Get Mystery Box with random crypto!

ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)

የቴሌግራም ቻናል አርማ esatchannal — ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)
የቴሌግራም ቻናል አርማ esatchannal — ኢሳት(ትኩስ ትኩስ ዜናዎች)
የሰርጥ አድራሻ: @esatchannal
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.98K
የሰርጥ መግለጫ

አዳዲስ ወሬዎችን ዜናዎችን ማግኝት ከፈለጉ እኛን ይቀላቀሉ ለወዳጅ ዘመዶ #share

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-07-22 16:46:58 ትግራይ
በትግራይ ክልል እንደ አዲስ ወታደራዊ ምልመላ ተጀምሯል። ትናንት በሽሬ እና አድዋ በርካታ ወጣቶች ተመልምለው በቅርቡ ወደ ወታደራዊ ስልጠና ትገባላችሁ ተብለው በጊዚያዊ ካምፕ አሰብስበው እንዲቀመጡ ተደርጓል።

@esatchannal
9.1K viewsedited  13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 16:46:58 በሰሜን ሸዋ ዞን መራኛ ልዩ ስሙ ዋሶ በርሀ በአካባቢው የፋኖ አባላት እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል ለ3 ሰዓት የቆየ ከፍተኛ ውጊያ እንደነበር ምንጮች ገልፀዋል። በዚህ ውጊያ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንም ተናግረዋል። በትናንትናው ዕለት ቀድም ብሎ ጠዋት አካባቢ በመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት ተፈፅሟል ተብሏል።

@esatchannal
8.8K viewsedited  13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 16:46:58 የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር "ክልሉን እንታደግ" ሲሉ ጥሪ አቀረቡ
ባልተለመደ ሁኔታ በላለፉት ሦስት ቀናት በዝግ የተካሄደው የአማራ ክልል ምክር ቤት፤ በክልሉ ወቅታዊ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ከአባላቱ ጠንካራ ጥያቄዎችን ማስተናገዱ ተሰምቷል፡፡

በምክር ቤቱ ሰብሰባ ላይ ጥያቄ ያነሱት የሕዝብ ተወካዮች፤ "የአማራን ሕዝብ አንገት ለማስደፋት ቀን ከሌሊት የሚሰሩ አካላት አሉ” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

አባላቱ ክልሉ አሁን ላይ የገጠመውን አለመረጋጋት ለመፍታት መጀመሪያ የክልሉ አስተዳደር መዋቅር ራሱን መፈተሸና ማስተካከል አለበትም ነው ያሉት።

የምክር ቤቱ አባላት አክለውም፤ "ክልሉ ያሉበትን መዋቅራዊ ችግሮች ካላስተካከለና ራሱን አስተካክሎ በግልጽ ካላወጣ፣ የሕዝቡን ጥያቄ መመለስ አይቻልም" ሲሉ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

በየአካባቢው የሚስተዋሉ ውጊያዎች የክልሉን ሕዝብ እያዳከሙ ነው ያሉት አባላቱ፤ የክልሉ መንግሥት መከላከያ ሠራዊት አስገብቶ ውጊያ እንዲደረግ መፍቀድ አልነበረበትም የሚል ትችትም አንስተዋል።

ከምክር ቤት በአባላቱ ጠንካራ ጥያቄዎች የቀረቡላቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡትም ምላሽ፤ “ክልሉን እንታደግ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

“ችግራችንን በራሳችን የመፍታት አቅም እንፍጠር” ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በየዞኑ ከምክር ቤት አባላት አምስት አምስት ሰው ተመርጦ የኃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራንና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች የተሳተፉበት ውይይት ያለምንም ገደብ እንዲደረግም ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ ያቀረቡት የውይይት ጥሪ በአስር ቀናት ውስጥ እንዲካሄድም ነው የጠየቁት። በውይይቱ የሚነሱ ጉዳዮች በወረዳ፣ በዞንና በክልል በየደረጃው መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጥረት እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል፡፡

አስተዳደራቸው ለሰላም አማራጭ ቅድሚያ በመሰጠት፤ በሽዋ፣ በወሎ፣ በጎጃምና በጎንደር ውይይት እንዲደረግ ዕድል መፍጠሩን አስታውሰዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ “እንታደገው” ያሉትና የሚመሩት ክልል፤ በተለይ የመከላከያ ሠራዊት በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከተሰማራ ጊዜ ጀምሮ በውጊያ፣ መንገድ በመዝጋት፣ በሕዝብ ተቃውሞና በመሳሰሉት ሁነቶች ውስጥ እያለፈ ነው፡፡

የመከላከያ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከአማራ ክልል የሰላም እጦት ጋር በተያየዘ በቅርቡ በሰጡት አስተያየት፤ “ክልሉ ፓራላይዝድ ሆኗል” ሲሉ መደመጣቸው የሚታወስ ነው፡፡

ፊልድ ማርሻሉ የአማራ ክልል አስተዳደር ሽባ ሆኗል የሚል ይዘት ያለው አስተያየት ከሰጡ በኋላ፤ የመከላከያ ሠራዊት በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር ውጊያ ውስጥ ገብቷል፡፡

በመንግሥት እና በታጣቂ ቡድኑ መካከል ያለው ግጭት፤ ገና ከጅምሩ በውይይትና በድርድር እንዲፈታ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች ጥሪ ሲያቀርቡ ቢቆዩም፣ አሁንም በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ውጊያዎች እየተካሄዱ ነው፡፡

@esatchannal
8.9K viewsedited  13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 11:52:20 የሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ የፀጥታ ም/ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ ይህ የወጣው ትናንት በአካባቢው የተፈጠረውን ጥቃት ተከትሎ ነው።
1. በማህበራዊ ሚዲያም ሆነ በሌሎች የመጠጥ ቤቶችና በማንኛውም ቦታና ሰዓት በህግ ዕውቅና ያልተሰጠው ሀይልን በማጀገን የወገንን ሀይል ፣ የመከላከያችንን፣ የሚሊሻ  የህዝባችንን ክብርና ሞራል የሚነካ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እና የአሉባልታ ወሬ በመንዛት ህዝባችንን ማሸበር ፍጹም የተከለከለ ነው፡፡ ይህንን በሚያደርግ ግለሰብም ይሁን ቡድን ላይ የፀጥታ ሀይሉ እርምጃ ይወስዳል፡፡

2. በከተማችን ውስጥ የትኛውም ቦታ በየትኛውም ሰዓት  ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ የከተማው ነዋሪም ሆነ ከሌላ አካባቢ የመጣ ግለሰብ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑ።

3/.ከተፈቀደላቸው ተሸከርካሪዎች ውጭ  ሞተር ከምሽቱ 12:00 ስዓት ፤ ባጃጅ ከምሽቱ 1:00 ስዓት፤ ሌሎች መኪኖች ደግሞ  ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን ይህን ተላልፎ በሚገኝ አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል፡፡

4/.ማንኛውም የከተማችንና የቀበሌ ነዋሪዎች
በወረዳና በቀበሌ ደረጃ የሚገኝ የፀጥታ አካል የሚሰጠውን ትዕዛዝ ተቀብሎ አካባቢያችሁን በሚጠብቅበት ስዓት ተገቢውን ትብብር የማድረግ ግዴታ አለበት።

5/. ማንኛውም በወረዳው ውስጥ የሚገኝ  ነዋሪ በግቢው፣ በሆቴሉ ወይም በማንኛውም የግል ቤት እና ድርጅቱ ያከራያቸውን፣ ግለሰቦችን በወጣው አስቸኳይ ጊዜያዊ አዋጅ መሰረት መከታተል አለበት።

6/. በከተማና በቀበሌዎች ውስጥ ስምሪት ከተሰጣቸው የመንግስት የፀጥታ አካላት ውጭ በማንኛውም ጊዜና
ቦታ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው

7/. ሁሉም የከተማችን ነዋሪ ፀጉረ ልውጥን መከታተል፣ መጠቆም እና ለህግ አካሉ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡

8/.ከኮማንድ ፖስቱ እውቅናና ፈቃድ ውጭ ስብሰባ ማድረግና የፀጥታ ቅስቀሳዎችን ማድረግ የተከለከለ ነው። ይህንን ሲያደርግ የተገኝ ማንኛውም አካል በህግ ተጠያቂ ይሆናል።

9/. ሁሉም በከተማና በገጠር የሚገኘው ነዋሪ ራሱንና አካባቢውን ስምሪት ከተሰጣቸው የፀጥታ አካላት ውጭ የሚጠበቅና ጥቆማ የመስጠት ሀላፊነትና የተዘረዘሩ ውሳኔዎችን በመፈፀም የወረዳችንን ብሎም በህዝባችን ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን የመጠበቅ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ስንል ከታላቅ አደራ ጋር እንጠይቃለን፡፡
የሚዳ ወረሞ ወረዳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ>>> ኮማንድ ፖስት

@esatchannal
8.7K viewsedited  08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 11:52:20 በጠለምትና አካባቢው በትግርኛ ቋንቋ የሚጠሩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ስያሜ ወደ አማርኛ ሊቀየር መሆኑ ተሰማ
በአማራ እና ትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚገኙና በትግርኛ ቋንቋ የሚጠሩ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ስያሜ ወደ አማርኛ ቋንቋ ሊቀየር መሆኑን አዲስ ማለዳ ከጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ሰምታለች።

ኮሚቴው በጠለምትና አካባቢው የሚገኙና በትግርኛ ቋንቋ ስያሜ ያላቸው ኹሉም ወረዳዎች፤ ቀበሌዎችና ጎጦችን የአማርኛ ስያሜ ሊሰጣቸው መሆኑን አመላክቷል።

በወቅቱ ክልሎች ሲመሰረቱ አካባቢው ወደ ትግራይ ክልል እንዲካለል በመደረጉ በአማርኛ ቋንቋ ይታወቅ የነበረው ስያሜያቸው ወደ ትግርኛ ቋንቋ እንዲቀየር ተደርጎ ቆይቷል ነው የተባለው።

ይህን ተከትሎም በአሁኑ ወቅት በጠለምትና አካባቢው የሚገኙ ወረዳዎችን፣ ቀበሌዎችንና ጎጦችን ስያሜ ለመቀየር እንቀስቃሴ መጀመሩን መረዳት ተችሏል።

ለአብነትም አራተኛ መደበኛ ጉባኤውን ሐምሌ 01/2015 ያካሄደው የአዲርቃይ ወረዳ ምክር ቤት፤ “ሰላም በር” እና “ሰገነት” የተሰኙ ኹለት አማራጭ ስያሜዎችን ተቀብሎ በሕዝብ ምርጫ እንዲጸድቅ ወስኗል ነው የተባለው።

በተጨማሪም በወረዳው ሥር የሚገኙ ቀበሌዎች ስያሜ ለውጥ እንዲደረግ የተለያዩ ስያሜዎች ለምክር ቤቱ ቀርበው እንዲጸድቁም መወሰኑ ተጠቅሷል።

በማይጠብሪ ወረዳም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ መኖሩ የተገለጸ ሲሆን፤ በጠለምት አካባቢ የሚገኙት እንደ ማይትክሊት፣ አዲወሰኔ፣ ጻዳቀርኒ የተባሉ ቀበሌዎች እንዲሁም አዶፋሪ፣ አዲናቴ፣ አዲሐሮሶን፣ ማይ ዳጉሳ፣ ማይ ቃጫ፣ ማይ ሎሚን የተባሉ ጎጦች የአማርኛ ቋንቋ ስያሜ ሊሰጣቸው መሆኑ ተጠቁሟል።

የሥም ለውጥ የሚደረግባቸው ኹሉም ቦታዎች ሥም ዕቅድ ተዘጋጅቶ በጠለምት ሥር ለሚገኙ ወረዳዎች ምክር ቤት መሰራጨቱ እንዲሁም፤ ጉዳዩ በክልልና በዞን ደረጃም ተቀባይነት ማግኘቱ ነው የተገለጸው።
የቦታዎች ስያሜ ሲቀየር፤ የየመስሪያ ቤት ማህተሞችን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት ላይ የስያሜ ለውጥ መደረጉም አይቀሬ ነው ተብሏል።
በእነዚህ አካባቢዎች ኹለቱም ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱ ሲሆን፣ ቦታዎቹ በአማራ እና በትግራይ ክልል ሕዝብ ዘንድ በተለያዬ ስያሜ ሲጠሩ ይስተዋላል።

@esatchannal
8.3K viewsedited  08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 21:01:20 መርሃቤቴ

ከሁለት ወር በፊት ኦሮሚያ ክልል ወለንጭቲ አቅራቢያ የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ትጥቅ አስቀምጠው ስፖርት እየሰሩ ባለበት ከታጣቂዎች በተከፈተ የተኩስ ሩምታ በርካቶች መገደላቸውን ሰምተን ነበር።ዛሬ ማለዳ ደግሞ መርሃቤቴ አለም ከተማ አቅራቢያ በተመሳሳይ ስፖርት እየሰሩ የነበሩ የሠራዊቱ አባላት ጥቃት እንደተፈፀመባቸውና በርካቶች ህይወታቸውን እንዳጡ ነዋሪዎ።እስከዛሬ ከታዩት ሁነቶች አንፃር የአማራ ክልልንም ሆነ የኦሮሚያ ክልልን ጉዳይ ከውይይት እና ከምክክር ውጭ በኃይል የሚፈታ አይደለም።ቢታሰብበት መልካም ነው።

@esatchannal
9.0K viewsedited  18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 21:01:20


የሁለት ዋንጫ ተሸላሚ

አሚና አህመድ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ነች። በአጠቃላይ ከሴት ተማሪዎች እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው የ2015 ዓ.ም ተመራቂዎች 3.995 ውጤት በማምጣት ከፋርማሲ ትምህርት ክፍል የሁለት ድርብ ዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።አሚናን መሰል ታታሪ ሴት ተማሪዎች ማገዝ ይገባል።
8.9K views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 20:43:51 ወላጅ እናቱን በዱላ ደብድቦ የገደለው ግለሰብ እጁን ለፖሊስ ሰጠ
በደቡብ ኦሞ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ ጨለቆት ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ወላጅ እናቱን በዱላ ደብድቦ ገድሏል በሚል የተጠረጠረዉ የ28 አመት ወጣት በአድራጎቱ የተበሳጩ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ሲያሯሩጡት አምልጦ እጁን ለፖሊስ እንደሰጠ ተገልጿል።

ተጠርጣሪዉ ወላጅ አባቱ በህይወት ሳለ ከሌሎች ወንድም እህቶቹ ጋር የእርሻ መሬት ድርሻዉን በዉርስ አግኝቷል ያለዉ ፖሊስ ከአባቱ የተላለፈለት ይዞታ በኮንትራት መልክ ለሌላ ሰዉ አሳልፎ መሸጡና የእናቱን ድርሻ እኔ ካልተጠቀምኩበት በሚል ልጅ ከእናቱ ጋር ሰጣ ገባዉስጥ ገብቶ ነገሩ ለግጭት እንደዳረጋቸዉ ነዉ የተገለፀዉ።

የእናቱን ይዞታ አርሶ ለመጠቀም ያነሳዉ የእራስ ወዳድነት አጀንዳ እናትየዉ ዉድቅ ማድረጋቸዉ ተከትሎ በነገሩ የተበሳጨዉ የ28 አመት ወጣት እናቱ ላይ የፈረጠመ ጡንቻዉን ሊያሳርፍበሰቸዉ ይሰናዳል።

ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 4:00 ሰዓት ግድም የ 50 ዓመት አዛዉንት እናቱን በዱላ ደጋግሞ ሲያሳርፍባቸዉ ተዝለፍልፈዉ ወድቀዉ ከወደቁበትም ሳይነቁ ህይወታቸዉ አልፏል።

ልጅ ወላጅ እናቱን በዱላ ደጋግሞ ሲደበድባቸዉ የጣር ጩኸት ማሰማታቸዉን ተከትሎ ፈጥነዉ ከወንጀሉ ስፍራ የደረሱት የአካባቢዉ ነዋሪዎች በልጅ እኩይ አድራጎት ተበሳጭተዉ ተጠርጣሪዉ ላይ እርምጃ ለመዉሰድ ሲያሯሩጡት ሸሽቶ ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመዝለቅ እጁን እንደሰጠ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

@esatchannal
8.5K viewsedited  17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 20:18:29 " ተፈታኞች በአካልም ይሁን በስነልቦና እራሳችሁን ዝግጁ አድርጉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መርሃ ግብርን ይፋ አድርጓል።

በዚህም ፥ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሐምሌ 16 እና 17/2015 ዓ.ም ወደተመደቡበት ተቋም ይገባሉ።

ሐምሌ 18/2015 ዓ.ም ገልጻ ይሰጣቸዋል።

ከሐምሌ 19 እስከ 21/2015 ዓ.ም ፈተናቸውን ይወስዳሉ። ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ ተማሪዎች ወደመጡበት ይመለሳሉ።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች  ደግሞ ሐምሌ 22 እና 23/2015 ዓ.ም ወደተመደቡበት ተቋም ይገባሉ።

ሐምሌ 24/2015 ዓ.ም ገለጻ ይሰጣቸዋል።

ከሐምሌ 25 እስከ 28/2015 ዓ.ም ፈተናቸውን ይወስዳሉ።  ከሚቀጥለው ቀን ጀምሮ ተማሪዎች ወደመጡበት ይመለሳሉ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን በሚውስዱበት ጊዜ የፈተናውን ህግና ስርዓት እንዲያከብሩ በጥብቅ አሳስቧል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተናው ግልጋሎት ከሚሰጡ የፅህፈት መሳሪያዎች እርሳስ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ እና ስክቢቶ ውጭ ወደ ፈተና ክፍል ይዞ መግባት ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን እንዲያውቁት ብሏል።

ተማሪዎቹ ከቤታቸው ሲወጡ፦
- መታወቂያ ፣
- አድሚሽን ካርድ
- የት/ቤት ዩኒፎርም መያዛቸውን እንዳይረሱ ፤ ወላጆችም ይህንን እንዲያስታውሷቸው ጥሪ ቀርቧል።

ወደ መፈተኛ ተቋማት ቆሎ፣ ጭኮ፣ በሶ የመሳሰሉ ደረቅ ምግቦችን ይዞ መግባት የሚፈቀድ ሲሆን የቴክኖሎጂ ውጤቶች፣ አይፓድ፣ ላፕቶፕ የመሳሰሉ እንዲሁም ማንኛውም ጌጣጌጥ ይዞ መግባት ፈፅሞ የተከለከለ ነው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ተፈታኞች በአካልም ይሁን በስነልቦና እራሳቸውን ዝግጁ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ለመውሰድ ከ869 ሺህ በላይ ተፈታኞች በኦንላይን መመዝገባቸውን ይፋ መደረጉ አይዘነጋም።

@esatchannal
8.6K viewsedited  17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 16:32:22
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ በአካል ቀርበው ምዝገባ እንዲያከናውኑ ጥሪ አቀረበ።

ዩኒቨርሲቲው በጦርነት የተቋረጠውን የመማር ማስተማር ስራውን ለማስቀጠል ሰፊ ዝግጅት ሲያደርግ እንደነበር ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ፦

- በ2013 ዓ/ም ተመራቂ የነበሩ የመጀመርያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች
- የድህረ ምረቃ ተማሪዎች
- የተከታታይ ትምህርትና የማታ ተማሪዎች
- የሕክምና ትምህርት ክፍል ተማሪዎች

ሐምሌ 26 እና 27/2015 ዓ/ም በአካል ተገኝተው እንዲመዘገቡ ዛሬ ጥሪ አቅርቧል።
8.8K views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ