Get Mystery Box with random crypto!

ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)

የቴሌግራም ቻናል አርማ esatchannal — ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)
የቴሌግራም ቻናል አርማ esatchannal — ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)
የሰርጥ አድራሻ: @esatchannal
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.98K
የሰርጥ መግለጫ

አዳዲስ ወሬዎችን ዜናዎችን ማግኝት ከፈለጉ እኛን ይቀላቀሉ ለወዳጅ ዘመዶ #share

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-07-21 15:58:38 ሰበር ዜና-መከላከያ ማዘዣውን ቀየረ/የአማራ ክልል ም/ቤት ታመሰ












8.5K viewsedited  12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 14:54:24
መቀሌ ዩኒቨርስቲ
#በትግራይ ክልል የሚገኘው "መቐለ ዩንቨርሲቲ" ለተማሪዎቹ ጥሪ አደረገ
የመቐለ ዩንቨርሲቲ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል ከታች የተዘረዘሩትን ተማሪዎቹን ሐምሌ 26 እና 27/2015 በአካል ተገኝተው ይመዝገቡ ዘንድ ጥሪ አድርጓል።
*በዚህም መሰረት
1. በ2013ዓ.ም ተመራቂ የነበሩ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች
2. የድህረ ምረቃ ተማሪዌች
3. የተከታታይ ትምህርትና የማታ ተማሪዎች እና
4. የሕክምና ትምህርት ክፍል ተማሪዎች የሆናቹህ የመቐለ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ሐምሌ 26 እና 27/2015 #በአካል ተገኝታቹህ መመዝገብ ይኖርባቹሃል።

*የምዝገባ ቦታ ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ!
@esatchannal
8.3K viewsedited  11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 14:54:24
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዩክሬንን እንዲጎበኙ ግብዣ አቀረቡ
ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ በኹለትዮሽ የግንኙነት ጉዳዮች ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ዘለንስኪ ሩሲያ ከጥቁር ባህር የእህል ስምምነት መውጣቷን፣ ሕገ ወጥ የባህር ጉዞን መከልከሏን፣ የዩክሬንን ወደብ እና የኢነርጂ መሠረተ ልማት መጨፍጨፍን በተመለከተ፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ማብራሪያ መስጠታቸው ተገልጿል፡፡

ዩክሬን በጥቁር ባህር የእህል ስምምነት ወደ 300 ሺሕ ቶን የሚጠጋ እህል ለኢትዮጵያ ማቅረቧን የገለጹም ሲሆን፤ በተጨማሪም ሌላ 90 ሺሕ ቶን እህል በሰብአዊ ድጋፍ መልክ ማቅረቧንም ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ዩክሬን ለአለም አቀፍ የምግብ ዋስትና መሆኗን ለመቀጠል ዝግጁ መሆኗን የገለጹም ሲሆን፤ ከኢትዮጵያ ጋር በጸጥታ፣ በዲጂታይዜሽን እና የመሳሰሉት የኹለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት አፅንኦት ሰጥተዋል።

አክለውም ከአፍሪካ አገራት ጋር የውይይት መድረክ መፍጠር እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል።
"የኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ ህብረት፣ የመላው አፍሪካ ድምጽ ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው" ሲሉም ዘለንስኪ ተናግረዋል።

ኹለቱ መሪዎች በዓለም አቀፉ የሰላም ጉባኤ ዝግጅት ዙሪያ የተወያዩም ሲሆን፤ ዘለንስኪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዩክሬንን እንዲጎበኙ ግብዣ ማቅረባቸውን የፕሬዳንቱ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በበኩላቸው በይፋዊ የቲውተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከቮሎድሚር ዘለንስኪ ጋር በኹለትዮሽ እና አለማቀፍ የጋራ ጉዳዮች እንዲሁም በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ሰላም ማምጣት በሚቻልበት መንገድ ላይ በስልክ መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡

@esatchannal
8.1K viewsedited  11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 21:41:55
ኢቢሲ በጉማ አዋርድ ላይ ግንባሯን በጥይት መመታቷንና አፏን በሽቦ መለጎሟን በሚያሳይ ሜካፕ የቀረበችውን ፍላጎት አብርሃምን ከስራ አገደ
ሰኔ 2/2015 ምሽት በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በተካሄደው 9ኛው የጉማ ሽልማት ላይ የወገኗን መታፈን በሜካፕ ያሳየችው የቴሌቭዥን ፕሮግራም አዘጋጇና ታዋቂ ቲክቶከሯ ፍላጎት አብርሃም/የልጅ ማኛ/ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢቢሲ/ ከነበራት የኢትዮጵያን አይዶል የዳኝነት ስራዋ ተሰናብታለች።
ፍላጎት ከዚህ በፊት በአትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን የተሰጥኦ ውድድር /ኢትዮጵያን አይዶል/ ላይ በዳኝነት ስራ ቀረፃዎችን ከውና እንዲሁም ከሚዲያው ጋር ውል ተዋውላ ነበር።
ይሁን እንጂ ተቋሙ አዲስ በገነባውና ነገ በሚያስመርቀው የሚዲያ ኮምፕሌክስ ህንፃ ዛሬ ምሽት በጀመረው የኢትዮጵያን አይዶል ውድድር ላይ በፍላጎት ቦታ ከዚህ ቀደም በውድድሩ የዳኝነት ስራ ላይ ያልነበረው አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ ተተክቷል።
ሚዲያው ፍላጎትን ከዚህ ስራዋ ያገደበትን ምክንያት በግልፅ ማወቅ ባይችሉም ፣ በጉማ አዋርድ ላይ በሜካፕ ባስተላለፈችው መልዕክት ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል

@esatchannal
2.3K views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 21:36:45
የሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድ ፓስት አስቸኳይ መግለጫ አውጥቷል።በዚህም መሰረት:—
ከነገ ማለትም ከሰኔ 28/2015 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ  ከምሽቱ 12:00 ስዓት ጀምሮ
ማንኛውም ተሽከርካሪ ይሁን የሰው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የተገደበ ነው

አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የምሽት ክለቦችን ጨምሮ ከምሽቱ 12 ስዓት  በኃላ  ምንም አይነት አገልግሎት አይሰጡም

እንዲሁም የከተማው ነዋሪ ለጸጥታ መዋቅሩ እገዛውንና ድጋፍ በማድረግ ከተማዋን ካለባት ከፍተኛ የጸጥታ ችግር  ልንታደጋት ይገባል ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊው አቶ አብዱ ሁሴን ከስራ ወጥተው መኪናቸው ውስጥ እንዳሉ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉን ከሰዓታት በፊት መዘገቤ ይታወሳል
@esatchannal
2.3K viewsedited  18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 21:36:45
የክርስቲያን ታደለ እና የገንዘብ ሚንስትሩ ፍጥጫ
“ለቤተ መንግስት ግንባታ የተጠየቀ በጀት የለም፤ እየጸደቀ ያለ በጀትም የለም” የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ
የፌደራል መንግስት “ለአዲስ ቤተ መንግስት ግንባታ ያቀረበው የበጀት ጥያቄም ሆነ እያጸደቀ ያለው በጀት አለመኖሩን” የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ፡፡ አቶ አህመድ ይህንን የተናገሩት ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 27፤ 2015 በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው፡፡
በዛሬው መደበኛ ስብሰባ የፌደራል መንግስት ባቀረበው 2016 በጀት ላይ ከምክር ቤቱ የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም ከሌሎች የምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች የገንዘብ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ስብሰባ ላይ ከተነሱ ጥያቄዎች ውስጥ “ለቤተመንግስት እና ገበታ ለሀገር” ፕሮጀክቶች “እየተሰበሰበ ነው” የተባለን “500 ቢሊዮን ብር” የተመለከተው ይገኝበታል፡፡

ይህንን ጥያቄ ያነሱት የተቃዋሚው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባል የሆኑት አቶ አበባው ደሳለው፤ የገንዘብ አሰባሰቡ “የመንግስትን አሰራር እና መመሪያ” ተከትሎ እየተፈጸመ ነው ወይ ብለዋል፡፡ እኚሁ የፓርላማ አባል፤ “ይህ ብር የመንግስት ቋት ውስጥ አለ ወይ?” ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ለዚህ ጥያቄ የተወሰነ ማብራሪያ እየሰጡ ባሉበት ወቅት ከሌላው የአብን የፓርላማ አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ ተቋርጧል፡፡ “የስነ ስርዓት ጥያቄ” ያነሱት አቶ ክርስቲያን፤ የገንዘብ ሚኒስትሩ የሚሰጡት ምላሽ የምክር ቤቱን “የህግ እና የስነ ስርዓት ጉዳዮችን የጣሰ” እንደሆነ ገልጸው “እርምት እንዲደረግ” ጠይቀዋል፡፡
ethiopianinsider እንደዘገበው
2.2K views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 21:33:53
በበረራ ላይ የአውሮፕላን በር ለመከፍት ግብግብ

ብሪታኒያዊው ቦክሰኛ እየበረረ ያለ አውሮፕላን በር ለመክፈት በሚል ከበረራ አስተናጋጆችና ከተሳፋሪዎች ጋር ግብግብ ፈጥሯል።

ሆኖም ግን ከተሳፋሪዎች መካከል የተወሰኑት ተነስተው ተግበሩን በጉልበት ሊያስቆሙት ችለዋል። ቦክሰኛው አውሮፕላኑ እንዳይከፈት ያደረጉ ሰዎች ጀግና ተብለው ተወድሰዋል።

@esatchannal
2.2K viewsedited  18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 21:33:53 ሰበር አሳዛኝ ነው
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አብዱ ዛሬ አመሻሹን በስራ ቦታው አቅራቢያ መገደሉን ምንጮች ገልፀዋል።
ከስራ ሲወጣ መኪናው ውስጥ እንዳለ ነው 11 ሰዓት አካባቢ የተገደለው።

@esatchannal
2.2K viewsedited  18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 15:08:07 እስከ 40 ሺሕ የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች ተገድለዋል ተባለ

ማክሰኞ ሰኔ 27 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የመንግሥት ለውጥ ከተደረገበት 2010 ወዲህ ባሉት ዓመታት ከ25 ሺሕ እስከ 40 ሺሕ የሚገመቱ የአማራ ተወላጆች በአክራሪ ብሔርተኞች መገደላቸውን ካውንተር ፓንች በድህረ ገጹ አስነብቧል።

ዘገባው አብዛኞቹ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በሚል በሚጠራው እና በመንግሥት “ኦነግ ሸኔ” ተብሎ በተፈረጀው ኃይል የተገደሉ መሆናቸውን መገለጹን  ከድህረ ገጹ ዘገባ ተመልክቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም፤ ከአምስት እስከ ሰባት ሚሊዮን የሚደርሱ ዜጎች በየጊዜው በሚፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው ነው የተገለጸው።

እንዲሁም በአገሪቱ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ከጊዜ ወደ ጊዜ አደጋ ውስጥ እየገባ ነው የተባለ ሲሆን፤ የመሰበሰብ፣ የሚዲያ ነጻነት እና ሌሎች ተያያዥ ዴሞክራሲያዊ መብቶች አደጋ ውስጥ መግባታቸው ተጠቅሷል።

በዚህም ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ የአገር ውስጥ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ በግልጽ የሚናገሩ ጋዜጠኞች እና የግል የሚዲያ ተቋማት በነጻነት የመናገርና የመስራት መብታቸውን አጥተዋል ሲል የካውንተር ፓንች ዘገባ አመላክቷል።

ዘገባው መሰረቱን በአሜሪካ ያደረገ “ፍሪደም ሃውስ” የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅትን መረጃ ጠቅሶ፤ በኢትዮጵያ በስፋት መንግሥትን የሚተቹ አካላት ከእውቅናቸው ውጭ በሆነ መንገድ በመንግሥት የደህንነት አካላት በእጅ ስልካቸው ላይ ሳይቀር ሚስጥራዊ ክትትል እንደሚደረግባቸው ጠቁሟል።

በአገሪቱ የዘፈቀደ እስራት በተደጋጋሚ እንደሚፈጸም በመጥቀስም፤ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ አክቲቪስቶች እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሠራተኞች ከመኖሪያ ቤታቸው፣ ከሥራ ቦታቸው ወይም ከመንገድ ላይ  ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በደህንነቶች ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ እንደሚወሰዱመወ ተገልጿል።

በአገሪቱ ሥር የሰደደ ሙስና መኖሩን የጠቀሰው ዘገባው፤ ገንዝብ ተቀብለው ፍርድ የሚያጣምሙ ዳኞች ላይ ሳይቀር ያለው ተጠያቂነትም እምብዛም ነው ብሏል።

የጋዜጠኞች መብት ተማጋች ሲፒጄ በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች ነጻነት አሳፋሪ ገጽታ እንዳለው በመጠቆም፤ ባለስልጣናት የታሰሩትን ጋዜጠኞች በሙሉ ሊለቁ እንደሚገባና እስር ቤት ውስጥ በነበሩበት ወቅት በደል ወይም ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል የሚለውን መመርመር ብሎም ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚገባቸው ማሳሰቡ ይታወሳል።

አብዛኛው የአገሪቱ ሕዝብ ትልቅ ተስፋ ጥሎበት የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስተዳደር፣ ቀስ በቀስ ራሱን ወደ አምባገነናዊ ስርዓት እየለወጠ ነው ሲልም ካውንተር ፓንች በዘገባው አመላክቷል።

@esatchannal
4.4K viewsedited  12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 12:46:09 ጀነራሎቹ ስብሰባውን ረግጠው ቀሩ ፡ አብይ “ሰላም ከፈለጋቹህ ገዳን ተቀበሉ” ፡ የአብይ ወዳጅ ኢትዮጲያ ፈርሳለች









4.7K viewsedited  09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ