Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Matric

የሰርጥ አድራሻ: @ethiomatric
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 33.87K
የሰርጥ መግለጫ

Ethio Matric ለ12ኛ ክፍል ኢንትራንስ ፈተና የሚያዘጋጅ የሞባይል አፕሊኬሽን ነው። አፕሊኬሽኑን ከዚህ ሊንክ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric ዳውንሎድ አድርጋቹ መጠቀም ትችላላቹ
ከአፕሊኬሽኑ ጋር ለተያያዘ ጥያቄ
@ethiomatric_support

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-02-13 21:54:42 ውድ የኢትዮማትሪክ ተጠቃሚዎች፡፡ ሰሞኑን ብዙ ስልኮች እየተደወሉልን ነው እና አብዛኞቹ ተደውሎልን የምንጠየቃቸው ጥያቄዎች ተደጋጋሚ አይነት ናቸው፡፡ እነዚህን በብዛት የምንጠየቃቸውን ጥያቄዎች በቋሚነት እና እኛ ጋር ሳይደወል በፍጥነት ምላሽ ማግኘት የምትችሉበትን መንገድ እየሰራን ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ከነገ ጀምሮ ለሚቀጥሉት አራት ቀናት የስልክ ጥሪ አገልግሎት የማንሰጥ መሆኑን በዚህ የምናሳውቃቹ ይሆናል፡፡

አፕሊኬሽናቹ ላይ የሚያስቸግራቹ ነገር ካለ ወይም ጥያቄ ካላቹ በቴሌግራም t.me/addis_support መጠየቅ ትችላላቹ፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ እንደማንኛውም ጊዜ አፕሊኬሽኑም ያለምንም ችግር መስራቱን ይቀጥላል ፤ መግዛት ለሚፈልግም መግዛት ይችላል፡፡ የምናደርገው ብቸኛ ለውጥ በዚህ አራት ቀን ውስጥ ወደኛ የሚደወሉ ስልኮች ማንሳት አለመቻል ነው፡፡
3.1K viewsedited  18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 19:07:45 ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜው ነገ ያበቃል!

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁና በወጪ መጋራት ወደ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች የተመደባችሁ ተማሪዎች ከምደባ ጋር ተያይዞ ያላችሁን ማንኛውም ቅሬታ እስከ የካቲት 07/2015 ዓ.ም 6፡00 ድረስ ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ምንም አይነት ማመልከቻም ሆን ቅሬታ በአካል እንደማይቀበል መግለጹ ይታወቃል።

ከምደባው ጋር ተያይዞ ጥያቄ ያላችሁ ተማሪዎች placement.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Complaint የሚለውን በመጫን ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ።

የትምህርት ሚኒስቴር
@ethio_moe
3.5K viewsedited  16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 11:48:04
#የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ማሳወቂያ

የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) እንዲተገበር መወሰኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው በ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን አነስተኛ የመግቢያ ውጤት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ።

1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት(ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናል።
3.4K views08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 23:23:19 አሁን ዌብሳይቱ መስራት ጀምሯል። በቴሌግራም ቦቱ Invalid Admission Number ያላችሁ ሁሉ በዌብሳይቱ ስትሞክሩት የተመደባቹበትን ዩኒቨርስቲ ያሳያል።

https://placement.ethernet.edu.et/

ካልሰራላቹ ፤ ደጋግማቹ መሞከር ይኖርባችሃል፡፡
4.5K viewsedited  20:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 22:30:40
#ማስታወቂያ የዩኒቨርስቲ ምደባ ተለቀቀ!

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለመማር ያመለከታችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የ Remedial ፕሮግራም መቁረጫ ነጥብ ነገ ይፋ የሚደረግ መሆኑን እናሳውቃለን።

Website: https://placement.ethernet.edu.et

SMS: 9444

Telegram bot: @moestudentbot
3.8K views19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 12:18:51
#ማስታወቂያ የዩኒቨርስቲ ምደባን በሚመለከት

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለመከታተል ላመለከታችሁ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከየካቲት 05/2015 እኩለ ሌሊት ጀምሮ ይፋ ይደረጋል።

ስለሆነም ተማሪዎች ከታች በተገለጹት አማራጮች የተመደባችሁበትን ተቋም ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ከየካቲት 15/2015 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትቆዩ እናሳስባለን፡፡

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

Website: https://result.ethernet.edu.et

SMS: 9444

Telegram bot: @moestudentbot

ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችሁ ማንኛውም ጥያቄ

result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Complaint

የሚለውን በመጫን ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ምንም አይነት ጥያቄም ሆነ ማመልከቻ በአካል የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን።

በዚሁ አጋጣሚ ተማሪዎች የትምህርት ጥራትን ለማረጋጋጥ የጀመርናቸውን የሪፎርም ሥራዎች እንዲሳኩ የበኩላችሁን እንድትወጡ እያልን በዩኒቨርስቲ ቆይታችሁ ህልማችሁ እንዲሳካና በቀጣይ ጠንካራ አገር ለመገንባት እንደ ህዝብ ለጀመርነው ተግባር ተገቢውን እውቀትና አስተውሎት የምትይዙበት ዘመን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር
3.7K views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 10:04:02
#MoE

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ያረጋገጠውና ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተላከ አንድ ደብዳቤ ፦

1. የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ነሐሴ አጋማሽ በከፍተኛ ተምህርት ተቋማት ውስጥ ለመስጠት ታቅዷል።

2. የ2015 ዓ/ም የመጀመሪያ ዲግሪ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና እስከ ሐምሌ 15 /2015 እንዲጠናቀቅ ታሳስቢ ተደርጓል።

3. የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው በመንግስት የኒቨርስቲዎችና ተቋማት የሚደለደሉትንና በራሳቸው ወጪ በመሸፈን በግል የሬሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን በተመለከተ ፦

3.1 የራሚዲያል ፕሮግራም ለአራት (4) ወራት ከየካቲት 15 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 15 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲሰጥ ታቅዷል።

3.2 የሬሚዲያል ፕሮግራም በተፈጥሮ ሳይንስና ማህበራዊ ሳይንስ በሁለት መስክ ተከፍሎ ከማዕከል በተዘጋጀ ይዘት መሰረት ዩኒቨርስቲዎች ተጨማሪ የሚያክሉትን በማካተት በተዘጋጀው መነሻ መሰረት ፕሮግራሙ እንዲከናወን ታቅዷል።

3.3 የሬሚዲያል ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ተማሪዎች ተከታታይ ምዘና እንዲኖራቸው ተደርጎ በየተቋማት የሚሰጠው ምዘና 30 % እና በማዕከል የሚዘጋጀው ፈተና 70% ተመዝነ በድምሩ አማካይና ከዚያ በላይ (50 ከመቶና በላይ) የሚያመጡት በመንግስት ተቋማት ሲከታተሉ የቆዩት በዚያው ተቋም መቀጠል የሚችሉ ሲሆን በራሳቸው ወጪ ሸፍነው ወደ ግል ተቋማት ሄደው መማር ቢፈልጉ መብታቸው የተጠበቀ ይሆናል።

(ተጨማሪውን ከደብዳቤው ያንብቡ)

Via @tikvahethiopia
2.5K viewsedited  07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 19:05:26 ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርስቲ  ምርጫ ማስተካከያ ቀን እስከ የካቲት 03/2013 ዓም. መራዘሙን አሳውቋል።

በ2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ እንዲሁም በመንግስት ተቋማት ገብተው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫቸውን እስከ የካቲት 03/2015 ዓ.ም 12፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያስተካክሉ ቀኑ የተራዘመ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደማህበራዊ ሳይንስ ቀይረው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች መቀየር የሚችሉት ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኋላ መሆኑን ገልጾ ይህም የሚሆነው ዩኒቨርስቲዎቹ ለመቀበል ፈቃደኛ ከሆኑ ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል። ስለዚህ ተማሪዎች የምርጫ ማስተካከያቸውን በጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
1.4K views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 20:44:52 በ 2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ እና በመንግስት ተቋማት ገብታችሁ መማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 02/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:-
በ 2015 የትምህርት ዘመን በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ መርጣችሁ መመደብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ የምትሹ (ተመሳሳይ ጾታ ያላችሁ መንትያዎች፣ እመጫቶች(በቅርቡ የወለዳችሁ እናቶች) ፣ ነፍሰጡር ተማሪዎች፣ በመንግስት ሆስፒታሎች ህክምና ቦርድ የተረጋገጠ ልዩ ክትትል የሚሻ ህመም ታማሚዎች … ወዘተ) ተማሪዎች ማመልከቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በቀጣዩ ሊንክ
https://student.ethernet.edu.et

የትምህርት ሚኒስቴር
3.3K views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 09:29:11 ግን neaea.gov.et:8081 አሁን እየሰራ አይደለም
2.2K views06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ