2022-07-15 14:43:30
በም/ቤቱ እራሳቸውን የተከላከሉት ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ !
" እኔ መጀመሪያ ማንሳት የምፈልገው ፤ መጀመሪያ ከግል ስብእናዬ መነሳት ፈልጋለሁ እኔ እስከማስበው ድረስ ምስኪኑ ህዝብ ቆጥቦ ቤት እንዲያገኝ ነው ፍላጎቴ ፤ ይሄ ከነበረኝ ስብእና እንፃር ሙስና የሚለው የሚገልፀኝ አይደለም።
ነገር ግን ድርጊቱ ተደርጎ ከሆነ እኔም አዝኛለሁ፤ ይሄም ጥልቅ የሆነ ምርመራ ተደርጎ ነገ ሁላችንም የምናየው ይሆናል።
ወደ ዋናው ሀሳቤ ስሄድ የአመራር ሚና ምድነው እኔ የቢሮ ኃላፊነ ነኝ፣ በተለይ የቢሮ ኃላፊ ስሆን አጠቃላይ strategic የሆነ direction ነው የምሰጠው።
እነዚህ የ routine የሆኑ ስራዎች ላይ ስራዎችን አልሰጥም። ነገር ግን በዚህ ሂደት ማየት የሚገባኝን የአመራር ክፍተቶችን እወስዳለሁ። እሱን የምክደው አይደለም።
እኔ በ Presentation ላይ በኢንሳ ተረጋገጠ አላልኩም። የቪድዮ ቅጂ ስላለ እሱን ማየት ይቻላል። ነገር ግን እንዴት ነበር የሚለውን ለዚህ ምክር ቤት ለታሪክ መቅረት ስላለበት ማቅረብ ይገባኛል።
መጀመሪያ ለዕጣው ዝግጁ ስናደርገው ከ9 ወር በፊት ነው ይሄ ስራ ያተጀመረው ይሄ ስራ ከተጀመረ በኃላ መጀመሪያ የተደረገው ለኢኖቬሽን ... እ "
የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ወ/ሮ ሱፌና አልከድር ፦
" የተከበሩ ዶ/ር ሙልቀን ... በሂደቱ ላይ ሳይሆን "
ዶ/ር ሙሉቀን ፦
" አይደለም ሀሳቤን ... "
የም/ቤቱ አፈጉባኤ፦
" በቀረበው ላይ ብቻ አስተያየት ይስጡ "
ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ፦
" ገብቶኛል ክብርት አፈጉባኤ ... "
የም/ቤቱ አፈ ጉባኤ ፦
" እሱን ፍርድ ቤት የማያጣራው ጉዳይ ይሆናል "
ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ፦
" አይደለም፤ ይሄ ም/ቤትም... ለመደመጥም እንትን ልሁን ምክንያቱም ይሄ ምክር ቤትም ማወቅ የሚገባውን አካሄዱን ማወቅ ስለሚገባው ስላለበት ነው መናገር ያለብኝ ።
ስለዚህ በሂደቱ አስተያየት መስጠት ያለብኝ በዚህ መልክ ነው።
ሎተሪው ዕጣ ከመውጣቱ በፊት 2 ደብዳቤ በህዳር 17 /2014 በአብርሃም ተፈርሞ ለኢኖቬሽን ሚኒስቴር እና ለኢንሳ የሞያዊ ድጋፍ ኣስፈላጊድን እንድታደርጉ ብለን ፅፈናል።
የኢኖቬሽን ሚኒስቴር በታህሳስ 26/2014 በደብዳቤ ምክረ ሀሳብ ሰጥቶናል። ከዛ በምክረ ሀሳቡ መሰረት የሚስተካከለውን አስተካክለናል። ኢንሳን በተመለከተ ግን ምንም አይነት ነጥብ አልሰጠንም personally እንደውም ዶ/ር ሹመቴን አግኝቼ ለማውራት እባክህን...ክብርት ያስሚንም ስላለች ክብርት ያስሚንም ደውላለት እንደውም ፍቃደኛ ያልሆነበት ሁኔታ ነበር የነበረው። ዕጣው ከመውጣቱ በፊት የነበረው ሂደት ይሄው ነው።
ሰኔ 21 ቀን 2014 በአቶ ሽመልስ የተፃፈ ደብዳቤ ተወካይ ይመደብልን በተባለው ሰዓት ..."
የም/ቤቱ አፈጉባኤ፦
" በጣም ያሳጥሩልን "
ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ፦
" አሳጥራለሁ ግን ካልተሰማሁ at least ይሄ ምክር ቤት ይስማኝ ካዛ በኃላ ችግር የለውም ሌላውን ነገር ..."
የም/ቤቱ አፈጉባኤ፦
" ማለት ይሄ የተከበረው ምክር ቤት ይሄንን ከማጣራት ስልጣን የለውም፤ የማጣራት ስልጣን ያለው ፍትህ ሚኒስቴር ነው "
ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ፦
" ለታሪክ መቀመጥ ስላለበት እኔ ከግል ስብእናዬ ከከፈልኩት የፖለቲካ ዋጋ ካለኝ ነገር ይሄ ምክር ቤት understand አድርጎ ለታሪክ መቀመጥ ስላለበት ነው። ይሄን መናገር የፈለኩት።
ከይቅርታ ጋር ክብርት አፈጉባኤ ባያቋርጡኝ ብቀጥል። አጭር አጭር አድርጌ ልግለፅ።
ስለዚህ ሰኔ 21 ቀን በአቶ ሽመልስ በተፃፈው ደብዳቤ የዘርፉ ምክትል ኃላፊ ለሆኑት ለአቶ አብርሃም ደርሷቸዋል። "
የም/ቤቱ አፈጉባኤ፦
" አሁንም ላስቆሞት ነው። አልፈቅድም። ሁሉንም ዝርዝር እንዳያቀርቡልን አልፈቅድም "
ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ፦
" አጭር ነው ፤ ሀሳቤን ወይም ደቂቃ ይስጡኝና... "
የም/ቤቱ አፈ ጉባኤ፦
" ሀሳቡን አጭር አድርገው፣ የሚቃወሙትን ነገር ላይ ብቻ "
ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍታ፦
" ክብርት አፈ ጉባኤ የምቃወመው ይሄን ሀሳቤን ገለፅኩኝ በኃላ ነው "
የም/ቤቱ አፈ ጉባኤ፦
" ለማስቆም እየተገደድኩ ነው "
ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ፦
" እሺ በምን ልናገር ታዲያ ? "
የም/ቤቱ አፈጉባኤ፦
" በጣም በማሳጠር "
ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ፦
" እሺ፣ ችግር የለውም ! በጣም አሳጥራለሁ። የምክር ቤት አባላትን በጣም ይቅርታ ጠይቃለሁ። ማወቅ ስላለባችሁ ነው።
ሰኔ 21 ቀን በአቶ ሽመልስ የተፃፈው ደብዳቤ እኔ ሰኔ 21 ምናልባት በጊዜው አልነበርኩም በባለቤቴ ወሊድ ምክንያት በዚህ ሰዓት ዳታ ሲቀበሉ፣ እንዲህ ያለውን ደብዳቤ ሲፃፃፉም በጊዜው አልነበርኩም።
የኔ ምክትል የነበረው ግን ይሄንን ዳብዳቤ ተቀብሎ ባለሞያ ወክልሉልን ባለን መሰረት ለሶፍትዌር ዳይሬክተር ባለሞያ እንዲወክል ፅፏል።
ከዛም በድጋሚ አቶ ሽመልስ ሰኔ 21 የቤት መረጃ ለቢሯቹ የላክን መሆኑን ይላል። እዚህ ጋር አቶ ሽመልስ አጠቃላይ የቤት ምዝገባ ያተደረጉበትን፣ ዕጣ የሚወጣባቸውን አቶ ሽመልስ ልኳል።
እኔ በዛ ሰዓት ስላልነበርኩ ምክትሌ አቶ አብርሃም አሁንም ይሄንን ለሶፍትዌር ዳይሬክተሮች መርቶ ወደባለሞያው የገባበት ሁኔታ አለ።
ለምን ይሄን አነሳሁኝ ለሚለው ሁለት ነገር ነው።
አንደኛው ዕጣ ከመውጣቱ በፊት ክብርት ያስሚንም እንደውም እኔ አልነበርኩም ክብርት ያስሚን የእኔ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች ይዛ ቢሯችን መጥታ እዛ ስላልነበርኩኝ ያለውን ነገር ውይይት አድርጋ ሲስተሙ እንዴት ነበር ተብሎ display ተደርጎ ነበር እሱ በማየት ደረጃ እሳቸውም ስላሉ ይገልፁታል።
ሌላው ከ4 በላይ ሙከራ ተደርጓል የተባለው ምናልባት ክብርት ከንቲባ ባሉበት ሙከራ አድርገናል። ከዛም በኃላ ይሄ ኮምፒዩተር እኛ አዲስ ብለን ነው የሰጠነው። እንግዲህ ይሄ too በጣም technical እኔ የተማርኩት በሰላምና ደህንነት more of social science ነው። እኔ strategically በሆነ way ነው እንጂ መሥጠት ያለብኝ ምን አይነት algorithm ተጠቅሟል፣ behind የሰራውን ምን አይነት ሶፍትዌር ይጫን የሚልውን ነገር እኔ አላውቀውም።
ነገር ግን ይሄ ኮምፒዩተር አዲስ ነው። ከግዢ የሰጠነው ነው። ሰጠን ባለሞያው ይጠቀምበት ይሄን ያድርግበት እኔ እንደ አመራርነቴ ወርጄ የማየት role አለኝ ብዬ አላስብም።
ዕጣው ከመውጣቱ ለፊት ማታ ታሸገ፣ ከታሸገ በኃላ ታዛቢ ባለበት ታሸገ፣ ምንም ዳታ እንደሌለው ታይቶ ታሸገ። እኔ ኮምፒዩተሩ ጋርም ቀርቤ አላውቅም። ከዛ በነገታው መጡ ክብርት ያስሚን ባለችበት ሌላም ታዛቢ ባለበት በሩ ተከፍቶ ተገባ ካዛ ኮምፒዩተሩ ታየ ከዛም ክብርት ከንቲባ ባለችበት ያሬድ የሚባል ባለሞያ በቴክኖሎጂ የታወቀ ነው እሱ ይየው ተብሎ መጣ ያሬድ የሚባለው ሰውዬ ክሊክ አድርጎ ያለውን ነገር ጠቅላላ አየ መሄድ ይችላል ብሎ እዛው confirmation ሰጠን ምክንያቱም ክብርት ያስሚንም ስላሉ በዚህ መሰረት ወደ እጣው መጣ።
ወደ ዕጣው ሢመጣ presentation ተዘጋጀ፣ ከዛም ለቢሮው ይመጥናል አንተ ብታቀርበው ተብዬ እንዳቀርብ ተደረገ፤ ከዛ ውጭ Presentation ላይ ያቀረብኩት ደግሞ አንዱ ነገር ጠቅላላ የተሰጠኝን ሀሳብ ነው።
ለምሳሌ ከታች ባለሞያ አለ ከባለሞያው በላይ ዳይሬክተር አለ፣ ከዳይሬክተር በኃላ..."
ዶ/ር ሙሉቀን ይህንን እየተናገሩ እያሉ በቀጥታ በአዲስ ቴሌቪዥን ለህዝብ ሲሰራጭ የነበረው ንግግር ተቋርጧል። በኃላም ያለመከሰስ ማብታቸው ተነስቷል።
@esatchannal
1.8K viewsedited 11:43