Get Mystery Box with random crypto!

ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)

የቴሌግራም ቻናል አርማ esatchannal — ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)
የቴሌግራም ቻናል አርማ esatchannal — ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)
የሰርጥ አድራሻ: @esatchannal
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.98K
የሰርጥ መግለጫ

አዳዲስ ወሬዎችን ዜናዎችን ማግኝት ከፈለጉ እኛን ይቀላቀሉ ለወዳጅ ዘመዶ #share

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 141

2022-07-14 17:52:10 ሩስያና ዩክሬን እህል ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ከስምምነት ይደርሳሉ የሚል ተስፋ እንዳላቸው የተመድ ዋና ጸሀፊ አንቶንዮ ጉተሬሽ ተናገሩ።

ጉተሬሽ የሩስያና የዩክሬን ተደራዳሪዎች ከፈጠነ በሚቀጥለው ሳምንት በጥቁር ባህር በኩል የእህል ንግድ በነጻነት እንዲካሄድ የሚያስችል ይፋ ስምምነት ላይ ሊደርሱ ይችላሉ ብለው ተስፋ ያደርጋሉ።የእህል አቅርቦት እገዳን ለመፍታት በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ትላንት ኢስታንቡል ቱርክ ውስጥ ፊት ለፊት የተነጋገሩት ሁለቱ ሀገራት በመጪው ሳምንት የመጨረሻ ስምምነት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የተመድና ቱርክ አስታውቀዋል። የሩስያና የዩክሬን ተደራዳሪዎች ባካሄዱት ንግግር የቱርክና የተመድ ተወካዮችም ተገኝተዋል።

ከዩክሬንና ከሩስያም እህልና ማዳበሪያ በመርከብ አጓጉዞ ለዓለም ገበያ ለማቅረብ የተመድ ባወጣው እቅድ ሁለቱ ወገኖች በሰፊው መስማማታቸውንም ጉተሬሽ ተናግረዋል።የስብሰባው አስተናጋጅ ቱርክ ሁለቱ ወገኖች በጥቁር ባህር ወደቦች የእህልና የማዳበሪያ ዝውውር ደኅንነትን በማረጋገጥ ጉዳዮች ላይ መስማማታቸውን አስታውቃለች።22 ሚሊዮን ቶን እንደሚደርስ የሚገመት እህል ዩክሬን ጎተራዎች ውስጥ ይገኛል።በዩጦርነቱ ምክንያት የእህል አቅርቦት መቆሙ በርካታ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን ህዝቦች አደጋ ላይ ጥሏል።

በዓለማችን የናረው የምግብ ዋጋም 181 ሚሊዮን ሰዎችን ለረሀብ ያጋልጣል የሚል ስጋት አሳድሯል።ኪቭ ሞስኮን የእህል አቅርቦቱን በማገድና እህል በመስረቅ ከሳለች።ይህን ያስተባበለችው ሩስያ ኪቭ ከወደቦቿ እህል በመርከብ ለመጓጓዝ ገደብ የለባትም ብላለች።ሆኖም ዩክሬንና ሩስያ የሚዋሰኑት ጥቁር ባህር ላይ ሁለቱም ሀገራት ፈንጂዎች ጥለዋል።በእቅድ መሠረት እህል ለማጓጓዝ የታሰበው ፈንጂዎች ያሉበትን አካባቢዎች በመተው የተወሰኑ መተላላፊያዎችን በመጠቀም ነው።

[DW]
@esatchannal
1.9K viewsedited  14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:04:10 አስተዳደሩ ባወጣው የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ በማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አመራሮችና ሰራተኞችን ዝርዝር ይፋ አደረገ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ እና ከቤቶች ቢሮ በማጭበርበር ወንጀል የተጠረጠሩ አመራሮችና ሰራተኞችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡

የተጠረጠሩ አመራሮችና ሰራተኞች ስም ዝርዝርም እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

1. ዶ/ር ሙሉቀን ሃብቱ- የቢሮ ሃላፊ፣ ከሃላፊነቱ የተነሳ

2. አብርሀም ሰርሞሎ -የዘርፉ ምክትል ቢሮ ሃላፊ

3.መብራቱ ወልደኪዳን -ዳይሬክተር

4. ሀብታሙ ከበደ -ሶፍትዌር ባለሙያ

5. ዬሴፍ ሙላት-ሶፍትዌር ባለሙያ

6. ጌታቸው በሪሁን -ሶፍትዌር ባለሙያ

7. ቃሲም ከድር- ሶፍትዌር ባለሙያ

8. ስጦታው ግዛቸው- ሶፍትዌሩን ያለማ

9. ባየልኝ እረታ - ሶፍትዌር ተቆጣጣሪ

10. ሚኪያስ ቶሌራ- የቤቶች ኢንፎሜሽን ና ቴክኖሎጂ ባለሙያ

11.ኩምሳ ቶላ የቤቶች ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳሬክተር

@Esatchannal
2.2K viewsedited  19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:04:10 የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ የተከሰሱበትን ወንጀል ፖሊስ ይፋ አደረገ


የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ የተከሰሱት፥ከኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንደዴቭሎፕመንት አሶሴሸን ዳይሬክተር የማነ ወ/ማሪያምና ከሌሎችም ሰራተኞች ጋር በመመሳጠር በተረጂዎች ስም ለኦሶሲዬሽኑ ከተሰጠው የእርዳታ እህልና የምግብ ቁሳቁስ ጋር በተያያዘ የተፈፀመ የሙስና እና ህገ ወጥ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የሙስና ወንጀል መሆኑን ፖሊስ በላከውመረጃ አስታውቋል።

ፖሊስ ባደረገው የማጣራት ስራ መሰረት ያገኘውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች እንደሚከተለው ቀርቧል።

በፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ዐቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል እና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ቀድሞ ሲከናወን በቆየው የምርመራ ስራ እንዳረጋገጥነው የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንደ ዴቭሎፕመንት አሶሴሸን ዳይሬክተር የማነ ወ/ማሪያም እና ከሌሎችም ሰራተኞች ጋር ያልተገባ የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር በሺዎች በሚቆጠሩ በሌሉ ተረጂዎችና ስም እንዲሁም የተረጂዎችን ቁጥር በማጋነን ለበርካታ ጊዜያት እህልና የምግብ ቁሳቁሶች ከኮሚሽኑ መጋዘን ካወጡ በኃላ እህሉ ለተረጂዎች ሳይደርስ ለዱቄት ፋብሪካዎችና ለሌሎች ግለሰቦች በሚሊዮን ብሮች በመሸጥ ህገወጥ ጥቅም ሲያገኙ የነበረ መሆኑን፣ ለዚህም ስራቸው አቶ ምትኩ ካሳ በቤተሰቦቻቸው ስም ከሌልሻዳይ ድርጅት በተለያዩ ጊዜያት በሚሊየን ብር የሚገመት ጥቅም ያገኙ እንደነበረ በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡
 
ሙሉ መግለጫ ከፋይሉ ጋር ተይያዟል...

@esatchannal
2.0K viewsedited  19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:04:09 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ሀምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሰጡት መግለጫ

በመግለጫውም ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ፤ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት የአጣሪ ቡድን መሪ አቶ በሀይሉ አዱኛ መግለጫውን በጋራ ሰጥተዋል፡፡

በዚህ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ ከኢንሳ፤ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፤ እንዲሁም ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አጣሪ ቡድን እንዲቋቋም ተደርጎ ወደ ማጣራት ስራ በመግባት ሲጣራ ቆይቶ በዛሬው እለት በጋዜጣዊ መግለጫው ይፋ ተደርጓል፡፡

በመግለጫው የአስተዳደሩ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች ቀጥሎ ቀርበዋል፦

በጋዜጣዊ መግለጫው ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት የጋራ መኖርያ ቤት እጣ በማውጣት ሂደት ባጋጠመን ችግር ህዝቡንም ከተማ አስተዳደሩንም ያሳዘነ ድርጊት መፈፀሙን አንስተዋል፡፡

በዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ ህብረተሰቡ በትእግስት በመጠበቅ እንዲሁም የጀመርነውን ጥረት ከጎናችን በመቆም ላሳየው ጥረት ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለህዝባችን ቃል በገባነው መሰረት ችግር ቢያጋጥም እንኳን በቀጥታ ኦዲት እናደርጋለን ብለን በገለፅነው መሰረት ጥቆማ ስለደረሰ ጊዜ ሳንሰጥ በሚመለከታቸው አካላት የማጣራት ስራ እንዲጀመር አስደርገናል፡፡

የቴክኖሎጂ ውንብድና አጋጥሞናል፡ አመራር የመራው ውንብዳ ነው፡፡ በዚህ ሂደት የቤት ስርቆት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፍላጎት ጭምር መግለፅ ይቻላል ብለዋል፡፡
የዚህ ስራ ሌላው አላማ መንግስት ህዝብን ማገልገል ብቃት የለውም የሚል ገፅታ ለመፍጠርና ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ እንዲያምፅ ለማድረግ በማሰብ ነው በማለት ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል፡፡

በዚህ ሂደት ችግር እንዳጋጠመን ማጣራት መጀመራችን ህዝብን ሃብት መታደግ እንድንችል አድርጎናል፡፡ ህዝቡን መታደግ ችለናል፡፡

ህብረተሰቡም መብቱን ለማስጠበቅ ያደረግነውን ጥረት ተረድቶናል፡፡ እኛም ድሃውን ማህበረሰብ መታደግ በመቻላችን ያስደስተናል፡፡

የቀረበልን ሪፖርት በሚገባ ሲስተሙ ተቆጣጣሪ ጭምር እንዳለውና አስተማማኝ እንደነበረ ነበር፡፡ ይህንንም ለማመን ምክንያቶች ነበሩ፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት በዚህ ቡድን የለሙና ጥቅም ላይ የዋሉ ሲስተሞች ነበሩ፡፡

ማረጋገጫ ለማግኘት የተሄደበትና ተቋም ለተቋም የተደረጉ ግንኙነቶችም ችግር ነበረባቸው፡፡ ሰዎች ለሰዎች የተደረጉ ግንኙነቶች አይነት የተደረጉ ግንኙነቶችም መመልከት ተችሏል፡፡

ኢንሳ ማረጋገጫ ሰጥቶ እንደነበርም በወቅቱ ተገልፆ ነበር ነገር ግን ህጋዊ በሆነ ደብዳቤ ኢንሳ ያረጋገጠው እንዳለሆነ ታይቷል፡፡

ዳታው በሰዎች አጅ ለአምስት ቀን ያህል መቆየቱና ይህም የተከናወነው በሃላፊዎች ትእዛዝ እንደነበር ገልፀዋል

ነገር ግን የምዝገባው ዳታውን በቴሌግራም ጭምር ሲላላኩ እንደነበር በኋላ በምርመራ መታወቁን

በሂደቱም እጣ ቁጠባ ያቋረጡ ሰዎች ፤ቁጠባቸውን ከረሱበት ቦታ ጭምር እጣ እንዲወጣላቸው መደረጉን

የማጣራት ሂደቱን እጣ የወጣ እለት ከሰዓታት በኋላ መጀመሩን ከንቲባ አዳነች ገልፀዋል፡፡

ይህ የማጣራት ሂደት ኢንሳ አራት ባለሙያዎች መወከሉንና ከዚህ በተጨማሪም ከሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ከብሄራዊ ደህንነት የተዋቀረ ኮሚቴ በኢንሳ አስተባባሪነት ስራውን ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡

ቴክኖሎጂዎች ለመጠቀም ያደረግነውን ጥረት ወደፊትም አጠናክረን እንቀጥላለን፤ ቴክኖሎጂዎችን የሚያለማው ሰው ቢሆንም ወደፊት በረቀቀ የሙያ ስልት እጣ አወጣጡን ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን እናድርጋለን

እዚህ በግልፅ ማንሳት የምንፈልገው በወቅቱ የተሰጠን ማብራርያ ከእውነቱ የራቀ መሆኑን በባለሙያዎች ጭምር ተረጋግጧል፡፡

ባለሙያዎችና አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ እንዲሁም አንድ ሃላፊና አንድ ምክትል ሃላፊ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡

ሌሎች እርምጃዎች እንደ ሚዛኑ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ አሁንም ቆራጥ አቋሙ ህዝቡን መብት ማስከበር መሆኑን ይህንን ቤት ለህዝብ ለማቅረብ ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ጭምር የጎደለውን መሰረተ ልማት በሟሟላት ለህዝብ ማድረሱን

በፍትሃዊነት ህዝብን ሃብት ለማድረስና የኋላ የኮንዶሚኒየም መጥፎ ታሪክን ላለመድገም ከፍተኛ ፍላጎት ነበረን፡፡ አሁንም ይቀጥላል፡፡

አሁንም ተቋም ግንባታ አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

ስለሆነም በዚህ ሁሉ ችግር እና ሂደት የወጣን እጣ ተዓማኒነት ስለሌለው እጣው ሙሉ ለሙሉ ውድቅ እንዲሆን አድርገናል፡፡

AMN

@esatchannal
1.9K viewsedited  19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:04:09
የጋራ መኖሪያ ቤት ላይ የወጣው እጣ ውድቅ ተደረገ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ ውድቅ አደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ25 ሺሕ 491 ያወጣው የ20/80 እና 40/6 ላይ እጣ የወጣበት ሲስተም ላይ የተአማኒነት ጉድለት እንደነበር በመረጋገጡ ነው የወጣውን ዕጣ ውድቅ ያደረገው፡፡

ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ከዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጥቆማዎች በመቅረባቸው የኦዲት ሥራ የጀመረው ከተማ አስተዳደሩ በባንክ የተላከውና ለእጣ እንዲውል ወደ ኮምፒዩተር የተጫነው ዳታ ልዩነቶች መገኘታቸውን መግለጹ ይታወሳል::

@esatchannal
1.9K viewsedited  19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 11:58:29
የስሪላንካ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱን ለቀው ተሰደዱ!

የስሪላንካ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱን ለቀው ወደ ማልዴቪስ ተሰድደዋል።

በእስያዋ ስሪላንካ በተከሰተው የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ላለፉት ሳምንታት ህዝባዊ ተቃውሞ በመላ ሀገሪቱ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ፕሬዝዳንት ጎታብያ ራጃፓክሳ ስልጣን እንዲለቁ ሲጠይቁ የቆዩ ሲሆን በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ፕሬዝዳንቱ ስልጣን ለመልቀቅ ተገደዋል፡፡

ተቃዋሚዎች ባሳለፍነው ቅዳሜ በሀገሪቱ መዲና በሆነችው ኮሎምቦ ከተማ የሚገኘውን ቤተመንግስት የተቆጣጠሩ ሲሆን የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ድርጊቶችን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

ተቃውሞ የበረታባቸው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ራጃፓክሳም ወደ ጎረቤት ሀገር ማልዴቪስ እንደተሰደዱ ሮይተርስን ጠቅሶ አል አይን ዘግቧል፡፡

@esatchannal
2.3K viewsedited  08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ