Get Mystery Box with random crypto!

Arsenal Vs Bayern Tactical Analysis ባየርን ትልቅ አሰልጣኝ አለው በተለያዩ | ETHIO ARSENAL

Arsenal Vs Bayern Tactical Analysis

ባየርን ትልቅ አሰልጣኝ አለው በተለያዩ ቡድኖች ላይ ውጤታማ የሆነ እና የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያሳካ። ባየርን አሁን ላይ ወጥ የሆነ ቡድን ባይሆን የአሰልጣኙ የማሰልጠን ችግር ሳይሆን የገባበት ሰዓት ትክክል ስላልሆነ ነው።

አርሰናል ወጣት በታክቲክ ግን ምጡቅ የሆነ አሰልጣኝ አለው! በታክቲክ በጨዋታ ፊሎዞፊ ኳስን ይዞ መጫዎት የሚወድ አሰልጣኝ ሲሆን መከላከል ከፈለገ ግን መከላከል የሚችል ራሱን በአንድ ደረጃ ከፍ ያደረገ ትልቅ አሰልጣኝ ነው። አርሰናል አሁን ላለበት ደረጃ የደረሰው ከስህተቶች ትምህርት ወስዶ ፣ የተጨዋቾችን ጥራት ጨምሮ ነው።

በቡድን ስብስብ ሲመዘኑ በአሁኑ ሰዓት በተወሰነ መልኩ ባየርን የተሻለ ነው ። ምክንያቱም ባየርን ከግብ ጠባቂ ጀምሮ እስከ አጥቂ ምርጥ ምርጥ ተጨዋቾችን ይዟል። ግብ ጠባቂ ማኑዌል ኑየር ፣ ተከላካይ ላይ ጉሬሮ፣ ዲየር፣ ኦፓሚካኖ፣ ዲላይት፣ ማዝራዊ፣ ኪም መሀል ላይ ጎርቴዝካ፣ ኪሚች፣ ሙሲየላ ፣ሙለር፣ ሌማር፣ አጥቂ ላይ ግናብሪ፣ ኬን፣ ኮማን፣ ሳኔ እና ቴልን የመሳሰሉ ድንቅ ተጨዋቾች አሏቸው።

ክለባችንም አሁን በጣም ጥሩ ስኳድ አለው በስኳድ ደረጃ ባየርን የተሻለ ሲሆን ልዩነት አሁናዊ አቋም ነው። ለአንድ ቡድን ስኬት ዋናው መሰረት Coordination ነው አንድ ቡድን Coordinationኑ ጥሩ ከሆነ ጨዋታውን ለመሻነፍ ግማሽ % ተራምዷል። አርጀንቲና የአለም ዋንጫ ከማሳካቷ በፊት የምትቸገረው በስብስብ እጥረት ሳይሆን Lack of coordinated ችግር ስለነበር ነው። አሁን ላይ የባየርን አንዱ ችግር Lack of Coordination ነው።

የቡድን ውህደት በተለያዬ ምክንያት ይፈጠራል አንደኛ በጉዳት ምክንያት ፣ ይሄ ባለፈው አመት ላይ አርሰናል ተቸግሮ ነበር። ሌላኛው መልበሻ ክፍሉ ላይ ጥሩ አለመሆን፣ ሌላው የአሰልጣኝ ችግር ነው። ባየርን በአሁኑ ሰዓት Team Coordination ይጎለዋል አርሰናልም ይሄንን የቡድን ውህደት ችግር በመጠቀም የማሸነፍ ቅድመ ግምት ይሰጠዋል። ስለሁለቱ ቡድኖች ይሄንን ካልኩ ወደ ግምታዊ አሰላለፍ እና የጨዋታ ፅንሰ ሀሳብ የተወሰነ ነገር ልላችሁ ወደድኩ

ባየር ሙኒክ

ባየር ሙኒክ በቶማስ ቱሄል እየተመራ በ4 2 3 1 Formation የጨዋታ ፍልስፍና ይጫዎታል ተብሎ ይገመታል ። ግብ ጠባቂ ኑየር ፣ ተከላካይ ጉሪየሮ፣ ዲላይት፣ ዲየር እና ኪሚች በፉልባክ ሚና የመጫዎት እድል ይኖረዋል! መሀል ክፍሉ በDouble Pivot በሌማር እና ጎርቴዝካ እንዲሁም 10 ቁጥር ቦታ ላይ ሙሲየላ ፣ በቀኝ እና ግራ ክንፍ አጥቂ ላይ ሳኔ እና ኮማን እና በብቸኛ አጥቂነት በሀሪ ኬን ወደ ሜዳ ይገባሉ ተብሎ ይገመታል

የቶማስ ቱሄል የጨዋታ ፍልስፍና በተለዋዋጭነት እና በቁጥር ብልጫ ላይ በማተኮር የሚታወቅ ነው። ቱሄል በአንድ የጨዋታ ፍልስፍና አይፀናም እንደ ተጨዋቾቹ ድክመት እና ጥንካሬ የጨዋታ ፎርሜሽኖችን እና ፍልስፍናውን ይቀያይራል። ይሄ የጨዋታ ፍልስፍናቸው ግን በዚህ አመት ችግሮችን ፈጥሯል! የቡድን ውህደቱንም አሳጥቶታል።

ቱሄል በመከላከል ላይ በአካላዊ ሰውነታቸው እና በፍጥነታቸው ጥሩ የሆኑትን ኦፓሚካኖን እና ሄርናንደዝን ለማጣመር የሞከሩ ሲሆን! ቱሄል እነዚህ ተጨዋቾችን ማጣመር የፈለገበት ምክንያት ወደፊት ተጠግተው ተጋጣሚን ጫና ውስጥ ለመክተት አስበው ነበር ነገር ግን ይሄ የጨዋታ ፍልስፍናቸው በመልሶ ማጥቃት ቡድኖች ጫና ስለፈጠሩበት ይሄንን ጥምረትም ማስቀጠል አልቻለም።

ይሄ የጨዋታ ፍልስፍና አጥቂውን ጥሩ ቢያደርገውም መከላከሉን ደካማ በማድረጉ ማጥቃት እና የመከላከል ሁኔታው ተቃራኒ በመሆኑ ቡድኑ በቀላሉ በመልሶ ማጥቃት የሚጫዎት ቡድን እንዲያሸንፈው ምክንያት ሁኗል። የቶማስ ቱሄል ቡድንም ዋናው ችግር ይሄ ነው። ስለዚህ አርሰናል ይሄንን የጨዋታ ፍልስፍና ምክንያት በማድረግ ተከላካይ ላይ ቶሚያሱን ወይም ኪዮርን በግራ ፉልባክ ላይ መጠቀሙ አስፈላጊ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ የተጋጣሚን ስጋት በፍጥነት በቶሚ/ኪዮር እና በቤን ዋይት ከተከላከሉ በዋላ ኳስ በማሰራጨት አስደናቂ የሆነውን ፓርቴን በመጠቀም ከተጋጣሚ በፍጥነት ኳስ  በመንጠቅ ፓርቴ ለፈጣኑ  ጋብርኤል ማርቲኔሊ በመስጠት የግብ እድል መፍጠር ይቻላል። ስለዚህ በዛሬው ጨዋታ ማርቲኔሊ ግዴታ አስፈላጊ ነው።

ክፍል 2: How to defend Munic threat ይቀጥላል