Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Matric

የሰርጥ አድራሻ: @ethiomatric
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 33.87K
የሰርጥ መግለጫ

Ethio Matric ለ12ኛ ክፍል ኢንትራንስ ፈተና የሚያዘጋጅ የሞባይል አፕሊኬሽን ነው። አፕሊኬሽኑን ከዚህ ሊንክ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric ዳውንሎድ አድርጋቹ መጠቀም ትችላላቹ
ከአፕሊኬሽኑ ጋር ለተያያዘ ጥያቄ
@ethiomatric_support

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2022-08-15 11:51:07
#MoE

" የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 /2015 ዓ/ም ጀምሮ በ2 ዙር እንዲሰጥ ታቅዷል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ2ዐ14 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርስቲዎች እንዲሰጥ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ #በሁለት_ዙር እንዲሰጥ መታቀዱን በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተፈርሞ ለ42 ዩኒቨርሲቲዎች በተላከውን እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትክክለኛነቱን ባረጋገጠው ደብዳቤ መመልከት ችለናል።

በዚሁ መሠረት ከመስከረም 28 እስከ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ዩኒቨርስቲዎች ፦

1. ምንም አይነት የመደበኛ ተማሪ በግቢ እንዳይኖር እንዲያደርጉ፤

2. በቀጣይ በሚገለጸው ተማሪ ቁጥር ልክ ምግብ እንዲቀርብ ዝግጅት እንዲያደርጉ፤

3. ለፈተናዎች ማቆያ ቦታ እንዲዘጋጅ እና

4. የፈተናውን አሰጣጥና ደህንነት የሚቆጣጠር በፕሬዚዳንት የሚመራ ዋና ግብረ-ኃይልና በየካምፓሶቹ በዲን /ካምፓስ ኃላፊ የሚመራ ንዑስ ግብረ-ኃይል እንዲያደራጁ መልዕክት ተላልፎላቸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች የ2ዐ15 የአካዳሚክ ካላንደር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወቅት (ከመስከረም 28 - ጥቅምት 17) ታሳቢ በማድረግ እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia
8.8K views08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 10:08:53 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለጸ!

የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ የኤጀንሲው መረጃ ያመላክታል፡፡
17.5K views07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 23:45:08
#ትምህርት_ሚኒስቴር

የ2014 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑን የሚገልፁት ፕ/ር ብርሃኑ ጎን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎችና በፌዴራል ተቋማት እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢፕድ የሰጡት ቃል፦

" ...የክልል ባለሟሎች፣ የክልል ኃላፊዎችን ከፈተና ጉዳይ ጋር እንለያቸው ፤ ፈተናው እራሱ የፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስለሆነ በፌዴራል ተቋማት ውስጥ ብቻ እንስጥ ብለን አሁን በሙሉ ተማሪዎቹን አጓጉዘን ቢቻል ሁሉንም ከክልላቸው ውጭ በሆኑ ክልሎች ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እና የፌዴራል ተቋማት ውስጥ ለመስጠት ነው እየተዘጋጀን ያለነው።

ያ የሚያደርገው ሁለት ነገር ነው። አንደኛ በመንገድ ላይ ሊኖር የሚችለውን የመሰረቅ አደጋ ይቀንሰዋል። ሁለተኛ ክፍል ውስጥ ከተገባ በኃላ ለመስረቅ የሚቻልበትን አደጋ ይቀንሰዋል።

ከዛም በላይ ፈተናዎቹን በማዘጋጀት ደረጃ በፊት በ4 የተለያዩ ፈተናዎች ነበር የምናዘጋጀው እስከ 12 አድርገን Completely scrambled እንዲሆኑና ማንም ጎኑ ያለው ተማሪ የሚፈተነው ፈተና አንተ ከምትፈተነው ፈተና order ጋር በፍፁም ያልተገናኘ እንዲሆን አድርገን እየሰራን ነው።

ይሄ በጣም በብዙ ደረጃ የፈተና ስርቆትን ይቀንሰዋል ብለን ነው ተስፋ የምናደርገው። "

@tikvahethiopia
11.6K views20:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 18:13:47
የአሁኑ የኢንትራንስ ፈተና ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል መሆኑ ይታወቃል፡፡

ለዚህም ኢትዮማትሪክ ላይ በቅርቡ አዲስ update ለቀናል፡: ይህም
ከ9-10 እና ከ11-12 ያለውን ያለምንም ችግር በቀላሉ እየቀያየራቹ መጠቀም የምትችሉበት መንገድ እና
ከ9-10ኛ ክፍል ላሉት ደግሞ ተጨማሪ ፈተናዎችን አካትተናል፡፡

ይህ የሚገኘው በአዲሱ ቨርዥን (6.1) ብቻ ሲሆን ፤ በዚህ ሊንክ update ማድረግ ትችላላቹ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric
13.1K viewsedited  15:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 21:12:40
16.6K views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 09:38:46
14.6K views06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 13:40:03
13.4K views10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 21:26:53
14.6K views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 11:44:27
10.4K views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-26 09:54:48
የ ኢንትራንስ ፈተና ከ 9 -12 መሆኑን መቼ ነው ያወቃቹት
Anonymous Poll
36%
በዚህ 2 ሳምንት
40%
ይሄ ነገር የእውነት ነው አንዴ? አስከአሁን አላመንኩም
6%
በዚህ 4 ወር ውስጥ
7%
ከ4ወር በፊት
11%
ከነዚህ ውጭ : የምርጫ ውጤት ለማየት ብቻ
2.5K voters14.0K views06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ