Get Mystery Box with random crypto!

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

የቴሌግራም ቻናል አርማ bookshelf13 — ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖
የቴሌግራም ቻናል አርማ bookshelf13 — ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖
የሰርጥ አድራሻ: @bookshelf13
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.28K
የሰርጥ መግለጫ

"ስለመጻሕፍት ከመጻሕፍት መንደር እንዘምራለን!"

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 51

2022-07-08 08:49:30 ያልታተመው መግቢያ
(የቀጠለ)

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን በአንደኛው ቴያትሩ ላይ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን እንደ ባህሪ ስሎ የሚከተለውን እንዲሉ አድርጓቸዋል። ጃንሆይ አዲስ አበባ ወህኒ ቤትን ሲመርቁ የሚናገሩት ነው። “…የአባታችን እርስተ-ጉልት የሆነውን ይህንን የአገር ወህኒ ቤት መርቀን ስንከፍትላችሁ፣ እናንተም በተለመደው ባህላችሁ እንድትተሳሰሩበት በማሰብ ነው!” ከእነዚያ እዋሻው ክፍሎች ውስጥ ከታጐሩት ሰዎች ማህል እንደብረቱ መዝጊያ ብረት ልብ ያላቸው አሉ። ከጥጥ የተሠራ ይመስል የሚሳሳ፣ የሚባዘት፣ የሚዳወር፣ የሚበጫጨቅ ልብ ያላቸውም አሉ። ከጥጡ እስከ ብረቱ ልብ ያላቸውን ሰዎች ሁሉ ያ የብረት መዝጊያ በዐይነ-ቁራኛ ይጠብቃቸዋል። ለአንዳቸውም አልራራ ባይ ነው። አልፎ አልፎ መርጦ ከሚያስወጣቸው በቀር። የየክፍሉ የብረት በር አንዳንዴ ገርበብ ብሎ ይከፈትና ትንሽ አየር ይመፀውታቸዋል። ሲያሰኘው በደምብ ብርግድ ብሎ ይከፈትና በሙሉ ሳምባቸው አየር እንዲተነፍሱ ይፈቅድላቸዋል። አንዳንዴ ደግሞ ጠባቂው ከከፋው፣ ወይም የጠባቂው ጠባቂ ከከፋው፤ ወይም ሌላኛው ጠባቂ የሚኖበት ሰፈር ሰላም ካልሆነ፣ የ የብረት መዝጊያጥርቅም ብሎ ይዘጋና ‘አትተንፍሱ! አትናፈሱ! አትጠጉኝ! ዋ ዛሬ ሁልሽም ቀንሽ ደርሷል!’ ይላል። ብረት መዝጊያው አንዳንዴ ተአምር ይሠራል። ጠባቂዎቹን በጥበብ ከጣራው ያወርዳቸውና እክፍሉ ውስጥ አስገብቶ ያስቀምጣቸዋል። ከእስረኛ ይቀላቅላቸዋል። ጠባቂውን ተጠባቂ ያደርገዋል! እስረኛ ዜጋ! በየክፍሉ የሚኖሩት ዜጎች የራሳቸው የአኗኗር ዘዴ አላቸው። ማህበራዊ ኑሮ ይባላል። የዛው ዋሻ መከራና ረሀብ የፈጠሩት ኑሮ ነው። በየትኛው ዘመን እንደተመሠረተ ባይታወቅም የመጀመሪያዎቹ፣ ከቤቱ ከዋሻው ጋር የተሠሩት እስረኞች፣ የፈጠሩት ሳይሆን አይቀርም የሚል ጠንካራ ግምት አለ። አብሮ ይበላል። አብሮ ይጠጣል። አብሮ ይተኛል። አብሮ ይወጋል። አብሮ ይነጋል። ህይወትም በዚህ ዓይነት አብሮ ይገፋል። በለስ ካልቀናም አብሮ ይሞታል! ማህበራዊ ህይወትና ማህበራዊ ሞት የዚያ ዋሻ ዜጐች ተገደው የፈቀዱት ደምብ ነው። ከአብሮ መኖሩ ጋር ሀሳብን ለመክፈል ሲባል መጨዋወትና መዝናናት አይቀርም። የስቃዩ ዋሻ ከአብራኩ ፌሽታን የሚወልድበት ጊዜ አለ። ከምጥ በኋላ እልል ማለትን ሰው ያውቅበት የለ? ታዲያ ሲዝናኑ የውጪውን ዓለምም ይረሱታል። ህልማቸውም፣ ቅዠታቸውም ከዋሻ ህይወታቸው ጋር የተሳሰረ ነው። ህልምም ይታሰራል ለካ! ሐምሌት በጋሽ ፀጋዬ ገብረ መድኅን አንደበት እንዲህ ይለናል።
«መሆን ወይስ አለመሆን፣ እዚሁ ላይ ነው ችግሩ
የዕድል የፈተና አለንጋ፣ ሲወናጨፍ ወስፈንጥሩ
በሀሳብ ግርፊያ መሰቃየቱን፣ ችሎ ታፈነ ማደሩ
ወይስ የፈተናውን ማዕበል ተጋፍጦ ጦሩን ከጦሩ ተጋትሮ ወግቶት ድል መምታት እስኪነቀል ከነሥሩ
የቱ ነው ለሰው ልጅ ክብሩ
መሞት፣መተኛት፣ማንቀላፋት፤
እስከመቼም ላለመንቃት
የሚጸለይለት ሲሳይ ነው፣ የምኞት ሁሉ አናት።
ለእንቅልፍ ሲባል መሞቱ
በሞት እፎይታን ማግኘቱ፤
የሰላም ህልም ማየቱ
ህልም አልኩ እንዴ? እሱ ነው ጉዱ!! በሞት የእንቅልፍ ዓለም ደሞ፤ የሕልም ወግና ሽርጉዱ፤ ቢኖር የሰላን ድባብ፣ የጸጥታን እሹሩሩ የሚያውክ ዓይነት አይሆንም፣ ይታገዳል መጻረሩ
ይሄ ሟች ጉፋያ ስጋ ሲደመደም መቃብሩ
እዚያ ላይ ይገታል ክብሩ!
ኑሮ የሚሉት ውጥንቅጥ፣ እንቅልፍ ላይ ነው ድንበሩ?...››

ይቀጥላል…
3.3K views05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ