Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፲ @yanetmasra እ | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፲
@yanetmasra

እያለቀሰች ወደኛ ቀረበች በጉልበቷ ተንበርክካ አቅፋው አለቀሰች በዛን ሰአት እግሮቹ መንቀሳቀስ ጀመሩ አይኑንም ገለጥ አደረገ ሁለታችንም በድንጋጤ መንፈስ ሆነን " በሱፈቃድ አለህ ? ደና ነህ ?" አልነው " እግዚአብሔር ይመስገን ደና ነኝ እራሴን ስለሳትኩ ነው ብዙ አልጎዳኝም ስለነሰረኝ ነው ልብሴ በደም የተጨማለቀው " አለን እኛን ለማረጋጋት ሲል እንጂ ነገሩ እንደዛ እንዳልሆነ ፊቱን ብቻ በማየት መረዳት ይቻላል ፊቱ አብጧል ደሙም እንዳለው የነስር ብቻ አልነበረም ቆሞ መሄዱን እራሱ ፈርቼለት ነበር ቢሆንም እኔና እናቱ  " እሺ "ብለን ደግፈን ወደቤት ወሰድነው እናቱ ነጭ ጨርቅ ውሀ ውስጥ እየነከሩ በመጭመቅ ደሙን ጠራረጉለት ሀኪም ቤት ሂድ ቢባልም አሻፈረኝ አለ ስለጉዳዩ ስንጠይቀው ከአንድ ወታደር ጋር ተጣልቶ መሆኑን ነገረን "ምን አገናኝቶህ ነው ? " አልኩት "ምን ያገናኘናል ብለህ ነው ዛሬ ቅዳሜ መሆኑን መቼም አልዘነጋኸውም ከፀሎት ወተን ስንመጣ በእጃችን መፅሀፍ ቅዱስ ይዘን ነበር ታድያ ከነሱ ተለይቼ ብቻዬን ወደቤት መምጣት ስጀምር ጠራኝና ወደሱ ሄድኩ እግዚአብሔር የለም የሚለውን የሶሻሊዝም አስተምህሮ ለምን እንደማላከብር ጠየቀኝ እኔም ሶሻሊዝም ፣ እኛ ፣ ከኛ በፊት የነበሩት በአጠቃላይ አለም ሳይፈጠር እግዚአብሔር ያለና የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ስለሆነ  " አልኩት ያኔ ተናደደና እግዚአብሔር የለም እንድል ካለዛ እንደሚመታኝ ነገረኝ እኔም እሺ እግዚአብሔር የለም ብዬ እንዳምን አንድ ነገር ንገረኝ እውነት እግዚአብሔር ባይኖር ኖሮ ማን እንደዚ አድርጎ ፈጠረህ ሠማይና ምድርን ፀሀይና ጨረቃን ማን አበጃጀ መቼስ ይሄን ሊያደርግ የሚችል የሰው ልጅ የለም ነገ የሚፈጠረውን የሚያውቅ ሞቱን ማስቀረት የሚችል ሰው አለ ? የለም ! ምክንያቱም ይሄን ሊያደርግ የሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው ሌላውን ነገር ተወውና አሁን የጠየቅኩህ ነገር እግዚአብሔር እንዳለ ካላሳመነህ በተቃራኒው አንተ እግዚአብሔር እንደሌለ የሚያሳምኑና የሰው ልጅ ሊያደርገው የሚችላቸው መሆኑን አሳምነኝ አልኩት



ሊለኝ የሚችለው ነገር አልነበረም ስለዚህ ንዴቱን በመደብደብ ተወጣብኝ ይሄ ብቻ ነው የሆነው አለን " ይሄ ብቻ ነው የሆነው ? ቆይ ከዚ በላይ ምን ይሁን ? አንተ ሰውዬ መሞት ፈልገሀል ጭራሽ መልስ ትመልስለታለህ ዝም ብትል ምን ነበረበት ቢያንስ ይሄ መከራ እስከሚያልፍ በትዕግስት መኖር አቅቶህ ነው ብትሞትስ ትንሽ እንኳን ለነፍስህ አትሳሳም " አልኩት " ደሞ ለወንጌል እንኳን መደብደብ ህይወት ይሰጥ የለ እንዴ ፈርቼማ ዝም አልልም በአቋሜ እንደፀናሁ ወይ መከራው ያልፋል ወይ እኔ አልፋለሁ " አለኝ በዚ መሀል  እናቱ ጣልቃ ገቡና "የበኩር ልጄ በሱፈቃድ እንደዚ ልብህ ለጌታ ቅርብ መሆኑ እግዚያብሄር በልጅ እንደባረከኝ የምመለከትበት ነው በምታደርገው ነገር ሁሉ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ ግን እንድትሞትብኝ አልፈልግም አረማመድህን አስተውል ይቺ መከራ እስከምታልፍ ድረስ በጥበብ ኑር "አሉት  እሱም ቆይ እማ የምትይኝ ይሄ ጊዜ እስከሚያልፍ ተደብቄ እነሱ የሚሉኝን እያደረግኩና ሰውን እያስደሰትኩ ፈጣሪን እያስከፋሁ እንድኖር ነው የምትፈልጊው ከልጅነቴ ጀምሮ መፅሀፍ ቅዱስ እንዳነብ ለእግዚአብሔር ቃል እንድገዛ ችግር በመጣ ጊዜ ወደ ሗላ እንዳያስቀረኝ እየነገራችሁ ያሳደጋችሁኝ ዛሬ በመከራው ሰአት ወደ ሗላ እንዳፈገፍግ ነው ? ቆይ ብሞትስ ? ወደዛ የሚቀር አለ ? የእኛ ክርስትያኖች ተስፋ የዘለአለም ህይወት ማግኘት አደል በስጋማ ሁላችንም እንሞታለን ግን የዘለአለም ሞትን አንሞትም ስለዚ መደነቅ አያስፈልግም መቼም ቢሆን እውነትን ከመናገር ወደ ሗላ አልልም " አላት አንዳንድ ጊዜ በሱፈቃድ የሚያወራውን ነገር ስሰማ በሁለት አመት የሚበልጠኝ ሳይሆን የአባቴ እኩያ ነው የሚመስለኝ ፍቅሩ ፣ ርህራሄው ፣ ትዕግስቱ ፣ መልካምነቱ እንዳለ ሁሉ ባመነበት ነገር ላይ ግን አቋሙ የማይቀየር ነብር ነው

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur