Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO ARSENAL

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_arsenal — ETHIO ARSENAL
ርዕሶች ከሰርጥ:
Epl
Size
Northlondonderby
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_arsenal
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 279.53K
የሰርጥ መግለጫ

–The Best Arsenal Football Club Telegram Channel in Ethiopia.
–በኢትዮጵያ ትልቁ የአርሰናል ቴሌግራም ቻናል ነው። ስለ አርሰናል አዳዲስና ትኩስ መረጃዎች የዝውውር ፣ ዜናዎች ፣ኃይላይቶች፣ቪዲዬች፣ ትንታኔ በቀጥታ ያገኛሉ። ____________________
📥 ለማስታወቂያ ስራ : @Mex_classic

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2024-04-09 14:50:56
ዴክላን ራይስ እና ጆሽዋ ኪሚች በዚ ሲዝን ያላቸው ቁጥራዊ መረጃ

[ WHOSCORED ]

SHARE @ETHIO_ARSENAL
20.8K viewsᴋᴀʟᴜ 27 , 11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 14:46:45
|| አሜሬትስ እሳት ይሆናል !

◉ ተጫዋቾቹ ሲወጡ በኖርዝባንክ እና በምስራቅ ባለዉ መቀመጫ በኩል ከፍ ብለው የሚሰቀሉ ባነሮች ይኖራሉ ።

◉ ከመጀመሩ በፊት የብርሃን ትርኢት ይታያል።

◉ ከጨዋታው በፊት ተጫዋቾቹ ወደ ሜዳ ሲገቡ ልክ ምስሉ ላይ እንዳለዉ የ እሳት ነበልባል ይወጣል ።

◉ ለደጋፊዎች የትም እንዳሄዱ የተለያዩ ምግቦችን እና መጠጦችን ይቀርባሉ ። [ Connor Humm]

photo

SHARE @ETHIO_ARSENAL
20.8K views𝙼𝚎𝚜𝚞𝚝 𝚂𝚊𝚖𝚒, edited  11:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 14:45:29
ዊሊያም ሳሊባ እና ዳዮት ኦፔሜካኖ በዚ ሲዝን ያላቸው ቁጥራዊ መረጃ ! ዊሎ

[ WHOSCORED ]

SHARE @ETHIO_ARSENAL
19.3K viewsᴋᴀʟᴜ 27 , edited  11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 14:34:36
የዛሬውን ጨዋታ በኤምሬትስ መግደል አለብን አምና ሲቲ ባየርንን እንዳረገው ።

SHARE @ETHIO_ARSENAL
20.2K viewsᴋᴀʟᴜ 27 , 11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 14:30:28
90MIN አርሰናል 2-0 ባየርንሙኒክን ያሸንፉል ሲሉ ገምተዋል !

SHARE @ETHIO_ARSENAL
20.8K viewsᴋᴀʟᴜ 27 , 11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 13:52:00
ኤምሬትስ ስታድየም በአዲስ ባነር ብቅ ብሏል።

"SHARE" . @ETHIO_ARSENAL
23.2K viewsEʟᴀ Sᴀᴋᴀ, edited  10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 13:44:31 Arsenal Vs Bayern Tactical Analysis

ባየርን ትልቅ አሰልጣኝ አለው በተለያዩ ቡድኖች ላይ ውጤታማ የሆነ እና የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያሳካ። ባየርን አሁን ላይ ወጥ የሆነ ቡድን ባይሆን የአሰልጣኙ የማሰልጠን ችግር ሳይሆን የገባበት ሰዓት ትክክል ስላልሆነ ነው።

አርሰናል ወጣት በታክቲክ ግን ምጡቅ የሆነ አሰልጣኝ አለው! በታክቲክ በጨዋታ ፊሎዞፊ ኳስን ይዞ መጫዎት የሚወድ አሰልጣኝ ሲሆን መከላከል ከፈለገ ግን መከላከል የሚችል ራሱን በአንድ ደረጃ ከፍ ያደረገ ትልቅ አሰልጣኝ ነው። አርሰናል አሁን ላለበት ደረጃ የደረሰው ከስህተቶች ትምህርት ወስዶ ፣ የተጨዋቾችን ጥራት ጨምሮ ነው።

በቡድን ስብስብ ሲመዘኑ በአሁኑ ሰዓት በተወሰነ መልኩ ባየርን የተሻለ ነው ። ምክንያቱም ባየርን ከግብ ጠባቂ ጀምሮ እስከ አጥቂ ምርጥ ምርጥ ተጨዋቾችን ይዟል። ግብ ጠባቂ ማኑዌል ኑየር ፣ ተከላካይ ላይ ጉሬሮ፣ ዲየር፣ ኦፓሚካኖ፣ ዲላይት፣ ማዝራዊ፣ ኪም መሀል ላይ ጎርቴዝካ፣ ኪሚች፣ ሙሲየላ ፣ሙለር፣ ሌማር፣ አጥቂ ላይ ግናብሪ፣ ኬን፣ ኮማን፣ ሳኔ እና ቴልን የመሳሰሉ ድንቅ ተጨዋቾች አሏቸው።

ክለባችንም አሁን በጣም ጥሩ ስኳድ አለው በስኳድ ደረጃ ባየርን የተሻለ ሲሆን ልዩነት አሁናዊ አቋም ነው። ለአንድ ቡድን ስኬት ዋናው መሰረት Coordination ነው አንድ ቡድን Coordinationኑ ጥሩ ከሆነ ጨዋታውን ለመሻነፍ ግማሽ % ተራምዷል። አርጀንቲና የአለም ዋንጫ ከማሳካቷ በፊት የምትቸገረው በስብስብ እጥረት ሳይሆን Lack of coordinated ችግር ስለነበር ነው። አሁን ላይ የባየርን አንዱ ችግር Lack of Coordination ነው።

የቡድን ውህደት በተለያዬ ምክንያት ይፈጠራል አንደኛ በጉዳት ምክንያት ፣ ይሄ ባለፈው አመት ላይ አርሰናል ተቸግሮ ነበር። ሌላኛው መልበሻ ክፍሉ ላይ ጥሩ አለመሆን፣ ሌላው የአሰልጣኝ ችግር ነው። ባየርን በአሁኑ ሰዓት Team Coordination ይጎለዋል አርሰናልም ይሄንን የቡድን ውህደት ችግር በመጠቀም የማሸነፍ ቅድመ ግምት ይሰጠዋል። ስለሁለቱ ቡድኖች ይሄንን ካልኩ ወደ ግምታዊ አሰላለፍ እና የጨዋታ ፅንሰ ሀሳብ የተወሰነ ነገር ልላችሁ ወደድኩ

ባየር ሙኒክ

ባየር ሙኒክ በቶማስ ቱሄል እየተመራ በ4 2 3 1 Formation የጨዋታ ፍልስፍና ይጫዎታል ተብሎ ይገመታል ። ግብ ጠባቂ ኑየር ፣ ተከላካይ ጉሪየሮ፣ ዲላይት፣ ዲየር እና ኪሚች በፉልባክ ሚና የመጫዎት እድል ይኖረዋል! መሀል ክፍሉ በDouble Pivot በሌማር እና ጎርቴዝካ እንዲሁም 10 ቁጥር ቦታ ላይ ሙሲየላ ፣ በቀኝ እና ግራ ክንፍ አጥቂ ላይ ሳኔ እና ኮማን እና በብቸኛ አጥቂነት በሀሪ ኬን ወደ ሜዳ ይገባሉ ተብሎ ይገመታል

የቶማስ ቱሄል የጨዋታ ፍልስፍና በተለዋዋጭነት እና በቁጥር ብልጫ ላይ በማተኮር የሚታወቅ ነው። ቱሄል በአንድ የጨዋታ ፍልስፍና አይፀናም እንደ ተጨዋቾቹ ድክመት እና ጥንካሬ የጨዋታ ፎርሜሽኖችን እና ፍልስፍናውን ይቀያይራል። ይሄ የጨዋታ ፍልስፍናቸው ግን በዚህ አመት ችግሮችን ፈጥሯል! የቡድን ውህደቱንም አሳጥቶታል።

ቱሄል በመከላከል ላይ በአካላዊ ሰውነታቸው እና በፍጥነታቸው ጥሩ የሆኑትን ኦፓሚካኖን እና ሄርናንደዝን ለማጣመር የሞከሩ ሲሆን! ቱሄል እነዚህ ተጨዋቾችን ማጣመር የፈለገበት ምክንያት ወደፊት ተጠግተው ተጋጣሚን ጫና ውስጥ ለመክተት አስበው ነበር ነገር ግን ይሄ የጨዋታ ፍልስፍናቸው በመልሶ ማጥቃት ቡድኖች ጫና ስለፈጠሩበት ይሄንን ጥምረትም ማስቀጠል አልቻለም።

ይሄ የጨዋታ ፍልስፍና አጥቂውን ጥሩ ቢያደርገውም መከላከሉን ደካማ በማድረጉ ማጥቃት እና የመከላከል ሁኔታው ተቃራኒ በመሆኑ ቡድኑ በቀላሉ በመልሶ ማጥቃት የሚጫዎት ቡድን እንዲያሸንፈው ምክንያት ሁኗል። የቶማስ ቱሄል ቡድንም ዋናው ችግር ይሄ ነው። ስለዚህ አርሰናል ይሄንን የጨዋታ ፍልስፍና ምክንያት በማድረግ ተከላካይ ላይ ቶሚያሱን ወይም ኪዮርን በግራ ፉልባክ ላይ መጠቀሙ አስፈላጊ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ የተጋጣሚን ስጋት በፍጥነት በቶሚ/ኪዮር እና በቤን ዋይት ከተከላከሉ በዋላ ኳስ በማሰራጨት አስደናቂ የሆነውን ፓርቴን በመጠቀም ከተጋጣሚ በፍጥነት ኳስ  በመንጠቅ ፓርቴ ለፈጣኑ  ጋብርኤል ማርቲኔሊ በመስጠት የግብ እድል መፍጠር ይቻላል። ስለዚህ በዛሬው ጨዋታ ማርቲኔሊ ግዴታ አስፈላጊ ነው።

ክፍል 2: How to defend Munic threat ይቀጥላል
23.8K viewsJack Wilshere |Y|, 10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 13:44:22
22.6K viewsJack Wilshere |Y|, 10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 13:44:18
22.9K viewsJack Wilshere |Y|, 10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 13:44:13
22.9K viewsJack Wilshere |Y|, 10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ