Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፲፫ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፲፫
@yanetmasra

መቼም የማልረሳው ታድያ እናቴ መነጫነጮ አልቀረም "አባትህ ስለሞተ ምንም አታመጣም ብለህ ነው አደል የምልህን የማትሰማኝ ለነገር አሁንማ ለመድኩት እንኳን አንተ የሰፈሩ ሰው ሁሉ ባሏ ሞተባት ኑሮ አጎሳቆላት ብሎ አደል ንቆ ከሰው በታች ያደረገኝ አይ ጊዜ ስንቱን ያሳያል ዛሬ እንዲ መሆኔን አትይ ሌላው ቢቀር አንተ እንኳን ስማኝ አክብረኝ " ብላ ልታለቅስም አሻት በጣም ታሳዝነኛለች ጉዳቷን አልወድም በሌላ በምንም አይነት ሁኔታ ላሳዝናት አልፈልግም እንደውም ከሌላ ጊዜ በተለየ ለትምህርቴ ትኩረት መስጠት ጀመርኩ ምክንያቱም የኔ ደና ቦታ ላይ መገኘት የናቴንም ህይወት ደና ያደርገዋል ብዬ ማሰብ ጀመርኩ በስራም ቢሆን ከትምህርት ጎን ለጎን ጫማ በመጥረግ እናቴን ለማገዝ እፍጨረጨራለሁ እሷ ግን ይሄ አልታያትም ሁሉ ነገር ቀርቶባት መፅሀፍ ቅዱስ ባላነብና ጴንጤ ባልሆን ምኞቷ ነው ይሄ ደሞ ሌላ ፍርሀትና ጭንቀት ፈጠረባት በዛ ላይ የሠፈር ሰው በማያገባው እየገባ ልጅሽን እዚ አየሁት እዛ አየሁት ተቆጣጠሪው ፣ ቅጭው ፣ መጥፋቱ ነው ይሏታል ከሁሉ በላይ የሰው አፍ አላስቀምጥ አላት የናትነት አንጀቷም አላስችል እያላት እንዳልታሰር ፣ እንዳልመታ  ስትል ስጋት ያድርባታል እኔ ግን ምን ላርግ አንዴ የበራልኝን ብርሀን እንዴት ላጨልመው የቀመስኩትን የሰማሁትን እውነት እንዳላየ ሆኜ እውነት ማለፍ ብፈልግም እንኳን ማድረግ አልችልም በተለይ በዛን ወቅት አዲስ ክርስቲያን እንደመሆኔ መጠን የሚቀጣጠልብኝ እግዚአብሔርን የማወቅ እሳት እንዲሁ በከንቱ የሚጠፋ አልሆነም በዛ ላይ ከስር ከስር በሱፈቃድ ጋዝ ሲጨምርበት ቦግ ይላል ታድያ በዚ ሁኔታ ሳለን በወታደራዊው መንግስትና በአማኙ ማህበረሰብ ያለው



እንደ አይጥና ድመት መተያየት በዛው ልክ ፋመ በቅርብ የምናውቃቸው አማኞች መፅሀፍ ቅድስ ሲያነቡ በነበሩበት ወቅት በቀበሌ አመራሮችና በወጣቶች ተከበቡ በወቅቱ ከያዟቸው በሗላ መፅሀፍ ቅዱሳቸውን ሰብስበው አቃጠሉትና እንዲታጠኑት አደረጉ በዚ መልኩ ሊጎዶቸው ይሆን ወይ መከራው ሲበዛ እምነታቸውን እርግፍ አድርገው ይተዋሉ ብለው አስበው ይሆን ባላውቅም አንድ የገባኝ እውነት ግን ለወንጌል ተብሎ የሚከፈል ዋጋ ከስቃዬች ሁሉ በጣም የሚጣፍጥ ስቃይ ነው መከራው ሲበዛ የሚሸሽ ሳይሆን በተቃራኒው አንገቴን ለቢላ እያለ የሚያምነው አማኝ በዛ እኔም ብሆን ባለማወቄ በሱፈቃድን የተቆጣሁት እየፀፀተኝና ለምን ይሄን እንዳደረገ በደንብ አድርጎ እየገባኝ መጣ እየቆየ ግን እናቴ አስማሚያዬን ስታይ ጠነከረችብኝ " ወይ ኢየሱስህን ወይ እኛን ትመርጣለህ "አለቺኝ " የት መሄጃ አለኝ አንቺ እናቴ ካስወጣሺኝ ሌላ ማን ይቀበለኛል "ብዬ አይኖቿን ትኩር ብዬ አየሁት ሆዷን ባባባው ብዬ እሷም አይኖን ካይኔ እያሸሸች  " አንተስ ልጄ አደለህ የምልህን መስማት የለብህም ነበር ? ፤ ደሞ አንተስ ተበላሸህ አፈንግጠህ ወጣህ ግን እነዚህ ሁለት ምንም የማያውቁ እህቶችህን እንድታበላሽብኝ አልፈልግም ሰሞኑን ቁጭ አድርገህ የምታወራቸው ነገር አላማረኝም ያንተን መስመር እንዳይከተሉ ስጋት አለኝ ስለዚ ይሄ ውሳኔዬ ነው የሚያዋጣህን ምረጥ " አለቺኝ ከእህቶቼ ጋር ያለኝ ....ይቀጥላል

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur