2023-05-16 15:21:27
የአብዮታዊው ሰራዊት ጥቁር ቀን
ዝክረ ግንቦት 8 1981 ዓ.ም ያልተሳካና ደም አፋሳሽ የነበረው መፈንቅለ መንግስት ሙከራ
ልክ በዛሬዋ ቀን ከ34 ዓመት በፊት ግንቦት 8 1981 ዓ.ም በከፍተኛ ጀነራል መኮንኖች በፕሬዚደንት ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማርያም ላይ በአዲስ አበባና በአስመራ ላይ ደም አፋሳሽ ሆኖ የተጠናቀቀው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የተደረገበት ዕለት ነው ።
ይህች ቀን በተለይም በአዲስ አበባ እና በአስመራ የመፈንቅለ መንግስቱ መሪዎች እቅዳቸውን ለማስፈፀም የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያምን ለጉብኝት ከሀገር መውጣት ተከትሎ እንቅስቃሴ የጀመሩበት እለት ነበረች ።
የመፈንቅለ መንግስቱ መሪዎች በግንቦት 8 ቀን ረፋድ ላይ አዲስ አበባ አምባሳደር ቲያትር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ሚኒስቴር ህንፃ ውስጥ በኢታማጆር ሹሙ ሜጀር ጀነራል መርዕድ ንጉሴ መሪነት የዕቅዱ አተገባበር ላይ ውይይት ይዘዋል ።
ሌ/ኮ መንግስቱ ሃይለማርያም ወደ ምስራቅ ጀርመን / GDR ለጉብኝት ለመጓዝ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ ገብተዋል ። የመፈንቅለ መንግስቱ መሪዎች የኮ/ል መንግስቱን አገዛዝ ለማስወገድ መከላከያ ሚኒስቴር ህንፃ ውስጥ የዕቅድ አፈፃፀም ውይይት ላይ ነበሩ ።
ጀነራሎቹ "ኮሎኔሉን በአየር ላይ እንዳሉ በአየር ኃይል ጀቶች ይመቱ አሊያም በአየር ኃይል ጀቶች ተገደው አስመራ አርፈው በቁጥጥር ስር ይዋሉ " በሚለው ቁልፍ የመፈንቅለ መንግስቱ ጉዳይ ላይ መስማማት ላይ ሳይደርሱ ፕሬዚደንቱን የያዘቸው አውሮፕላን የኢትዮጵያን የአየር ክልል ለቃ ወጣች ።
አዲስ አበባ ያሉት የጦር መሪዎች እርምጃ ሳይጀምሩ ቀደም ብሎ በታሰበው የአፈፃፀም እቅድ መሰረት አስመራ የነበረው በሁለተኛው አብዮታዊ ሰራዊት ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ደምሴ ቡልቶ የተመራው ኃይል ከአዲስ አበባ በተላከለት መልእክት መሠረት አድርጎ ኮ/ል መንግስቱ እንደተወገዱ ስለተነገረው እሱ መረጃ ይዞ ወደ ማስፈፀሙ ገብቶ መንግስቱ ኃይለማርያም ከስልጣን መውረዱን በአስመራ ራዲዮ አስነገረ ።
አዲስ አበባ ያለውንም እንቅስቃሴ ለመርዳት እና ቁልፍ የተባሉ መንግስታዊ ተቋማትን የራዲዮና ቴሌቭዥን ጣቢያ ፣ አየር ማረፊያ ፣ ቴሌኮሚኒኬሽን፣ የጦር ክፍሎች ፣... ለመቆጣጠር እንዲቻል መቺ ኃይል የሆነውን ኤርትራ የነበረውን 102ኛ አየር ወለዱን በሁአሠ ም/አዛዥ በነበሩት ሜ/ጀ ቁምላቸው ደጀኔ መሪነት ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ ላከ ።
ይሁን እንጂ በኋላ የነገሩን መበላሸት አይቶ የሀይል አሰላለፉን አስተካከለ በተባለለው የደህንነት ሚንስትሩ ኮሎኔል ተስፋዬ ወልደስላሴና በሻንበል መንግስቱ ገመቹ በሚመራው የልዩ ጥበቃ ብርጌድ አማካኝነት የአዲስ አበባው መፈንቅለ መንግስት ሙከራው አመሻሽ ላይ ከሸፈ ። ኮሎኔል መንግስቱም ከምስራቅ ጀርመን ወደ አዲስ አበባ በፍጥነት ተመለሱ ።
የአዲስ አበባው መፈንቅለ መንግስቱ በተለያዩ ምክንያቶች ከጥቂት ሰአታት በኃላ ሲከሽፍ ኢታማጆር ሹሙ ሜ/ጀ መርዕድ ንጉሴ እና የአየር ኃይል አዛዡ ሜ/ጀ አመኃ ደስታ መከላከያ ሚኒስቴር የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ራሳቸውን በታጠቁት መሣሪያ አጠፉ ። የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የነበሩት ሜጀር ጄኔራል ፋንታ በላይ ከሙከራው በኋላ ተሰውረው በፀጥታ ሃይሎች ሲፈለጉ ቆይተው ከሙከራው አራት ቀን በኋላ መከላከያ ሚኒስቴር ግቢ ውስጥ ተሸሽገው ተገኙ ። ጄኔራል ፋንታ ከተያዙ ከቀናት በኋላ እዚያው የታሰሩበት ማዕከላዊ ምርመራ ግቢ ውስጥ ባልታወቀ ምክንያት ተገደሉ ።
ሌላው የመፈንቅለ መንግስቱ ዋና ጠንሳሽ የዘመቻ መምርያ ኃላፊ የነበሩት ሜ/ጀነራል አበራ አበበ ጠንሳሾቹን ለማነጋገር የመጡትን የወቅቱን የመከላከያ ሚኒስቴር የነበሩትን ሜ/ጀነራል ኃ/ጊዮርጊስ ሀ/ማርያምን በሽጉጥ ክፋኛ አቁስለው ከጊቢው በአጥር ተንጠላጥለው አመለጡ ።
1/ ሜ/ጀ ኃይሉ ገ/ሚካኤል - የምድር ጦር ዋና አዛዥ
2/ ሜ/ጀ ወርቁ ዘውዴ - የፖሊስ ሰራዊት ጠቅላይ አዛዥ
3/ ሜ/ጀ ዓለማየሁ ደስታ - የምድር ጦር ምክትል አዛዥ
4/ ሜ/ጀ ዘውዴ ገብረየስ - የ603ኛ ኮር ዋና አዛዥ
5/ ብ/ጀ ደሣለኝ አበበ - የጦር ኃይሎች አካዳሚ ዋና አዛዥ 6/ ብ/ጀ ሰለሞን በጋሻው - የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ
7/ ብ/ጀ ተስፋ ደስታ - የአየር ኃይል ዘመቻ መኮንን
8 ብ/ጀ እንግዳ ወ/አምላክ - የ606ኛ ኮር ዋና አዛዥ /ሁአሰ 9/ ብ/ጀ እርቅይሁን ባይሣ - የ607ኛ ኮር ዋና አዛዥ /ሁአሰ 10/ ብ/ጀ ነጋሽ ወልደየስ - የ 608ኛ ኮር ዋና አዛዥ /ሁአሰ
11/ ብ/ጀ ገናናው መንግሥቴ - የ6ኛው አየር ምድር ዋና አዛዥ /ሁአሰ
12 ብ/ጀ ተስፋዬ ትርፌ - በአገር መከላከያ ሚኒስቴር ዘመቻ መኮንን
መፈንቅለ መንግስቱን ለማክሸፍ በተንቀሳቀሰው በሻንበል መንግስቱ ገመቹ በተመራው የልዩ ጥበቃ ብርጌድ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ ። በመጨረሻም ከአንድ አመት የጦር ፍ/ቤት ሂደት በኃላ ግንቦት 13/1982 ዓ.ም በፖለቲካዊ ውሳኔ ተረሸኑ ።
የሁአሠ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ የመሩት የአስመራው የመፈንቅለ መንግስቱን የሶስት ቀናት እድሜ አስቆጥሮ ነበር ። ሙከራው መክሸፋ ተከትሎ የ102 ኛ አየር ወለድ ወታደሮች ጀነራል ደምሴን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ መኮንኖችን በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት እየደበደበና በጭካኔ እናነቀ በዘፈቀደ ፈጃቸው ።
የዘመቻ መምሪያ ዋና ኃላፊ የነበሩት ሜ/ጀ አበራ አበበ መፈንቅለ መንግስቱ ከተካሄደበት መከላከያ ሚኒስቴር ግቢ አጥር ዘሎ አምልጠው ለወራት ሲፈለጉ ከቆየ በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኝ የዘመዱ ቤት ውስጥ ተደብቀው ቆይተው በጥቆማ ፖሊሶች ደርሰውባቸው ቤቱ ሲከበብ ሜ/ጀ አበራ አጥር ዘሎ ለማምለጥ ሲሞክሩ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ ።
መቺ ሀይል ከአስመራ በአንቶኖቭ ጭነው አዲስ አበባ የመጡት ሜ/ጀ ቁምላቸው ደጀኔ የነገሮች መበላሸትና የግንኙነት መስመር ስለተቋረጠባቸው ተሠውረው በመቆየት ከሀገር በሙውጣት በመጨረሻ አሜሪካን ገቡ ። ዋና ተዋናይ ሆነው ብቸኛ በህይወት የተረፋ ጀነራልም መኮንንም እሳቸው ብቻ ናቸው ።
ከሁለተኛው አብዮታዊው ሰራዊት ዋና አዛዥ ሜ/ጀ ደምሴ ቡልቶ ጋር በአስመራ ከተማ በ102ኛ አየር ወለድ ክፍለ ጦር ህይወታቸው በአሰቃቂ ና በዘፈቀደ ሁኔታ ህይወታቸውን ያጡት ስመጥር ጀነራሎች እና ሌሎች መኮንኖች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
1/ ብ/ጀ አፈወርቅ ወ/ሚካኤል = የኤርትራ ክ/ሃገር የአስቸኳይ ጊዜ ዋና አስተዳዳሪ
2/ ብ/ጀ ታዬ ባላኪር = የኤርትራ ክ/ሃገር አቢዮታዊ ፖሊስ ዋና አዛዥ
3/ ብ/ጀ ታደሰ ተሰማ = የሁአሰ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
4/ ብ/ጀ ወርቁ ቸርነት = የሁአሰ ፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ
5/ ብ/ጀ ንጉሴ ዘርጋው = የአስመራ አየር ኃይል ዋና አዛዥ
6/ ብ/ጀ ከበደ መሀሪ = የሁአሰ ድርጅት መምሪያ ኃላፊ
7/ብ/ጀ ተገኔ በቀለ = የኤርትራ ክ/ሃገር የአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር ዘመቻ መኮንን
8/ ብ/ጀ ከተማ አይተንፍሱ = የ 606ኛ ኮር ዋና አዛዥ
1.6K views12:21