Get Mystery Box with random crypto!

Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የቴሌግራም ቻናል አርማ christian_mezmur — Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር C
የቴሌግራም ቻናል አርማ christian_mezmur — Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር
የሰርጥ አድራሻ: @christian_mezmur
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 63.36K
የሰርጥ መግለጫ

🗣እኛስ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብከዋለን!
ትክክለኛ የሆኑ የወንጌል አስተምህሮዎችን መሰረት ያደረጉ፦
ትምህርቶች፣ ስብከቶች፣ ምስክርነቶች፣ የሪቫይቫል ታሪኮች፣ ዝማሬዎች፣ መንፈሳዊ ዜናዎች፣ እንዲሁም መንፈሳዊነታቸውን የያዙ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ!
ለወዳጅ ጋደኞቻቹ #ሼር በማድረግ ይጋብዙ!
አስተያየት @ChristianMezmur_bot ላይ ፃፉልን✍
ሁሌም ከኛ ጋር ስለሆናቹ እናመሰግናለን!

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-10-24 21:01:35 የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፲፪
@yanetmasra

ጎረቤት ደረቱን ቢደቃ እናቴና እህቶቼ አምርረው ቢያለቅሱ ላይመለስ አንቀላፋ  እኔም ከፍተኛ የልብ ሀዘን ተሰማኝ ግን ዋናው ችግር የመጣው ለቅሶው ጋብ እያለ የሰው መምጣት ሲቀዛቀዝ ከችግራች ጋር ተፋጠጥን አባቴ ከሞተ የምንተዳደርበት ቋሚ ንብረትም ሆነ የእናቴም ስራ አልነበረም ስለዚህ እናቴን የማግዛት የደረስኩ ልጅ እኔ ብቻ በመሆኔ ከትምህርት ጎን ለጎን ጫማ መጥረግ ጀመርኩ ለእኔ ቀላል የሚባል አልሆነልኝም ምንም እንኳን ከበፊቱ ደሀ ብሆንም በጊዜው ግን  ሀላፊነት ወስዶ ዝቅ ብሎ መስራት ከባድ ሆነብኝ እናቴም የኛን ጎሮሮ ለመሙላት የሰው ቤት እየተመላለሰች መስራት ጀመረች ኑሮ አልሞላ ሲላት  ጭቅጭቋ  በዛው ልክ ጨመረ በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን በሱፈቃድ ከጎኔ አልራቀኝም ነበር በሀዘኔ ሰዓት እያበረታ ከጎኔ ቆሞ ተገኘ ። በጣም ሳዝን ጊዜ " አይዞህ ቀን ያስጎነብሳል እግዚአብሔር ያነሳል " ይለኛል በዚህ ሁኔታ ሳለሁ አንድ ቀን በበሱፈቃድ ግፊት የፀሎት ህብረቱ ጋር ሄድኩ አካሌ እንጂ መንፈሴ እዛ አልነበረም ዝም ብዬ ድንዝዝ ብዬ እንደተቀመጥኩ እነሱ በሚፀልዩ ሰዓት አብርሀም ተጠግቶ እጆቼን ይዞ ፀለየልኝ ከዚህ በፊት አንደዚህ አድርጎልኝ ስለማያውቅ ግር አለኝ ቢሆንም ግን አልተቃወምኩትም ነበር ብቻ ግን "በእምነት እኔ የምለውን አብረኸኝ በል " አለኝ ከልቤ ሆኜ የሚለውን እየደገምኩ ማለት ጀመርኩ የሚፀልይልኝ ስለ መንፈስቅዱስ ሙላት ነበር እንዴት እንደሚሆን እና እንደሚሰራ ባይገባኝም ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ሳለ ሊሄድ ሲል አፅናኙን እልክላችኋለሁ እንዳለ ቃሉን ሲያነቡ ስሰማ የእውነት መፅናናትን ስለምፈልግ  በወቅቱ ከልብ  እንዲሞላኝ ተጠማሁት ያን ቀን ለእኔ አዲስ ሆነ በሰውነቴ እሳት ሲቀጣጠል ተሰማኝ የሆነ ሀይል ውስጤን ተቆጣጠረኝ



እጆቼ ተንቀጠቀጡ የሆነ የማላውቀው ቃል ከልቤ ተፈንቅሎ ሊወጣ ታገለኝ ያኔ አብርሽ "አትፍራ የሚመጣልህን ቃል ተናገረው ይሄ ልሳን "ይባላል አለኝ ከአፌ የማላውቃቸው ቃላቶች ወጡ ልቤ ይነግረኝ  የነበረው እውነት እግዚአብሔር ከኔ ጋር አለ የሚለውን ሀሳብ ነበር ፤ እውነትም ሊያፅናናኝ ይወዳል ፤ ችግሬን አይቷል ብዬ  አስብ ጀመርኩ በጉባኤው መሀል ትንቢት መጣልኝ "ጌታ እግዚአብሔር ታገለግለኛለህ " ብሎካል ተባልኩ "እውነት አገለግለዋለሁ? ይህንን ለማድረግ ብቁ ነኝ " ብዬ ተጠየኩ እነሱም "እግዚአብሔር ታማኝ አድርጎ የሚሾም አምላክ ነው ፈሪውን ጀግና የወደቀውን ከፍ ከፍ የሚያደረግ አምላክ ነው ። አንተ የበቃህ ስለሆንክ ሳይሆን እሱ አምላክ ስለሆነ ባንተ ላይ አድሮ ለጥቅም ለአገልግሎት ያበቃሀል አንተ ብቻ አትጠራጠር እመነው ተከተለው " አሉኝ ። ያን ለት ወሰንኩኝ ኢየሱስን እንደግል አዳኜ አድርጌ ተቀበልኩ ወስጤ ጨከን ሲል እና ቆራጥ ስሜት ሲሰማኝ ይታወሰኛል የዛን ቀን የጎበኘኝ የመንፈስ ቅዱስ እሳት በውስጤ ሲቀጣጠል ይኖራል   ከዛን ቀን በኋላ መንፈሳዊ ህይወቴ እያደገ መጣ በጥበብና በሞገስ እግዚአብሔር ሲያሳድገኝ ይሰማኝ ጀመረ እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ይሀ ፈሪ ዩሀንስ ወድያው ጠፋ ቃሉን ለማወቅ ያለኝ ጉጉት እና ረሀብ እየጨመረ መጣ ግን ዋናው ችግር የሆነብኝ ነገር የፀሎት ህብረት ወይም በሱፈቃድ ካልሄድኩ መፀሀፍ ቅዱስ ማግኘት አልችልም ነበር እንደውም ከእነሱ የሰማሁትን ቃል ቤቴ ገብቼ በተለይም ስተኛ አሰላስለዋለሁ። አንድ ቀን ግን አብረሀም ልዩ ስጦታ ሰጠኝ ለመጀመሪያ ጊዜ መፅሀፍ ቅዱስ ሊኖረኝ ቻለ በየትኛውም ጊዜ ላነበው መቻሌ በጣም አስደሰተኝ በህይወቴ ካገኘኋቸው ስጦታዎች ሁሉ ይሄ ልዩው ነው መቼም ማልረሳው...ይቀጥላል

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur
7.0K views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 19:01:51 የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፲፩
@yanetmasra

ወይ በሱፍቃድ እሱን መች አጣሁት መቼም ፈርተህ ኢየሱስን  እንድትክደው አልመክርህም ግን ቢያንስ ከእነሱ ጋር መመላለሱን አቁም ሲጠይቁህ ግን መልስላቸው እይታ ውስጥ  አትግባ መናገር ካለብህ ነገር በላይ አትናገር የኔ ሀሳብ ይሄ ነው በተረፈ የወደድከከውን አድርግ አልኩት እኔ እዛው ጭ  እንዳልኩ የእናቴን  ጥሪ ድምፅ ሰምቼ ለመውጣት ከመቀመጫዬ ተነሷው እሷ ከእኔ ቀርባ ኖሯል  ገና ሳልወጣ ገባች " አንተ ፈጣሪ የረገመህ ልጅ ጠፋብኝ ብዬ ሀገር ለሀገር ሳስ አንተ እንደ አይጥ እዚህ ተወሽቀህ ኖሯል ምናለ ስትወጣ እየተከተልኩህ መሆኑን አውቀሀል መለስ ብለህ እንኳን  እናቴ የት ገባች  አትልም ደሞ እዚህ ምን ትሰራለክ ጭራሽ እዚህ መዋል ጀመርክ እንደአለቺኝ  እውነት ለመናገር ከሆነ ሀሳቤ በሱፍቃድ ላይ ሆኖ  እናቴ ምንም ትዝ አላለቺኝም ነበር "ወይ እማ በጣም ጎድተውት ስለነበር ከእናቱ ጋር ደግፈን  እቤት አመጣነው በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኖ አንቺ ምንም ትዝ ልትይኝ አልቻልሽም ለዛ ነው ይቅርታ እንጂ ለመዋልም ፈልጌ አልነበረም አልኳት ይመስለኛል እናቴ ቤታቸው ያለዛሬ ገብቼ የማውቅ አልመሰላትም ብታውቅ ደስ ስለማይላት ዛሬ ገና እንደገባው አስመሰልኩ እንጂ በጣም ቤታቸው ከመግባቴ የተነሳ ቤታቸው ቤቴ እየመሰለኝ መቷል የበሱፍቃድ አባት የቤተክርስቲያን አገልጋይ ናቸው መፅሀፍ ቅዱስን ያስተምራሉ በዚህ ምክነያት ህይወታቸው ቀላል የሚባል አልሆነም እንዲያውም በሱፍቃድ እንደነገረኝ ከሆነ  የበፊት ቤታቸውን ለቀው የወጡበት ሠፈርተኛው ስለሚጠሏቸውና  በእነሱ ላይ የሚሰሩት ደባ መቋቋም ስላቃታቸው መሆኑን ነግሮኛል በል አሁን ቀጥ ብለህ ውጣ እዚህ ስትርመጠመጥ ደሞ ትታይና ሌላ እዳ እንዳታመጣብኝ



እንግዲህ ብመክር ብዘክርህ ባጥንህ አልሰማ ብለኸኛል አባትህ ሲመጣ ሁሉንም  ነግሬ የሚያደርግህን ያደርግሃል ቢገልህም አልራራልህም ሆ ሆ ያኔ  በእንቁላሉ ጊዜ በቀጣሺኝ እንዳይመጣ ከአሁኑ ብቀጣህ ይሻላል አለቺኝ በእርግጠኝነት አባቴ ሲመጣ እንደምትናገረው አልጠራጠርም አባቴን በጣም ነው የምፈራው እንኳን ሊገርፈኝ አይደለም ቀና ብዬ  ፊቱን ሳየው ራሱ ከመደንገጤ የተነሳ ልቤ ትርክክ ይላል እንደውም ከእኔ ይልቅ ለታናናሽ እህቶቼ ፊቱ ይፈታል አንዳንዴም ሸነጥ ካደረገው ሊያጫውታቸው ይችላል  ታዲያ ይህን ባለችን በሳምንቱ አንድ መጥፎ ዜና ይናፈስ ጀመረ ከአባቴ ጋር የነበሩ ብዙ ወታደሮች ህይወታቸው ማለፉን እና ለቤተቦቻቸው መርዶ መነገሩ ገሀድ ሆነ ታዲያ የአባቴ ድምፅ መጥፍቱ  ደብዳቤም  እየላከ ባለመሆኑ እናቴ ስጋት እየገባት መጥቷል እኔም ብሆን ፍቅሩን ያላጣጣምኩት በውል ማንነቱን ያልተረዳሁት አባቴ ነገር እያሳሰበኝ መጣ ጎረቤቶቻችን አንዳንድ እየመጣ ያፅፅናል አንዳንድ የሚናገረውን የማያውቅ ደሞ ጭራሽ ሆድ ያስብሰናል ግን የፈሩት ይደረሳል እንደሚባለው ሁሉ አንድ ቀን እየነጋጋ ሳለ ቤታችን ተንኳኳ እናቴ "ማነው ?" እያለች በሩን ለመክፈት ተጠጋች ፊቷ ግን ተረብሾ ነበር ልክ ስትከፍተው ብቻ ሰዎቹ  አንድ ነገር ሳይናገሩ ጭንቅላቷን ይዛ እዬዬዋን ቀጠለች "ወይኔ! ጀግናው ወይኔ ! ወንዱ የልጆቼ አባት የልጅነቴ እኔ አፈር ልብላልህ እኔ እንደወጣሁ ልቅር  ልጆችህን በትነህ እኔን ለማን ጥለህ ትሄዳለህ ........ በጣም አለቀሰች ድንጋጤዬ ካለሁበት አላንቀሳቀሰኝም አይኖቼ እናቴ ላይ ፈጠው ቀሩ እሷን ለማረጋጋት ለያረዱ የመጡ ሰዎች ባንድ በኩል ያለቅሳሉ በሌላ በኩል ያፅናኗታል ብቻ ሆነም ቀረ የአባቴ መሞት እውን ሆነ ቤተዘመዶች ቢሰበሰቡ ....ይቀጥላል


ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur
6.8K views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-23 21:01:37 የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፲
@yanetmasra

እያለቀሰች ወደኛ ቀረበች በጉልበቷ ተንበርክካ አቅፋው አለቀሰች በዛን ሰአት እግሮቹ መንቀሳቀስ ጀመሩ አይኑንም ገለጥ አደረገ ሁለታችንም በድንጋጤ መንፈስ ሆነን " በሱፈቃድ አለህ ? ደና ነህ ?" አልነው " እግዚአብሔር ይመስገን ደና ነኝ እራሴን ስለሳትኩ ነው ብዙ አልጎዳኝም ስለነሰረኝ ነው ልብሴ በደም የተጨማለቀው " አለን እኛን ለማረጋጋት ሲል እንጂ ነገሩ እንደዛ እንዳልሆነ ፊቱን ብቻ በማየት መረዳት ይቻላል ፊቱ አብጧል ደሙም እንዳለው የነስር ብቻ አልነበረም ቆሞ መሄዱን እራሱ ፈርቼለት ነበር ቢሆንም እኔና እናቱ  " እሺ "ብለን ደግፈን ወደቤት ወሰድነው እናቱ ነጭ ጨርቅ ውሀ ውስጥ እየነከሩ በመጭመቅ ደሙን ጠራረጉለት ሀኪም ቤት ሂድ ቢባልም አሻፈረኝ አለ ስለጉዳዩ ስንጠይቀው ከአንድ ወታደር ጋር ተጣልቶ መሆኑን ነገረን "ምን አገናኝቶህ ነው ? " አልኩት "ምን ያገናኘናል ብለህ ነው ዛሬ ቅዳሜ መሆኑን መቼም አልዘነጋኸውም ከፀሎት ወተን ስንመጣ በእጃችን መፅሀፍ ቅዱስ ይዘን ነበር ታድያ ከነሱ ተለይቼ ብቻዬን ወደቤት መምጣት ስጀምር ጠራኝና ወደሱ ሄድኩ እግዚአብሔር የለም የሚለውን የሶሻሊዝም አስተምህሮ ለምን እንደማላከብር ጠየቀኝ እኔም ሶሻሊዝም ፣ እኛ ፣ ከኛ በፊት የነበሩት በአጠቃላይ አለም ሳይፈጠር እግዚአብሔር ያለና የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ስለሆነ  " አልኩት ያኔ ተናደደና እግዚአብሔር የለም እንድል ካለዛ እንደሚመታኝ ነገረኝ እኔም እሺ እግዚአብሔር የለም ብዬ እንዳምን አንድ ነገር ንገረኝ እውነት እግዚአብሔር ባይኖር ኖሮ ማን እንደዚ አድርጎ ፈጠረህ ሠማይና ምድርን ፀሀይና ጨረቃን ማን አበጃጀ መቼስ ይሄን ሊያደርግ የሚችል የሰው ልጅ የለም ነገ የሚፈጠረውን የሚያውቅ ሞቱን ማስቀረት የሚችል ሰው አለ ? የለም ! ምክንያቱም ይሄን ሊያደርግ የሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው ሌላውን ነገር ተወውና አሁን የጠየቅኩህ ነገር እግዚአብሔር እንዳለ ካላሳመነህ በተቃራኒው አንተ እግዚአብሔር እንደሌለ የሚያሳምኑና የሰው ልጅ ሊያደርገው የሚችላቸው መሆኑን አሳምነኝ አልኩት



ሊለኝ የሚችለው ነገር አልነበረም ስለዚህ ንዴቱን በመደብደብ ተወጣብኝ ይሄ ብቻ ነው የሆነው አለን " ይሄ ብቻ ነው የሆነው ? ቆይ ከዚ በላይ ምን ይሁን ? አንተ ሰውዬ መሞት ፈልገሀል ጭራሽ መልስ ትመልስለታለህ ዝም ብትል ምን ነበረበት ቢያንስ ይሄ መከራ እስከሚያልፍ በትዕግስት መኖር አቅቶህ ነው ብትሞትስ ትንሽ እንኳን ለነፍስህ አትሳሳም " አልኩት " ደሞ ለወንጌል እንኳን መደብደብ ህይወት ይሰጥ የለ እንዴ ፈርቼማ ዝም አልልም በአቋሜ እንደፀናሁ ወይ መከራው ያልፋል ወይ እኔ አልፋለሁ " አለኝ በዚ መሀል  እናቱ ጣልቃ ገቡና "የበኩር ልጄ በሱፈቃድ እንደዚ ልብህ ለጌታ ቅርብ መሆኑ እግዚያብሄር በልጅ እንደባረከኝ የምመለከትበት ነው በምታደርገው ነገር ሁሉ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ ግን እንድትሞትብኝ አልፈልግም አረማመድህን አስተውል ይቺ መከራ እስከምታልፍ ድረስ በጥበብ ኑር "አሉት  እሱም ቆይ እማ የምትይኝ ይሄ ጊዜ እስከሚያልፍ ተደብቄ እነሱ የሚሉኝን እያደረግኩና ሰውን እያስደሰትኩ ፈጣሪን እያስከፋሁ እንድኖር ነው የምትፈልጊው ከልጅነቴ ጀምሮ መፅሀፍ ቅዱስ እንዳነብ ለእግዚአብሔር ቃል እንድገዛ ችግር በመጣ ጊዜ ወደ ሗላ እንዳያስቀረኝ እየነገራችሁ ያሳደጋችሁኝ ዛሬ በመከራው ሰአት ወደ ሗላ እንዳፈገፍግ ነው ? ቆይ ብሞትስ ? ወደዛ የሚቀር አለ ? የእኛ ክርስትያኖች ተስፋ የዘለአለም ህይወት ማግኘት አደል በስጋማ ሁላችንም እንሞታለን ግን የዘለአለም ሞትን አንሞትም ስለዚ መደነቅ አያስፈልግም መቼም ቢሆን እውነትን ከመናገር ወደ ሗላ አልልም " አላት አንዳንድ ጊዜ በሱፈቃድ የሚያወራውን ነገር ስሰማ በሁለት አመት የሚበልጠኝ ሳይሆን የአባቴ እኩያ ነው የሚመስለኝ ፍቅሩ ፣ ርህራሄው ፣ ትዕግስቱ ፣ መልካምነቱ እንዳለ ሁሉ ባመነበት ነገር ላይ ግን አቋሙ የማይቀየር ነብር ነው

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur
7.3K views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-23 19:00:51 የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፱
@yanetmasra

መልሱን ትነግረኛለህ " ብሎኝ ሄደ ጭራሽ ቢተወኝ ብዬ የተናገርኩት ቃሌ መልሶ እኔኑ አሰረኝ የእውነት አጣብቂኝ ውስጥ ገባሁ መልሼም ደሞ ሳስበው እውነት ግን በርበሬ ታጠንኩ ብዬ እንዲ ከሆንኩ እንዳልኩት የአባቴን ጠመንጃ ባይማ ሰይጣን እንደያዘው ሰው የማወራውን ሳላውቅ እለፈልፍ ነበር እራሴን ታዘብኩት በጣም !

   ከበሱፈቃድ ጋር ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ተራራቅን ወቅቱ ደሞ መጥፎ ነበር ለአራት አስርት አመታት ሀገሪቷን ያስተዳደሩት ንጉስ ለውጡን መቆጣጠር ስለተሳናቸው ስልጣኑ ወታደራዊ እጅ ላይ ወደቀ ለዚህም ደም ብዙ ምክንያቶች አሉት ከነሱ መካከል የተማሪዎች ፣ የምሁራን የማያባራ ግፊት ይጠቀሳል ቢሆንም ግን የንጉሱ መንግስት ወደቀ ማለት ወታደራዊው የተሻለ ብቃትንና የአመራር ዘዴ ይዞ መጥቷል ማለት አልነበረም እንደውም ሀገሪቷን ለመምራት በቂ ዝግጅት አልነበራቸውም ብሎ መናገር ይቻላል ። በተለይ ደሞ አማኝ ለሆነው ህብረተሰብ እጅግ ከባድ ወቅት እንዲያሳልፍ ምክንያት ሆነዋል ይህ ወታደራዊ አስተዳደር በዋናነት የሚከተለው እግዚአብሔር የለም የሚል አስተምሮ ሲሆን ይህም የሆነው በ1966 ዓመተ ምህረት  ነበር እንደውም እንኳን አደረሳችሁ ሳይሆን እንኳን ደረሳችሁ ነበር በወቅቱ የሚባለው ይህ አባባል የእግዚአብሔርን አይን ከመውጋት አይተናነስም ብዬ አምናለሁ የሰው ልጅ ሁሉ የእግዚአብሔር ፍጡር ሆኖ ሳለ የለህም ብሎ በድፍረት መናገር ትልቅ ሀጥያት ነው የእግዚአብሔር ትዕግስት የማያልቅ ባይሆን ኖሮ ስንቶቻችን እንደ ሀጥያታችን በጠፋን ነበር ታድያ በዚ ጊዜ በድፍረት ይሄን አባባል የማይከተሉትና እግዚአብሔር አለ ብለው በሚያምኑት ላይ ትልቅ ስደት ተጀመረ የኔ ነገር ያለየለት ጉዳይ ስለሆነ በአማኞች ላይ የሚደረገው ነገር ከማየትና ከመፍራት ውጪ የደረሰብኝ ነገር አልነበረም ነበር



እንደውም አንድ ቀን እናቴ " አንተ ገልቱ በጊዜ የእኔን ምክር ሰምተህ ባይሆን ኖሮ እንደነዚ ሰዎች ነበር እጣህ የሚሆነው እንደዛ ጂኒ ጓደኛህ በአደባባይ እየተገረፍክ ትዋረድ ነበር  " አለቺኝ ይሄን ቃል ያወጣችው አውቃ ይሆን የእውነቷን ወይ አምልጧት አላውቅም ብቻ በአደባባይ መገረፍ የሚለውን ቃል በጆሮዬ እንደገባ " የቱ ብዬ " "አፈጠጥኩባት ይሀ በሱፈቃድ የተባለው ነዋ " አለቺኝ  " የት ? መቼ ? ማን ገረፈው ? ..." በጥያቄ አጣደፍኳት " እዚ በላይ ባለው መንገድ ላይ ካንድ ወታደር ጋር ሲሟገት እንዳይሞት እንዳይሽር አድርጎ ቀጥቅጦታል ፤ ምናለ አርፎ ቢቀመጥ ? ጉድ እኮ ነው ! ምኑን ተማምኖ እንደሆነ ባላውቅም ሲመላለሰው ዋጋውን ሰጠው ፤ ይበለው ! ዘንድሮማ ጴንጤን የሚያሾር ተገኝቷል " አለቺኝ ምላሽ ሳልሰጣት በሱፈቃድ አለ ወዳለቺኝ ስፍራ መሄድ ጀመርኩ እናቴ መናገሯ ሳይቆጫት አይቀርም " አንተ ዩሀንስ ተመለስ ወዴት ነው ? ኧረ ጉድ ! ምን ልታደርግ  ነው ? አንተንም እንዳይደበድቡህ ሗላ ተናግርያለሁ ተመለስ ! ኧረ ጉዴ ዛሬ በገዛጄ ልጄን የእሳት እራት ላደርገው ነው ፤ምነው ዝም ብል ዩሀንስ "( እየተከተለቺኝ ቢሆንም መሮጥ ስጀምር ከወደ ሗላ ቀረች ድምፇም ቀስ በቀስ ከጆሮዬ ተሰወረ ) በሱፈቃድ አለ ወዳለቺኝ ቦታ ደረስኩ እንዳለችውም በደም ተለውሶ ወድቋል አካባቢው ላይ ያሉት ሰዎች ከመርዳት ይልቅ ክብ ሰርተው ይመለከቱታል ወደ ማህል ገብቼ ጭንቅላቱን ታፋዬ ላይ አስቀምጬ በእጆቼ ፊቱን መታ መታ እያደረኩ " በሱፈቃድ በሴ ተነስ " እያልኩ ልቀሰቅሰው ሞከርኩ ዝምታው ሲበዛብኝ የሞተ መስሎኝ እግሮቼ ቄጤማ ሆኑ ልብሱ በደም ስለራሰ ደሙ ፈሶ  አልቆ ነው ወደሚል ድምዳሜ ደረስኩ ይሄን እያንሰላሰልኩ ማን ነግሯት እንደሆነ ባላውቅም የበሱፈቃድ እናት " ልጄ ልጄ "ብላ እያለቀሰች ወደኛ ቀረበች

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur
7.1K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-12 14:47:34 ዝማሬ “መዳኔ"
ዘማሪ እንዳለ ወ/ጊዮርጊስ
Size 5MB
ርዝመት 5Min
Quality 128 kbps(High Quality)
Genres Gospel Song

ገራሚ ዝማሬ ነው ሰምታቹ ተባረኩበት
ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur
151 viewsedited  11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 21:01:40 #ተለቀቀ
ቃልኛ መንፈሳዊ መፅሔት
    ዘጠነኛ እትም
   በቃልቲዩብ የተዘጋጀ
7ሜ.ባ PDF ያውርዱት

●18 ጥያቄዎች
ለተወዳጇ ዘማሪት አይዳ አብርሀም
የስራ ባህልና ክርስትና
(በነቢይ መሳይ አለማየሁ)
ክርስትናችሁን ከወረት ጠብቁ
(በፓስተር ስንታየሁ በቀለ)
ትናንቱን የረሳ ትውልድ ፤ የባህልና ትውፊት ክስረት
(በቢንያም አዲሱ)
ጥሩ አድማጭ መሆን!
(በአቤኔዘር አለማየሁ)

እና ሌሎች . . .
... ለወዳጆቻችሁ ለአማኞች ፣ ለማያምኑ ሼር
  ለበፊት እትሞችን | ይሄን ይጫኑ |

         @KALTUBE
         @KALTUBE
         @KALTUBE
2.3K views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 15:38:44
#Challenge ለምትወዱ

ሁላቹም የቃልቲዩብ ቤተሰቦች  ከላይ ያለውን የቃልኛ ከቨር ፎቶ

በቴሌግራም ፕሮፋይል /Profile በማድረግ

●በ Facebook እና Instagram Story  ላይ በማድረግ አብረውን ያገልግሉ

ቢያንስ ደግሞ  ለ10 ወዳጆቻችሁ ሼር ይደረግ

@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
498 viewsedited  12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-08 09:38:53 አዲሱ የቤቲ ተዘራ አልበም ተለቋል!

አልበሙን ለመግዛት


Itune

Amazon

Spotify

Telegrambot
@FikirTetsafeAlbumBot

YouTube music

ZOE Store

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur
2.1K viewsedited  06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 09:54:39 ዝማሬ “ እኔ እሱን የማውቀው "
ዘማሪት MIHRET ETEFA
የተለቀቀው October , 2022
Size 8MB
ርዝመት 7Min
Quality 128 kbps(High Quality)
Genres Gospel Song

ገራሚ ዝማሬ ነው ሰምታቹ ተባረኩበት
ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur
2.3K viewsedited  06:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 21:58:28 በዚህ ሳምንት ከሚወጣው ቃልኛ መፅሔታችን የተወሰዱ ሀሳቦች

በሀገራችን ብዙ ጊዜ ስራ እንደሌለ ተደርጎ ይወሰዳል። ከዛ ብዙ ሰው ተመርቆ ስራ የለም ብሎ በማመን ቁጭ ይላል። ለምን ቁጭ አልክ ሲባል ስራ ስለሌለ የሚል ምላሽ ይመልሳል።ይህ የማህበረሰባችን መሰረታዊ የዕይታ ችግር ነው። በተመረቅኩበት ስራ አላገኘሁም ስለዚህ ስራ የለም የምትል ከሆነ  ቅጥርን እንደ ትልቅ ስኬት እየቆጠርክ ነው ማለት ነው። ስራ የለም ብለው የሚያምኑ ብዙ ሰዎች ዝቅ ብለው የመስራት ስነልቦና ያላዳበሩ ሰዎች ናቸው።በውጪው አለም ሁለትና ከዛ በላይ ዲግሪ ይዘው መኪና እጥበት የሚሰሩና ቤተሰባቸውን የሚረዱ ህልማቸውን በገንዘብ የሚረዱ ብዙ ሰዎችን ማየት የተለመደ ነው። ስለዚህ ምን እንጀምር? ምን እንስራ? በዝቅተኛ ካፒታል የሚጀመሩ ስራዎች ምንድናቸው? እንደ ክርስቲያን የግል ስራዎን መጀመር እንዴት ይቻላል? አቅማችሁን እንዳትጠቀሙ ያደረጋችሁ ምንድነው? የሚለውን በስፋት እንመለከታለን . . .
በነቢይ መሳይ አለማየሁ


ታሪክን ፣ ባህልን፣ቀኖናን ፣ አስተምህሮን፣ ወግን በትክክል በተገቢው ሁኔታ በአፍሪካ የወንጌላዊያን ክርስትና ባለመተላለፉ ምክንያት በቀደምት ተሐድሶአዊያን ያልታሰበ ባዕድ ሀሳብ፣ ለነገሮች ያለ ምልከታ፣ ባህል ፣ወግ እንዲሁም ህግ ፍፁም የሚቃረን መንገድ በሀገራችንም ብሎም በአፍሪካ እየተመለከትነው ያለነው ስርዓት አልበኝነት በፕሮቴስታንቲዝም እንቅስቃሴ ውስጥ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ሆኗል። . . .
በቢንያም አዲሱ


ማዳመጥ ግን ጥረት ይጠይቃል። በቀላሉ አይመጣም። በአንድ ጀምበር የማዳመጥ ጥበብን አንማረውም። ጥሩ የማዳመጥ ስሜት ማዳበር ከጊዜ ወደጊዜ የተሻሻለ ይሆናል፣ ነገር ግን ጥረት ማድረጉን የሆነ ቦታ መጀመር ይኖርብናል። . . .
በአቤኔዘር አለማየሁ


ጠያቂነታችን ከመኖር አላማችን ጋር የተቆራኘ መሆን አለበት።  ሁላችንም አጥርተን ባንረዳዉም  የምንኖርለት አላማ አለን ታዲያ አላማችንን መገንዘብ የምንችለዉ ለምን ተፈጠርኩ? በእኔ መኖር ዉስጥ ሊከፈት የሚገባዉ የትዉልድ በር ምንድነዉ? እነዚህና መሳል ጥያቄዎችን የጠያቂነት መብታችንን ተጠቅመን  መጠየቅ ስንጀምር ለተፈጠርንለት አላማም መኖር እንጀምራለን። . . .
በኤደን ቶሎሳ

ወረተኝነት ሄድ መለስ የሚል ስሜት ነው፤ ሞቅ ቀዝቀዝ የሚል አቋም፤ ከፍ ደግሞ ዝቅ የሚል መዋዠቅ ነው፤ እንዲህ ወይም እንዲያ ብለን እርግጠኛ የማንሆንበት መልክ ነው፡፡ በቆመበት የማናገኘው እንደ ጥላ የሚዞር፣ እንደ አየር የማይጨበጥ ነፋስ ነው፡፡ ስር ነቀል ፈውስ የሚሻም ደዌ ነው፡፡ ሳይታወቅበት ቤተክረስቲያን ውስጥ መሽጎ ቅዱሳንን የሚያስረመጠምጥ ነው፡፡ . . .
በመጋቢ ስንታየሁ በቀለ

እና ሌሎች ፁህፎች

ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር አድርጉ

ቃልኛ 9ኛ አትም
በዚህ ሳምንት

@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
2.5K views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ