Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፲፪ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፲፪
@yanetmasra

ጎረቤት ደረቱን ቢደቃ እናቴና እህቶቼ አምርረው ቢያለቅሱ ላይመለስ አንቀላፋ  እኔም ከፍተኛ የልብ ሀዘን ተሰማኝ ግን ዋናው ችግር የመጣው ለቅሶው ጋብ እያለ የሰው መምጣት ሲቀዛቀዝ ከችግራች ጋር ተፋጠጥን አባቴ ከሞተ የምንተዳደርበት ቋሚ ንብረትም ሆነ የእናቴም ስራ አልነበረም ስለዚህ እናቴን የማግዛት የደረስኩ ልጅ እኔ ብቻ በመሆኔ ከትምህርት ጎን ለጎን ጫማ መጥረግ ጀመርኩ ለእኔ ቀላል የሚባል አልሆነልኝም ምንም እንኳን ከበፊቱ ደሀ ብሆንም በጊዜው ግን  ሀላፊነት ወስዶ ዝቅ ብሎ መስራት ከባድ ሆነብኝ እናቴም የኛን ጎሮሮ ለመሙላት የሰው ቤት እየተመላለሰች መስራት ጀመረች ኑሮ አልሞላ ሲላት  ጭቅጭቋ  በዛው ልክ ጨመረ በዚህ ሁሉ ጊዜ ግን በሱፈቃድ ከጎኔ አልራቀኝም ነበር በሀዘኔ ሰዓት እያበረታ ከጎኔ ቆሞ ተገኘ ። በጣም ሳዝን ጊዜ " አይዞህ ቀን ያስጎነብሳል እግዚአብሔር ያነሳል " ይለኛል በዚህ ሁኔታ ሳለሁ አንድ ቀን በበሱፈቃድ ግፊት የፀሎት ህብረቱ ጋር ሄድኩ አካሌ እንጂ መንፈሴ እዛ አልነበረም ዝም ብዬ ድንዝዝ ብዬ እንደተቀመጥኩ እነሱ በሚፀልዩ ሰዓት አብርሀም ተጠግቶ እጆቼን ይዞ ፀለየልኝ ከዚህ በፊት አንደዚህ አድርጎልኝ ስለማያውቅ ግር አለኝ ቢሆንም ግን አልተቃወምኩትም ነበር ብቻ ግን "በእምነት እኔ የምለውን አብረኸኝ በል " አለኝ ከልቤ ሆኜ የሚለውን እየደገምኩ ማለት ጀመርኩ የሚፀልይልኝ ስለ መንፈስቅዱስ ሙላት ነበር እንዴት እንደሚሆን እና እንደሚሰራ ባይገባኝም ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ሳለ ሊሄድ ሲል አፅናኙን እልክላችኋለሁ እንዳለ ቃሉን ሲያነቡ ስሰማ የእውነት መፅናናትን ስለምፈልግ  በወቅቱ ከልብ  እንዲሞላኝ ተጠማሁት ያን ቀን ለእኔ አዲስ ሆነ በሰውነቴ እሳት ሲቀጣጠል ተሰማኝ የሆነ ሀይል ውስጤን ተቆጣጠረኝ



እጆቼ ተንቀጠቀጡ የሆነ የማላውቀው ቃል ከልቤ ተፈንቅሎ ሊወጣ ታገለኝ ያኔ አብርሽ "አትፍራ የሚመጣልህን ቃል ተናገረው ይሄ ልሳን "ይባላል አለኝ ከአፌ የማላውቃቸው ቃላቶች ወጡ ልቤ ይነግረኝ  የነበረው እውነት እግዚአብሔር ከኔ ጋር አለ የሚለውን ሀሳብ ነበር ፤ እውነትም ሊያፅናናኝ ይወዳል ፤ ችግሬን አይቷል ብዬ  አስብ ጀመርኩ በጉባኤው መሀል ትንቢት መጣልኝ "ጌታ እግዚአብሔር ታገለግለኛለህ " ብሎካል ተባልኩ "እውነት አገለግለዋለሁ? ይህንን ለማድረግ ብቁ ነኝ " ብዬ ተጠየኩ እነሱም "እግዚአብሔር ታማኝ አድርጎ የሚሾም አምላክ ነው ፈሪውን ጀግና የወደቀውን ከፍ ከፍ የሚያደረግ አምላክ ነው ። አንተ የበቃህ ስለሆንክ ሳይሆን እሱ አምላክ ስለሆነ ባንተ ላይ አድሮ ለጥቅም ለአገልግሎት ያበቃሀል አንተ ብቻ አትጠራጠር እመነው ተከተለው " አሉኝ ። ያን ለት ወሰንኩኝ ኢየሱስን እንደግል አዳኜ አድርጌ ተቀበልኩ ወስጤ ጨከን ሲል እና ቆራጥ ስሜት ሲሰማኝ ይታወሰኛል የዛን ቀን የጎበኘኝ የመንፈስ ቅዱስ እሳት በውስጤ ሲቀጣጠል ይኖራል   ከዛን ቀን በኋላ መንፈሳዊ ህይወቴ እያደገ መጣ በጥበብና በሞገስ እግዚአብሔር ሲያሳድገኝ ይሰማኝ ጀመረ እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ይሀ ፈሪ ዩሀንስ ወድያው ጠፋ ቃሉን ለማወቅ ያለኝ ጉጉት እና ረሀብ እየጨመረ መጣ ግን ዋናው ችግር የሆነብኝ ነገር የፀሎት ህብረት ወይም በሱፈቃድ ካልሄድኩ መፀሀፍ ቅዱስ ማግኘት አልችልም ነበር እንደውም ከእነሱ የሰማሁትን ቃል ቤቴ ገብቼ በተለይም ስተኛ አሰላስለዋለሁ። አንድ ቀን ግን አብረሀም ልዩ ስጦታ ሰጠኝ ለመጀመሪያ ጊዜ መፅሀፍ ቅዱስ ሊኖረኝ ቻለ በየትኛውም ጊዜ ላነበው መቻሌ በጣም አስደሰተኝ በህይወቴ ካገኘኋቸው ስጦታዎች ሁሉ ይሄ ልዩው ነው መቼም ማልረሳው...ይቀጥላል

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur