Get Mystery Box with random crypto!

ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)

የቴሌግራም ቻናል አርማ esatchannal — ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)
የቴሌግራም ቻናል አርማ esatchannal — ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)
የሰርጥ አድራሻ: @esatchannal
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.98K
የሰርጥ መግለጫ

አዳዲስ ወሬዎችን ዜናዎችን ማግኝት ከፈለጉ እኛን ይቀላቀሉ ለወዳጅ ዘመዶ #share

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-07-04 10:57:43
ትግራይ
ትምህርት ሚኒስቴርን ጨምሮ ሌሎች የፌደራል ተቋማት የፕሪቶሪያው ስምምነት ጥሰዋል፣ ከዚህ በኋላ ይሄን ስምምነት ለማክበር አንገደድም እያሉ በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ለሚገኙ ታጣቂዎች እየሰበሰቡ የፖሮፖጋንዳ ዘመቻ በማካሄድ ላይ መሆናቸው የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልጸዋል። በዚህም በማይጨው፣በኤርትራ አዋሳኝ ድንበር አካባቢዎች እንዲሁም በጠለምት አካባቢዎች ታጣቂዎችን እየሰበሰቡ የደቡብ አፍሪካው ስምምነት በይፋ መጣሱን እየገለፁላቸው ይገኛሉ። የተቀበረ መሳሪያ ጭምር አውጡ ልምምድ አድርጉ የሚል ነገር በአለቆቻቸው እንደተነገራቸው ታውቋል። ትምህርት ሚኒስቴር ሰሞኑን ይፋ እንዳደረገው ለወልቃይት እና በራያ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በአማራ ክልል ስር  መመደቡ ይታወሳል። በዚህም ጌታቸው ረዳ ይሄ ውሳኔ የደቡብ አፍሪካውን ስምምነት በግልጽ የጣሰ እና የትግራይን የወሰን ክልል የጣሰ ነው ማለቱ ይታወሳል።
4.9K views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 10:57:42 የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሜዲስን፤ ነርሲንግ፤ ጤና መኮንን፤ አንስቴዥያ፤ ፋርማሲ፤ ሜዲካል ላቦራቶሪ፤ ሚድዋይፈሪ፤ ዴንታል ሜዲስን፤ ሜዲካል ራዲዮሎጂ፤ ኢንቫይሮመንታል ሄልዝ፤ ፔዲያትሪክ ኤንድ ቻይልድ ሄልዝ፤ ሳይካትሪ ነርሲንግ፤ እና ኢመርጀንሲ ኤንድ ክሪቲካል ኬር ነርሲንግ ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ፈተናው ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ትምህርት ሚኒስቴር ከሚሰጠው የመውጫ ፈተና (Exit exam) ጋር በማቀናጀት የሚሰጥ መሆኑን እየገለፅን:-

1. የፈተናው አሰጣጥ ሂደት በኮምፒውተር ይሆናል።

2. የፈተናው መርሃግብር

- በ30/10/2015 ዓ.ም Nursing, Pharmacy, Public Health, Anesthesia, Medical Radiology Technology and Environmental Health, Medical Laboratory Science, Midwifery, Medicine, Dental Medicine, Pediatric and Child Health Nursing, Psychiatric Nursing and Emergency and Critical Care Nursing

3. እያንዳንዱ ተፈታኝ ከሚፈተንበት ቀን አንድ ቀን ቀደም ብሎ ማለትም ሰኔ 29/2015 ዓ.ም ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራትና፤ የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል።

4. የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን ለመስራት፤ ወደ ፈተና የሚያስገባውን Username and Password እና የመፈተኛ ጣቢያ ለማወቅ የመረጣችሁብት ዩኒቨርስቲ ዋና ግቢ ከፈተናው አንድ ቀን በፊት ማለትም  ሰኔ 29/2015 ዓ.ም በመገኘት ከጣቢያ አስተባባሪዎች ማግኘት ትችላላችሁ።

5. በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡

6. ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡

7. ፈተናውን በድጋሚ ለምትወስዱ ተመዛኞች ወደ ፈተና ጣቢያ ስትመጡ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) QR code የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጋችሁ መምጣት ይኖርባችኋል።

ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት ተቋም ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ የማትችሉ መሆኑን እያሳሰብን ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118275936/952 መደወል ይቻላል፡፡
4.9K viewsedited  07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 10:57:42
መረጃ
የአማራ ክልልን አጠቃላይ አሁናዊ እና የቀጣይ የፀጥታ ሁኔታን በተመለከተ ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በባህርዳር ከተማ ምክክር እየተደረገ ነው
የክልሉን አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታንና የቀጣይ አቅጣጫዎችን በተመለከተ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ ከዞን እስከ ክልል ያሉ ከፍተኛ የክልሉ የፖሊስ አመራሮ፣የክልሉ የአድማ መከላከላ ኃላፊዎች፣የፌደራል ፓሊስና የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
የምክክር መድረኩም የክልሉን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።
4.7K views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 13:25:13 የጠሚ አብይ አህመድ ዝግ ስብስባ ዝርዝር መረጃ ፤ አበባውም ብርሃኑም አልቀረላቸውም ፤ እስክንድር ነጋ









6.6K viewsedited  10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 22:22:24
ከንቲባው ከአዞ ጋር ጋብቻ ፈፀመ

በደቡባዊ ሜክሲኮ የምትገኝ ትንሽ ከተማ ሳን ፔድሮ ሁአሜሉላ ከንቲባ አንዲት ሴት አዞ ለዘመናት በዘለቀው የአምልኮ ሥርዓት መሰረት ትዳር መሥርተዋል ይህም ለህዝባቸው መልካም ዕድል ለማምጣት ነው። "እርስ በርሳችን ስለምንዋደድ ሃላፊነት እቀበላለሁ፣ ያለፍቅር ትዳር መመሥረት አይቻልም›› ብሏል በጋብቻ ስነ ስርዓቱ ወቅት።
7.1K views19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 22:17:02
ሰሞኑን በወለጋ ሆሮጉደሩ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች እና በኦነግ ሸኔ መካከል ሀይለኛ ጦርነት እየተካሄደ ነው። በርካታ የሸኔ መሪዎች ተማርከዋል። እርምጃ የተወሰደባቸው እጅግ ብዙ ናቸው።

@esatchannal
6.7K views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 22:30:54 የችሎት ዜና!

ጋዜጠኞቹ መስከረም አበራና ጎበዜ ሲሳይን ጨምሮ በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ችሎት ለህዝብ ክፍት እንዲደረግ ታዘዘ

በአማራ ክልል ከልዩ ሀይል መፍረስና ፋኖን ትጥቅ ማስፈታት ጋር ተያይዞ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረዋል ተብለው ለእስር የተዳረጉ በአማራ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ምሁራን ዛሬ ሰኔ 5/2015 ዓ/ም ከሰዓት በኋላ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።ችሎቱ ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው አቃቤ ህግ በእያንዳንዳቸው ተከሳሾች ላይ በሬጅስትራር በኩል የተረጋገጠ ክስ እንዲያቀርብ ነበር።

ሆኖም አቃቤ ህግ የተረጋገጠ ክስ ለሬጅስትራር ሰጥቻለሁ ቢልም ሬጅስትራር ግን ሊደርስልኝ የቻለው የ13 ተከሳሽ ክስ ብቻ ነው የሚል ምላሽ ሰጥቷል።በዚህም አቃቤ ህግ ባሉበትና በሌሉበት በሚል ክስ ከመሰረተባቸው 51 ተጠርጣሪዎች መካከል ለአስራ ሶስቱ የክስ ቻርጅ እንደተሰጣቸው ሮሃ ቲቪ በችሎት ተገኝታ ተከታትላለች።
በዚህ ላይ አስተያየት የሰጡት የተከሳሽ ጠበቆችም " የአስራ ሶስቱ ተከሳሾች ጉዳይ መታየት ይችላል ችግር የለብንም " ብለዋል።

ለችሎቱ የሰብዓዊ መብት አያያዛቸውን በተመለከተ ለችሎቱ አስተያየት የሰጡት ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው በበኩላቸው " ዶክመንተሪ ተሰርቶብን ስማችን የጠፋ የፖለቲካ እስረኞች ስለሆንን  ችሎቱ ለቤተሰቦቻችን በተለይም ለአማራ ህዝብ ክፍት ተደርጎ በሰፊ አዳራሽ እንዲታይልን" ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በበኩሉ "ሌላ ቦታ የተሰደብነውና የተደበደብነው  ሳያንስ በችሎት አዳራሽ ፊት በፖሊሶች እንሰደባለን፣ ከጠበቆቻችን ጋር እንዳናወራ እንደረጋለን" ብሏል።

ዶ/ር መሰረት ቀለመወርቅ ደግሞ "የደረሰብንን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አቅርበን ነበር አሁን ግን የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ወደ መደበኛ ችሎት ስለተቀየረ ምን ላይ እንዳለ አናውቅም ፣ ከምን እንደደረሰ ግልፅ ይደረግልን" ሲሉ ጠይቀዋል።47ኛ ተከሳሽ ማስረሻ እንየው " በህግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት ሰውነቴ ውስጥ የቀረ ጥይት አለ ፣እንዳልታከም ተደርጌያለሁ ፣በቀጠሮዬ ቀንም ህክምና እንዳልቀርብ ተደረወጌያለሁ፣ በዚህም ለ75 ቀናት ገላዬን እንኳን መታጠብ አልቻልኩም " ብሏል ለችሎቱ።

ችሎቱም ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይና ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ላቀረቡት "ጉዳያችን በክፍት አዳራሽ ይታይ" ጥያቄ በሰጠው ምላሽ በቀጣይ ጉዳያቸው በትልቅ አዳራሽ እንዲታይና ለህዝብ ክፍት እንዲሆን አዟል።በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ በኢሰመኮ  እንዲጣሩ ውሳኔ የተሰጠባቸውን መዝገቦች እኛ እናጣራለን ብሏል የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት መደበኛ ችሎት።

ዶክመንተሪ ሰርተው ተጠርጣሪዎቹ በህግ ፊት ነፃ ሆኖ የመታየት መብታቸውን ያሳጡ የተባሉት የመንግስት ሚዲያዎች በስም የተጠሩ ሲሆን ፣ ይህንንም ጉዳይ እንደሚያጣራ ነው  ችሎቱ ያሳወቀው።አቃቤ ህግ ግን "ዶክመንተሪ የሰራው የጋራ ግብረሃይሉ ነው እኔን አይመለከተኝም" ብሏል።

"ለአስራ ሶስቱ ተከሳሾች የቀረበው ክስና የሰነድ ማስረጃን በተመለከተ  ሃላፊነቱን የወሰደው አቃቤ ህግ ስምና ፊርማ የለም ፣ሃላፊነት የሚወስድ አካል ያስፈልጋል " ሲሉም የተከሳሽ ጠበቆች ጠይቀዋል።
አቃቤ ህግም" ሃላፊነቱን የሚወስደው ፍትህ ሚኒስቴር ነው ፣ የፍትህ ሚኒስቴር ማህተም እስካለ ድረስ ሃላፊነቱን የሚወስደው ተቋሙ ነው "የሚል ምላሽ ሰጥቷል።የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዚህና በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ዙሪያ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ብይን ለመስጠት ለሰኔ 9/2015 ቀጠሮ ሰጥቷል።

      (ሮሃ ሚዲያ )


@esatchannal
1.9K viewsedited  19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 20:25:18 ፍኖተ ሰላም ዛሬ አለመረጋጋት እንደነበር ተነግሯል።በንፁሃን ላይ ጥይት የተኮሱ የፀጥታ ኃይሎች አሉበት በሚል ወጣቶች ሰመሪያ ሆቴልን ማውደማቸው ተሰምቷል። በደንበጫ አካባቢም ወጣቶች መንገድ በመዝጋት የተቃውሞ ድምፅ ሲያሰሙ እንደነበር የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።

@esatchannal
3.1K viewsedited  17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 20:25:18 የገዥው ፓርቲ ብልጽግና ማዕከላዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ክልል ተቀያይረው ክልል አቀፍ የአመራር ውይይት ማካሄድ ጀምረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ወደ ሀዋሳ ተጉዘው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልልን የአመራሮች ወይይት እየመሩ ነው፡፡

የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳደር ርስቱ ይርዳው ወደ ባህር ዳር ተጉዘው የአማራ ክልል አመራሮችን ውይይት እየመሩ ነው፡፡

የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ኡመር የሲዳማ ክልል የአመራሮች ውይይትን እየመሩ ሲሆን ሌሎቹ ነገ ይጀመራሉ ተብሏል።

@esatchannal
3.1K viewsedited  17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 20:20:54
ተፈቷል

የ"ጉማ አዋርድ" አዘጋጅ ዮናስ ብርሃነ አርብ ምሽት ሰኔ 2 ቀን 2015 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል ከተካሄደው የሽልማት ሥነ ስርዓት በኋላ በመንግሥት የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ሥር የሰነበተ ሲሆን ዛሬ ረፋድ ከእስር መፈታቱ ታውቋል።

@esatchannal
3.0K viewsedited  17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ