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡

በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንና ፈተናውም ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው እንደሚፈተኑ የተገለጸ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ እንደሚያገኙም ተጠቁማል፡፡

ምንጭ፡ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
276 views10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-23 11:45:02
#ብሔራዊ_ፈተና

ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲ ከ50 ኪሎ ሜትር በላይ ለሆኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የትራንስፖርት ወጪን ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች እንደሚሸፍኑ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል።

ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም በሁለት ዙር ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አገልግሎቱ ገልጿል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ለ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኤፍ ቢ ሲ) የሰጡት ቃል ፦

- ፈተና ማተም ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች ከወዲሁ ተጠናቀዋል።

- ከመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በ50 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ ያሉ ተፈታኝ ተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪን በራሳቸው ይሸፍናሉ፤ ከ50 ኪሎ ሜትር ርቀት #በላይ የሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ ትምህርት ቤቶቻቸው የሚገኙባቸው ወረዳዎች ወጪያቸውን ይሸፍናሉ።

- ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ #የሚፈቀዱላቸው ፦

• መጽሐፍት፣
• ሲያጠኗቸው የነበሩ ማስታወሻወች፣
• የንጽህና መጠበቂያዎች
• የሌሊት ልብስ ከተፈቀዱት ቁሳቁስ መካከል ናቸው።

ተማሪዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ የቀበሌ መታወቂያ ፣ የመፈተኛ ካርድ ወይም አድሚሽን ካርድ መያዝ ይኖርባቸዋል።

- ተፈታኝ ተማሪዎች መያዝ #የሚከለከሏቸው ቁሳቁስ፦

• ማንኛውንም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
• ከጋብቻ ቀለበት ውጪ የተለየ ፈርጥ ያላቸው ቀለበቶች፣
• ሀብሎች ፣
• የጸጉር ጌጦች
• ድምጽ የሚያወጡ ጃኬቶች መያዝ አይቻልም።

- የመፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ለተፈታኝ ተማሪዎች የመኝታና የምግብ አገልግሎት ያመቻቻሉ።

@tikvahethiopia
2.5K views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-22 20:12:59
የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የልደት ምስክር ወረቀት በመያዝ ለፈተና እንዲቀመጡ ሊደረግ ነው!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኩል የመታወቂያ አገልግሎት መቆሙ የሚታወስ ነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ዝግጅት እየተደረገ እንደመሆኑ መጠን ለፈተና ለመቀመጥ ተፈታኞች የነዋሪነት መታወቂያ እየጠየቁ በመሆኑ በልደት የምስክር ወረቀት ለፈተና እንዲቀመጡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ማንኛውም የመታወቂያ አገልግሎት አሁን ላይ  የቆመ በመሆኑና የዜጎችን ማንነት የሚገልፅ ገዢ ሰነድ የልደት ምዝገባ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ለተፈታኞች በልደት የምስክር ወረቀት ለፈተና እንዲቀመጡ ለማድረግ ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ጋር በጋራ በመሆን በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ማስተካከያ እንዲደረግ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።የልደት ምዝገባ ያላከናወኑ ተፈታኞች ከወዲሁ ምዝገባውን አከናውነው የምስክር ወረቀት በእጃቸው እንዲይዙ ሲሉ አቶ ዮናስ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

[ዳጉ ጆርናል/ብስራት ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
3.4K views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 19:08:37
" በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል " - የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ፈተናው ከሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል።

ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናውን ፦
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤
- ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤
- ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ
- አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ዘንድሮ ፈተናው ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚሰጥ እንደመሆኑ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የፈተና ሂደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ፈተናው የተማሪዎችን የቀጣይ የህይወት ምዕራፍ የሚወስን በመሆኑ በአዲስ አበባ ፈተናው የሚሰጥባቸው ተቋማትም ሆኑ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በአዲስ አበባ 49,203 ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ መመዝገባቸውንና ፈተናውም ከመስከረም 30 ጀምሮ በቅድሚያ የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች ተፈትነው ሲጨርሱ የናቹራል ሳይንስ ተማሪዎች ቀጥለው እንደሚፈተኑ የተገለጸ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የምግብና የመኝታ አገልግሎቶችን በየተቋማቱ እንደሚያገኙም ተጠቁማል፡፡

(የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ)

@tikvahethiopia
6.7K views16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:41:02 Ethio Matric Google Play Store ላይ ተመልሷል ፤ ከዛሬ ጀምሮ ማግኘት ትችላላቹ:: ከታች ባለው ሊንክ ዳውንሎድ ማድረግ ትችላላቹ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric
1.2K views12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 09:38:53 ሰሞኑን Ethio Matric በጊዜያዊነት ችግር ምክንያት Google Play Store እየመጣ አይደለም፡፡

ይህ እስኪስተካከል 1-2 ሳምንት ሊፈጅ ስለሚችል እስከዛው ድረስ ከዚህ ዳውንሎድ አድርጋቹ መጠቀም ትችላላቹ፡፡
6.0K views06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ