Get Mystery Box with random crypto!

የሚጣፍጥ ስቃይ ተከታታይ ልብወለድ በያኔት ማስረሻ ክፍል ፲፬ @yanetmasra | Christian Mezmur - ክርስቲያን መዝሙር

የሚጣፍጥ ስቃይ

ተከታታይ ልብወለድ
በያኔት ማስረሻ
ክፍል ፲፬
@yanetmasra

ከእህቶቼ ጋር ያለኝ ቅርበት አባቴ ከሞተ በሗላ በትንሹም ቢሆን እየጨመረ መጥቷል እንዲያወሩኝ እንዲቀርቡኝ እድል እየሰጠሗቸው ነበር በዛ ወቅትም 17 አመቴ ሲሆን እነሱ ደሞ ፍቅርተ 14 መሠረት ደሞ 12 አመቷ ነበር እናቴ ስጋት ስለገባት እንጂ ከእነሱጋር ምንም ከዕምነት ጋር የተያያዘ ነገር ነግርያቸው አላውቅም ነበር ሀሳቡም አልነበረኝም ግን እናቴ ካለቺኝ በሗላ እንደውም ለምን አልነግራቸውም ብዬ አሰብኩ እናቴ ብነግራት እንደማትሰማኝ ግልፅ ነው እግዚአብሔር  ካልረዳት በቀር እነሱ ግን ገና አይምሯቸው በማህበረሰቡ ልማድና እይታ ስላልተወረሰ የምነግራቸውን ነገር ሊረድኝና ሁለት ነፍስ ወደ ጌታ ላመጣ እችላለሁ የሚል ሀሳብ ውስጤ ውስጥ ተፀነሰ ግን እንዴት የሚለው ነው ጥያቄው እናቴ ሳታውቅ እነሱን አግባብቼ እንዴት ነው የእግዚያብሄርን ቃል ልመግባቸው የምችለው እንዴትስ ብዬ ወሬውን ልጀምር ? እነዚህን ነገሮች በደንብ ማሰብ እንዳለብኝ ተሰምቶኛል ።

   እንደ ጨዋታ አድርጌ ለበሱፈቃድ አዋየሁት እሱም  " እናትህ የእውነት አምርረው ከቤት የሚያስወጡህ ከሆነ የት እሄዳለሁ ? ፣ የት እገባለሁ ? ብለህ እንዳታስብ  እኔ ለወላጆቼ ነግሬ ከእኛ ጋር ትኖራለህ ቤት የእግዚአብሔር ነው አትጨነቅ የእህቶችህን ነገር ደሞ መላ እንፈልግለታለን በመጀመሪያ ግን አብዝተህ መፀለይ እንዳለብህ አትዘንጋ አንተን ያየ ፣ ያዳነ የጎበኘ ጌታ እነዚ ብላቴና እህቶችህንም እንዲጎበኝ ፀልይ ፤ በነገራችን ላይ እኔም ታናሽ እህት እንዳለኝ ታውቃለህ ? " አለኝ በፍፁም አላውቅም ነበር ነግሮኝም አያውቅም እቤታቸውም ስሄድ ከእሱና ከወላጆቹ በቀር ሌላ አብሯቸው የሚኖር እንኳን ዘመድ አልነበረም " ታድያ እህት ካለችህ የት ሄደች ለምን አብራችሁ አትኖሩም " አልኩት በጣም በመገረም ስሜት ውስጥ ሆኜ እሱም " አብራን ነበር የምትኖረው ይህችን 4 አመት ግን የእናቴ እናት ጋር ሄዳለች



ብቻዋን ስለሆነች አያታችን የምትኖረው ምህረት አብራት እንድትኖርና እንድታግዛት ወላጆቻችን የወሰኑትና እሷም የተስማማችበት ነገር ነው ለክረምት ግን ሁሌ እኛ ጋር ትመጣለች ደሞ በ1 አመት ብቻ ነው የምበልጣት በጣም የምግባባት እና የምወዳት እህቴ ነች ከሁሉም ነገሯ ብልሀቷ ያስገርመኛል " አለኝ "ለምን እናንተስ አያትህ ጋር አትሄድም ወይም ደሞ እናትህ ቢረዷቸው አይሻልም ለእህትህ በልጅነቷ ሀላፊነት ከሚሰጣት ደሞ ባለፈው ክረምት ሳትመጣ ቀርታ ነው ወይስ ሳላያት ቀርቼ ነው አልኩት ነገሮችን ከነ ምክንያትና ውጤታቸው ስር ድረስ ዘልቆ ለመረዳት ያለኝ ጉጉት እና ፍላጎት ጥልቅ ነው " ምን መሠለህ ዩሀንሴ የእናቴ እናት በጣም አክራሪ ኦርቶዶክስ ናቸው ባለቤታቸውም ቄስ ነበሩ እና እናቴ ጴንጤ ሆነች ብለው ልጄ አደለሽም አትድረሽብኝ አልደርስብሽም ተባብለዋል አባቷ በህይወት የሉም እና ከአያቴ  ጋር ያላት  ግንኙነት ጥሩ ስላልሆነ ሲያማቸው ልታስታምማቸው አብራቸው ሆና ልትረዳቸው ስለማትችል ይሄን ለማድረግ ያለው ምርጫ እህቴን መላክ ነው በነገራችን ላይ ይህን ሀሳብ ያመጣችው እራሷ ምህረት ናት አያቴ ሴት ልጅ እንደምትወድ እናታችን ስለምትነግረን ለምን የእሳቸውን እምነት የምከተል መስዬ አልረዳቸውም ? " አለች አባቴ ግን መንፈሳዊ ህይወቷ ላይ ጉዳት ያመጣል ብሎ ስላሰበ መጀመሪያ ላይ አልፈቀደም ነበር እሷም መልሳ " በዚ በኩል ስጋት አይግባችሁ ለጥቂት አመታት በስውር አመልካለሁ በዛላይ አያቴ ያን ይህል ስለማትቆጣጠረኝ ህብረት ለማድረግም ለመፀለይም ይመቸኛል " አለች እናትና አባቴም ተማክረው በመጨረሻ እንድትሄድ ወሰኑ አሁን ድረስ አያቴ በጌታ መሆኗን አታውቅም ግን  ለዛውም ብርቱ ነች በቃ ምን ልበልህ በልጅነቷ በሳልናት እህቴ ስለሆነች አደለም እንዲ የምልህ እና ባለፈው ክረምት አያቴን ትንሽ ስላመማት መምጣት አልቻለችም በአሁኑ ግን ትመጣለች ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ከመጣች አስተዋውቅሀለው " አለኝ ....ይቀጥላል

ለሌሎችም እንዲደርስ #share


     ይ ላ ሉን
@christian_mezmur
@christian_mezmur