Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፱ @yanetmasra መ | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፱
@yanetmasra

መልሱን ትነግረኛለህ " ብሎኝ ሄደ ጭራሽ ቢተወኝ ብዬ የተናገርኩት ቃሌ መልሶ እኔኑ አሰረኝ የእውነት አጣብቂኝ ውስጥ ገባሁ መልሼም ደሞ ሳስበው እውነት ግን በርበሬ ታጠንኩ ብዬ እንዲ ከሆንኩ እንዳልኩት የአባቴን ጠመንጃ ባይማ ሰይጣን እንደያዘው ሰው የማወራውን ሳላውቅ እለፈልፍ ነበር እራሴን ታዘብኩት በጣም !

   ከበሱፈቃድ ጋር ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ተራራቅን ወቅቱ ደሞ መጥፎ ነበር ለአራት አስርት አመታት ሀገሪቷን ያስተዳደሩት ንጉስ ለውጡን መቆጣጠር ስለተሳናቸው ስልጣኑ ወታደራዊ እጅ ላይ ወደቀ ለዚህም ደም ብዙ ምክንያቶች አሉት ከነሱ መካከል የተማሪዎች ፣ የምሁራን የማያባራ ግፊት ይጠቀሳል ቢሆንም ግን የንጉሱ መንግስት ወደቀ ማለት ወታደራዊው የተሻለ ብቃትንና የአመራር ዘዴ ይዞ መጥቷል ማለት አልነበረም እንደውም ሀገሪቷን ለመምራት በቂ ዝግጅት አልነበራቸውም ብሎ መናገር ይቻላል ። በተለይ ደሞ አማኝ ለሆነው ህብረተሰብ እጅግ ከባድ ወቅት እንዲያሳልፍ ምክንያት ሆነዋል ይህ ወታደራዊ አስተዳደር በዋናነት የሚከተለው እግዚአብሔር የለም የሚል አስተምሮ ሲሆን ይህም የሆነው በ1966 ዓመተ ምህረት  ነበር እንደውም እንኳን አደረሳችሁ ሳይሆን እንኳን ደረሳችሁ ነበር በወቅቱ የሚባለው ይህ አባባል የእግዚአብሔርን አይን ከመውጋት አይተናነስም ብዬ አምናለሁ የሰው ልጅ ሁሉ የእግዚአብሔር ፍጡር ሆኖ ሳለ የለህም ብሎ በድፍረት መናገር ትልቅ ሀጥያት ነው የእግዚአብሔር ትዕግስት የማያልቅ ባይሆን ኖሮ ስንቶቻችን እንደ ሀጥያታችን በጠፋን ነበር ታድያ በዚ ጊዜ በድፍረት ይሄን አባባል የማይከተሉትና እግዚአብሔር አለ ብለው በሚያምኑት ላይ ትልቅ ስደት ተጀመረ የኔ ነገር ያለየለት ጉዳይ ስለሆነ በአማኞች ላይ የሚደረገው ነገር ከማየትና ከመፍራት ውጪ የደረሰብኝ ነገር አልነበረም ነበር



እንደውም አንድ ቀን እናቴ " አንተ ገልቱ በጊዜ የእኔን ምክር ሰምተህ ባይሆን ኖሮ እንደነዚ ሰዎች ነበር እጣህ የሚሆነው እንደዛ ጂኒ ጓደኛህ በአደባባይ እየተገረፍክ ትዋረድ ነበር  " አለቺኝ ይሄን ቃል ያወጣችው አውቃ ይሆን የእውነቷን ወይ አምልጧት አላውቅም ብቻ በአደባባይ መገረፍ የሚለውን ቃል በጆሮዬ እንደገባ " የቱ ብዬ " "አፈጠጥኩባት ይሀ በሱፈቃድ የተባለው ነዋ " አለቺኝ  " የት ? መቼ ? ማን ገረፈው ? ..." በጥያቄ አጣደፍኳት " እዚ በላይ ባለው መንገድ ላይ ካንድ ወታደር ጋር ሲሟገት እንዳይሞት እንዳይሽር አድርጎ ቀጥቅጦታል ፤ ምናለ አርፎ ቢቀመጥ ? ጉድ እኮ ነው ! ምኑን ተማምኖ እንደሆነ ባላውቅም ሲመላለሰው ዋጋውን ሰጠው ፤ ይበለው ! ዘንድሮማ ጴንጤን የሚያሾር ተገኝቷል " አለቺኝ ምላሽ ሳልሰጣት በሱፈቃድ አለ ወዳለቺኝ ስፍራ መሄድ ጀመርኩ እናቴ መናገሯ ሳይቆጫት አይቀርም " አንተ ዩሀንስ ተመለስ ወዴት ነው ? ኧረ ጉድ ! ምን ልታደርግ  ነው ? አንተንም እንዳይደበድቡህ ሗላ ተናግርያለሁ ተመለስ ! ኧረ ጉዴ ዛሬ በገዛጄ ልጄን የእሳት እራት ላደርገው ነው ፤ምነው ዝም ብል ዩሀንስ "( እየተከተለቺኝ ቢሆንም መሮጥ ስጀምር ከወደ ሗላ ቀረች ድምፇም ቀስ በቀስ ከጆሮዬ ተሰወረ ) በሱፈቃድ አለ ወዳለቺኝ ቦታ ደረስኩ እንዳለችውም በደም ተለውሶ ወድቋል አካባቢው ላይ ያሉት ሰዎች ከመርዳት ይልቅ ክብ ሰርተው ይመለከቱታል ወደ ማህል ገብቼ ጭንቅላቱን ታፋዬ ላይ አስቀምጬ በእጆቼ ፊቱን መታ መታ እያደረኩ " በሱፈቃድ በሴ ተነስ " እያልኩ ልቀሰቅሰው ሞከርኩ ዝምታው ሲበዛብኝ የሞተ መስሎኝ እግሮቼ ቄጤማ ሆኑ ልብሱ በደም ስለራሰ ደሙ ፈሶ  አልቆ ነው ወደሚል ድምዳሜ ደረስኩ ይሄን እያንሰላሰልኩ ማን ነግሯት እንደሆነ ባላውቅም የበሱፈቃድ እናት " ልጄ ልጄ "ብላ እያለቀሰች ወደኛ ቀረበች

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur