Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Matric

የሰርጥ አድራሻ: @ethiomatric
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 33.87K
የሰርጥ መግለጫ

Ethio Matric ለ12ኛ ክፍል ኢንትራንስ ፈተና የሚያዘጋጅ የሞባይል አፕሊኬሽን ነው። አፕሊኬሽኑን ከዚህ ሊንክ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric ዳውንሎድ አድርጋቹ መጠቀም ትችላላቹ
ከአፕሊኬሽኑ ጋር ለተያያዘ ጥያቄ
@ethiomatric_support

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-02-02 20:58:08 የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ነገ አርብ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት የሚያበቃ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲታቀርቡ እናሳውቃለን፡፡ ቀድማችሁ ቅሬታ ያቀረባችሁ ተፈታኞች የቅሬታችሁን መልስ neaea.gov.et:8081 ድረ ገጽ ላይ የመለያ ቁጥራችሁን (Registration Number/ID) ብቻ በማስገባት ከዛሬ 12፡00 ሰዓት…
3.4K views17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 20:53:07 የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ነገ አርብ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት የሚያበቃ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲታቀርቡ እናሳውቃለን፡፡

ቀድማችሁ ቅሬታ ያቀረባችሁ ተፈታኞች የቅሬታችሁን መልስ neaea.gov.et:8081 ድረ ገጽ ላይ የመለያ ቁጥራችሁን (Registration Number/ID) ብቻ በማስገባት ከዛሬ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ
• ቅሬታዎች ሁሉም ተጣርተው ሲጠናቀቁ በቀጣይ ቀናት የሚናሳውቅ በመሆኑ የቅሬታችሁ ምላሽ ያልደረሳችሁ ተፈታኞች በትዕግስት እንዲትጠብቁ እናሳስባለን፡፡
• ባልተሟላ ወይም በተሳሳተ ወይም በሌላ ሰው መለያ ቁጥር ያመለከታችሁ የስም ዝርዝራችሁን ዛሬ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ከላይ በተጠቀሰው ድረ ገጽ አድራሻ ላይ የምናሳውቅ ሲሆን ቅሬታችሁን በድጋሚ በተስተካከለ መለያ ቁጥራችሁ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
3.5K viewsedited  17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 10:18:44
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር፤ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ50% በታች ያመጡና በዩቨርሲቱ የቅበላ አቅም " ዕጩ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች " በዕጩነት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን ነጥብ ከ10 እስከ 15 ቀናት ውስጥ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለፋና ብሮድካስት በሰጡት ቃለ ምልልስ ፤ " ዕጩ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች " በዕጩነት ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን ነጥብ በጥቂት ቀናት ለማሳወቅ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ፤ " 10 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ይሄንን ለህዝቡ ይፋ እናደርጋለን።  በ10 ቀን ውስጥ የትኞቹ ተማሪዎች ዕጩ በመንግስት ተቋማት ሄደው እንደ ስኮላርሺፕ ተማሪ ዶርም ይዘው ምግብ ቀርቦላቸው በቅተው ለሚቀጥለው ዓመት ፌሬሽ ማን የመሆን ዕድል ይሰጣቸዋል፤ ሌሎች ደግሞ በሌሎች አማራጮች ይማራሉ የሚለውን ጉዳይ ቢገፋ በ10 ቀን ውስጥ ማወቅ አለብን በጣም ቢገፋ በ15 ቀን ውስጥ ማወቅ አለብን " ብለዋል።

" ዕጩ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች " ዩኒቨርሲቲ እንዲገቡ ተደርጎ ራሳቸውን የሚያበቃቸውን ትምህርት ተከታትለው በሚቀጥለው ዓመት የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በመሆን ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ለማድረግ ነው የትምህርት ሚኒስቴር አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ የታወቀው።

@tikvahethiopia
2.3K views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 20:51:15 በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው በመላ ሀገሪቱ ከ600 በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ወጪ እንደሚሸፍን አማራ ባንክ አሳውቋል።

ባንኩ በመላ ሀገሪቱ ከ600 በላይ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው በወር 750 ብር እየከፈለ እንደሚያስተምር የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሄኖክ ከበደ ገልጸዋል።

ውሳኔው የባንኩ የማኀበረሰባዊ አገልግሎት አካል መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል።

በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር እውቅናና ሽልማት ይሰጣቸዋል መባሉ ይታወሳል።

@tikvahuniversity
5.2K views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 21:45:51 ከሶሻል ያለፉት ከ1.2% ተማሪዎች ብቻ ናቸው፡፡

ከተፈኑት 570,000 የሶሻል ተማሪዎች ውስጥ ያለፉት 6,973 ተማሪዎች ብቻ ናቸው፡፡
6.8K viewsedited  18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 21:10:17
6.2K views18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 15:42:39
ትምህርት ሚኒስቴር ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደማይቀላቀሉ የገለፀ ሲሆን ነገር ግን የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት በውጤታቸው መሰረት ተጨማሪ ተማሪዎችን በመቀበል ለቀጣይ ዓመት ዩኒቨርሲቲ መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት እንዲያገኙ ይሰራል መባሉን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግባል።

@tikvahethiopia
5.7K views12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 14:50:22 በ2014 ዓም የትምህርት ዘመን ለፈተና የተመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላላ 985ሺ 3354 ተማሪዎች ሲሆኑ ለፈተና የቀረቡት 92.2 % 908ሺ ሺህ 256 ተማሪዎቹ ሲሆኑ 77ሺህ 98 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም ተብሏል።በደንብ ጥሰት ፣ለመኮራረጅ በመፈለግ እና በሌሎች ምክንያቶች 50ሺህ 170 ተማሪዎች ሳይፈተኑ ቀርተዋል።

በ2014 የትምህርት ዘመን 899ሺህ 520 ተማሪዎች ተፈትነዋል ።

በፆታ ማዕከልነት የአማካይ ውጤት በወንዶች 30.2 እንዲሁም ሴቶች 28.09 % አማካይ ውጤት አስመዝግበዋል።

በትምህርት ዘርፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ በተሻለ ውጤት ያስመዘገቢ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ 31.63 ከመቶ እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ 27.79 ከመቶ በአማካኝ አስመዝግበዋል።

በክልል ደረጃ ይህየ ነው የሚባል የውጤት ልዮነት እንደሌለ የተገለፀ ሲሆን አዲስ አበባ፣ሀረሪ እና ድሬደዋ የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል።

ከተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወንድ ከ 700፤ 666 ያስመዘገበ ሲሆን 650 ሴት ተማሪ አስመዝግባለች።በማህበራዊ ሳይንስ ከ600 ወንድ 524 አስመዝግቧል።እነዚህ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎይ በትምህርት ሚኒስቴር እውቅና እና ሽልማት ይሰጣቸዋል ተብሏል።

via @YeneTube
7.1K views11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 14:49:05
#Update

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ከ50 % በላይ ያመጡት ከተፈታኞች ውስጥ 3.3 በመቶ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፈተናውን በትክክል ከወሰዱት 896,520 ተማሪዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ ያመጡት፤ 29,909 መሆኑን ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በትላንትናው ዕለት ይፋ የተደረገውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

@tikvahethiopia
5.0K views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 10:01:40 ይሄ ነገር እውነት እየመሰለ ነው

ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች አሐዝ ከ28 ሺህ "ብዙም እንደማይርቅ" ቲክቫህ ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጧል።
7.1K views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ