Get Mystery Box with random crypto!

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖

የቴሌግራም ቻናል አርማ bookshelf13 — ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖
የቴሌግራም ቻናል አርማ bookshelf13 — ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖
የሰርጥ አድራሻ: @bookshelf13
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 16.28K
የሰርጥ መግለጫ

"ስለመጻሕፍት ከመጻሕፍት መንደር እንዘምራለን!"

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 50

2022-07-14 09:33:38
1.4K views06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 09:32:04 ያልታተመው መግቢያ
(የቀጠለ)

ይኸውም ከሰውነት ሁሉ ጠባቡ ስፋት ያለው በጐን በኩል ነውና በሰያፍ የሚተኛበት ዘዴ ፀደቀ። ስሙንም “ጩቤ ስክ” አሉት። የሰው ስለቱ ተገኘና ስም ወጣለት ማለት ነው። ይሄ ስክ የሚል ቃል አገልግሎቱ እንደ እስር ዘመኑ ስፋትና እንደመጪው ዜጋ ብዛትና ትጋት ተስፋፋና መጽሐፍ ለማንበብም ዋና ዘዴ ሆነ። የቀኑ ሃያ አራት ሰዓቶች በየአንድ አንድ ሰዓት ሃያ አራት ቦታ ይሸነሸኑና ሃያ አራት ሰው ይመደብባቸዋል። እያንዳንዱ ሰው አንድ አንድ ሰዓት ይደርሰዋል። በዚሁ ጊዜ ሰዓቷን ሳያባክን ያነብባታል። እንግዲህ በቀኑና በማታው ጊዜ ውስጥ ሃያ አራት የመጽሐፍ ስክ አለ ማለት ነው። በዚህ ዓይነት የንባብ ስክ ሥርዓት ከፍተኛ የመነበብ ዕድል በማግኘት ብትንትኑ እስኪወጣ ድረስ በመጉላላቱ፣ እፈተና ላይ የወደቀ ታላቅ መጽሐፍ፣ የማርጋሬት ሚሼል ጐን ዊዝ ዘ ዊንድ ነበር። ዘመነኛ ጓደኞቹ የሆኑት መጻሕፍት በሁለት በሦስት ዓመት ጡረታ ሲወጡ፣ እሱ በታተመ በሰላሳ ስድስት ዓመቱ፣ የወላጅ እናቱን የማርጋሬትን ዕድሜ ተሸክሞ፣ ጥቁር ከነጭ ፀጉር ካበቀለ በኋላ እንኳ ጭራሽ ጉርምስና ተሰምቶት የቀኑ አልበቃው ብሎ ይሄው ሌሊቱን ሙሉ ከእጅ ወደ እጅ ሲዞር፤ ሲነበብ ያድራል። ሰዓት-እላፊ አያቅ! ዘመን-እላፊ አያቅ! ድንበር-እላፊ አያቅ! እንዲሁ የጊዜና የቦታ ኬላ እንደጣሰ ኖሮ፣ ይኸው ይባስ ብሎ እስር ቤት ድረስ ገብቶ የዜጎቹን እንቅልፍ ይነሳል! በዚህ ሁኔታ እንቅልፍ ካጡት ዜጎች ማህል እኔ አንዱ ነኝ። ማንበብ ከጀመርኩበት እስከ ጨረስኩበት ሰዓት ድረስ አገሬን አገሬን እንደሸተተኝ ቆየ። ደግሜ ስክ ገባሁ። አነበብኩት። ከዜጐች ጋር ተወያየሁበት። በጣም ወደድነው። በደምብ ካነበብኩት፣ ከወደድኩት፣ የሥነ-ጽሑፍ ችሎታው ካለኝና ከሁሉም በላይ ደግሞ ባገሬ ዋሻ ውስጥ እያለሁ አገሬን አገሬን ከሸተተኝ የማልተረጉመው ሞቼ ነው ቆሜ? ደሞስ ከመቶ ሃያ ዓመታት በፊት ሌላ አገር ውስጥ የታየ ጦርነትና አስከፊ ውጤቱ፣ ዛሬ እኔ አገር ላይ ሲዘንብ እያየሁ ይህን መጽሐፍ በአማርኛ አንብቦ ይረካ ዘንድ፣ ላላየ ወገኔ ዐይንና አእምሮ ብሆነው፤ ብሞትስ ብቆምስ ግዴታዬም፣ ዓላማዬም አይደል እንዴ? እስክሞትም ይሁን እስክቆም መተርጐም አለብኝ ብዬ፣ ግጥምና ቴያትር ከመጻፍ አልፌ ወደ ረዥም ልብወለድ ትርጉም ተሸጋገርኩ። ትርጉም ሥራውን ለመጀመር ያነሳኋቸው አምስት ጥያቄዎች በጣም ጠጣር ነበሩ። እዋሻው ውስጥ ነኛ! የራስ ነፃነት ሳይኖር ለሌላው ነፃነት ለማሳየት ሲፍጨረጨሩ አቤት ያለው ሳንካ! አቤት ያለው እንቅፋት! አቤት ያለው በወንጀል ላይ ወንጀል የማከል ስጋት! ለመጻፍ የሚያስፈልገኝን ቅድመ ሁኔታ ለማሟላት የተወሰኑ መሠረታዊ ጥያቄዎችን መመለስ ነበረብኝ። የመጀመሪያው ጥያቄ በምን ሰበብ ልጻፍ? መጻፍ አይፈቀድማ! ሁለተኛው ጥያቄ በምን ላይ ልጻፍ! ወረቀት አይገባማ! ሦስተኛው ጥያቄ በምን ልጻፍ? እስክሪቢቶ ከቤት ተጠሪው እጅ አይወጣማ! የተሾመልን ቤት ተጠሪ ደግሞ ዋናውን ለራሱና ለኢኮኖሚ ተጠሪው በስተቀር አንዳያውል ለመንግሥት ቃል የገባ፤ የመንግስት አደራ የማይበላ፣ አፍቅሮተ - መንግስት እልቡ ውስጥ እንደ ጧፍ የሚነድ ጓድ ነው! -ያውም ግለሰብ ነው እንጂ አብዮት አላሰረኝም ››የሚል! አራተኛው ጥያቄ የትጋ ሆኜ ልፃፍ ነው? - ቦታ የለማ! አምስተኛው ጥያቄ ፅፌስ መውጫ መንገድ የለማ! ፍቺም ሆነ ግማሽ ፍቺ ቢገኝ ከጥፍር እስከ ጠጉር ተፈትሾነው የሚወጣው። አንድ ሺ ሃያ አራት ገፅ ያለው መፅሀፍ ተደክሞ ተተርጉሞ (መቼም የገፁ ብዛት ከኦርጅናሌው መብለጡ አይቀርም) ምን ሊኮን ነው?

ይቀጥላል…
1.6K views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 09:31:26
1.6K views06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 15:30:36 ያልታተመው መግቢያ
(የቀጠለ)

የዳማ፣ የቼዝ፣ የዶሚኖ ውድድር ይዘጋጃል! ቢንጐ ጨዋታ ይደራል! - በሲጋራ ካርቶን ሠንጠረዡን ሠርቶ፣ የብርቱካን ልጣጩን ቆራርጦ የሠንጠረዡን ቁጥሮች በልጣጭ እየደፈነ ቢንጐውን ይከሰክሳል! ኧረ ብዙ ጨዋታ ይፈጥራል! ሞኖፖሊ ሁሉ ተሠርቷል! ሞገደኛ እስረኛ! እጅ እግሩን በካቴና፣ በፌሮና በእግረ ሙቅ ቢጠፍሩት፤ “አንጐሌን አላሳስር!” ብሎ በር ተዘግቶበት፣ የስንት ጠባቂ አፈሙዝ ተደግኖበት እንኳ፣ የውጪውን ዓለም ጨዋታ እንደልቡ ይጫወታል። ተው ሲሉት በጄ አይል - እሩቅ አገር ይሄዳል! ሌላው መዝናኛ መጽሐፍ ነው። መጽሐፍ በዛ ቢባል በዚያ ዋሻ ውስጥ ሁለት ወይ ሦስት መጽሐፍ አለ። ለዛ ሁሉ ዜጋ መቼም ገጽ እየተበጨቀ ካልተሰጠ በቀር ለንባብ ማዳረስ አይቻልም። ስንት የተጠማ ዐይን፣ ስንት የተጠማ አዕምሮ እዚያ ታጅሎ ሁለት መጽሐፍ እንዴት ትብቃው፣ ወንድሜ?። ያም ሆኖ ሰው መች ዘዴ ያጣል? በስክ ያነበዋል።

"ስክ"
“ስክ” የዋሻው ውስጥ መዝገበ-ቃላት ያፈራው ታላቅ ቃል ነው። ያው የመከራ ምጥ የወለደው መግባቢያ! ልክ እንደተናጋሪዎቹ! አመጣጡ እንደሚከተለው ነው፡- ክፍሉ ጠባብ ነው። ዜጋው ብዙ ነው። የቆዳ ስፋትና የሕዝብ ብዛት አልተመጣጠኑም። ያለ ፕላን እያሠሩ ምርቱ በዝቶ መጋዘኑ ተጣቧል። ብቻ ምን ያደርጋል ሰውም ሠራ የሚባለውን ወንጀል በፕላን አይሠራ! እንዳመቸው ይሯሯጣል፤ ሳይዘጋጅ ይታሠራል። መች ተማረ! ኢትየጵያ ውስጥ ማንስ ከማን መች ልማር ይላል? ዝም ብሎ አዳሜ በየተራ ይታሠራል። ይቀፈደዳል። ታዲያ ያ የተትረፈረፈ ዜጋ ማታ ልተኛ ሲል ስንቱ ሊተኛ! ቦታ የለም። እንግዲያው መላ ምቱ ተባለ። መላ ተመታ። ዘዴ ተገኘ። በፈረቃ እንተኛ ተባለ። ተፈራርቆስ መች ሆነ? ያለፕላን የሚታሰረው ታሳሪ ዜጋ በላይ በላዩ ሲመጣ፣ በፕላን የሚተኛውን ፕላነ-ቢስ ያደርገዋል። በዚህ ምክንያት በተቻለ ተጣቦ የመተኛት የመጨረሻው የቦታ ቁጠባ ፕላን ተነደፈ። ጐጆ እሚባል የቦታ ሽንሸና ተመሠረተ። አንዱ የእስር ክፍል አራት ሜትር በአራት ሜትር ይሆናል። /4X4/ አራት ጐጆ ወይም አምስት ጐጆዎች ይኖሩታል ማለት ነው። አራቱ ጐጆዎች የክፍሉን ዜጋ ሁሉ በእኩል ተካፍለው ያስተናግዳሉ። የሚነጠፈው አንሶላ የጐጆው ነው። የሚለበሰው ብርድ ልብስ የጐጆው ነው። እያንዳንዱ ዜጋም የጐጆው ንብረት ነው። ጐጆው የክፍሉን አንድ አራተኛ ክልሉን ጠብቆ ለመተዳደር እጅግ ተጠጋግቶ መተኛት ነበረበት። ተተኛ። ታዲያ እራስ ለራስ ተገናኝቶ ሲተኙ ብዙ ቦታ መያዝ መጣ። ለዚህ ሌላ መፍትሔ ተገኘ! እራስጌና ግርጌ እየሆኑ መተኛት። አንደኛው ያንደኛውን እግር አቅፎ መተኛት። ትንሽ ትንፋሽ ተገኘ። ስሙንም ስክ አሉት። ሰው እንደጨፈቃ ተጨፍቆ፣ ሰው በሰው ማህል ተሰክቶ፣ የሚያድርበት ዓለም! የስክ አተኛኘት ተደርጎም ሙሉ ለሙሉ ጥበቱ አልተወገደም። እንደገና ተሰብስቦ መላ ተመታ። በጀርባ ወይም በደረት መተኛት ዋና የቦታ ጠር ነው ተባለ - በተግባር ታየ። እውነት ሆነ። ሁልህም በጐን በጐንህ ተኛ - ይዞታህ በጐንህ ስፋት ልክ ነው የሚል ህግ ወጣ።

ይቀጥላል…
2.3K views12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 15:30:09
1.8K views12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 15:27:24
ከታላላቆቹ ጎራ ናቸው። በስነፅሁፍ ድንበር ላይ በመረማመድ በጦር ሜዳ ጋዜጠኝነት፣ በገጣሚነት፣ በደራሲነትና ሃያሲነት ውስጥ በምልዓት ተመላልሰዋል— Abera Lemma።
የአጫጭር ልብወለድን አፃፃፍ ስልት ከፍ ወዳለ ደረጃ ካደረሱ ፈር–ቀዳጆች መሃል ይመደባሉ። የቀድሞውን የካቲት መፅሔት ጨምሮ በግል በግጥም ስራዎች፣ በተናጥልና ጋራም በታተሙ የአጭር ልብወለድ ስራዎች("አባ ደፋር"ን ዋቢ ያደርጓል) ውስጥ በመሳተፍ፣ እንዲሁም "ሙያዊ ሙዳዬ ቃላት" በማዘጋጀት በኢትዮጵያ ስነፅሁፍ ውስጥ ሊጠፋ የማይችል አሻራ አሳርፈዋል።

የሳንሱር ጫና ከሚበረታባቸው ከዋነኞቹ ደራሲያን መካከል ነበሩ። ሩዶልፍ ኬ ሞርቪየር በጥቋቁር አናብስት ስራው ተራማጅ እና አዲስ ስልትን ለመፍጠር ከጣሩ ውስጥ ይመድባቸዋል።

መቆያ ፤ ሕይወትና ሞትና፤ የማለዳሥንቅ የተሰኙ የአጭር ልቦለድ ስብስቦቻቸው ከገበያ ርቀው ቆይተዋል። አሁን እነዚህ ስራዎች በአንድ ተሰንደው የደራሲው የአጭር ልቦለድ ስራዎቻቸው በሙሉ "ትውስብ" በተሰኘ ድርሳን ለህትመት በመብቃት ወደገበያው ሊቀላቀሉ ቀናት ይቀራሉ። ለስነፅሁፍ አፍቃሪያንና ለስነፅሁፍ ተማሪና አጥኚዎች በሙሉ ይህ ትልቅ አጋጣሚ ነው።

Surafel Ayele
1.8K views12:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 15:24:02
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
(በነጻ)

•••

ልዩ መርሐግብር:- መጽሐፍ የማስፈረም: ከደራስያን ጋር የመተዋወቅና የመጨዋወት ልዩ ሥነስርዓት::

የዕለቱ የክብር እንግዳ አለማየሁ አረዳ(phd)

የተመረጠው መጽሐፍ:- ምሁሩ

የመርሐግብሩ አሰናጅ:- ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ እና ዋልያ መጻሕፍት::

ቦታ:- አራት ኪሎ: ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ: ኢክላስ ህንጻ ዋልያ መጻሕፍት::

ቀን:- ቅዳሜ: ሀምሌ 9: 2014: ከሰዓት በኋላ ከ10:00 እስከ 12:00 ድረስ:: (በሰዓቱ ይጀመራል)

(https://t.me/waliabooks)
ማስታወሻ::

1) እንዲህ ዓይነቱ ፕሮግራም ቀጣይነት ያለው ነው::

2) ከዚህ ቀደም የተደረጉ መሰል ፕሮግራሞችን ለመከታተል በዋልያ ቡክ ስቶር ቻናል ያገኙናል።

( https://m.youtube.com/channel/UCT2s8ZltG5kIS6Q1n7NGGxw)

Surafel Ayele
1.9K views12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 09:07:04 ያልታተመው መግቢያ
(የቀጠለ)

እዋሻው ሆድቃ ሲገቡ ብዙ ነገር ይረሳል። ቤት ንብረት ይዘነጋል። ሠርግና ቀብር ይረሳል። የቅርብ የስጋ ዘመድም በየቀኑ ስንቅ ባያመጣ ኖሮ መረሳት አይቀርለትም ነበር! ከሁሉ ነገር ይልቅ፣ ከሰውም ይልቅ ዜጎቹ ሁሉ የማይረሱት የታሰሩበትን ጉዳይ ነው። እራስ አይረሳማ! ከራስ በላይ ንፋስ… ወይም ከራስ በላይ ጠባቂ ነው! እንግዲህ በዜጎቹ አኗኗር ውስጥ ካሉት ህግጋት ውስጥ፡- የኢኮኖሚ ህግጋት፣ የአመጋገብ ህግጋት፣ የጤና አጠባበቅ ህግጋትና የመዝናናት ህግጋት አሉ። ሁሉም ህግጋት ደህና ፀሐፊ ቢያገኙ ወደል ወደል መጽሐፍ ይወጣቸዋል። እኔ ለመግቢያ ያህል የመዝናናቱን ነገር፣ ለ‹‹ነገም ሌላ ቀን ነው›› በሚበጀኝ መልኩ ባጭሩ አነሳዋለሁ። በየክፍሉ የሚኖሩት ዜጐች የመዝናኛ ተጠሪ የሚባል አንድ ሰው ይመርጣሉ። በዛ ዘመን እንደዛሬው የግቢ መዝናኛ ኮሚቴ አልነበረም። የግቢ መዝናኛ ኮሚቴ አሁን በቅርቡ የተፈጠረ ነገር ነው። ለመላ ግቢው አንድ አጠቃላይ ኮሚቴ የተቋቋመው ከጊዜ በኋላ ነው። ስለዚህ አሁን የምናወራው የአንዱን ክፍል ተጠሪ ጉዳይ ብቻ ነው። የመዝናኛ ተጠሪ ዋንኛ ኃላፊነቱ አዲስ ሰው ሲመጣ በዘልማድ በየፖሊስ ጣቢያው እስር ቤት “የሻማ” እየተባለ የሚጠራውን ከውጪው ዓለም /ከሞላ ጐደል ከተመቸ ኑሮ የመጣ ነው ተብሎ የሚታመነውን አዲስ ገቢ/ (ያው ለወጉ ‘እንኳን ደህና መጣህ’ ለማለት) የቤቱን ሰው ይሰበስብና ሁለት ዓይነት ጥያቄዎች ይጠይቀዋል። አንዱ የኢኮኖሚ፣ አንደኛው የመዝናኛ። የኢኮኖሚ የሚባለው እነዚያ ከአንድ ወር እስከ አራት - አምስት ዓመት ዋሻው ውስጥ የቆዩ ዜጎች ይበሉት ምግብ፣ ይለብሱት ልብስ፣ ይጫወቱት ቀልድ የሌላቸው በመሆናቸው ካዲሱ ዜጋ ጥቂት ምጽዋት ብናገኝ ብለው “እጅህ ከምን?” የሚሉበት ዘመናዊ ልመና፤ ግን ከህልውና ሊነጠል የማይችል ጉዳይ፣ ነው። አዲሱ ሰው የዜግነት መታወቂያውን ለማግኘት ለነባሮቹ ዜጎች አቅሙ የፈቀደውን ለመርዳት ቃል ይገባል። የደነገጠ ዘመድ - ወዳጅ ገንዘብ ሲልክለት የቃሉን ይፈጽማል። ሌላኛው ጉዳይ መዝናኛ የሚባለው ሲሆን አዲሱ ዜጋ ከኢኮኖሚው ጥያቄ ባላነሰ ሁኔታ ማሟላት ያለበት ግዴታ ነው። ወይ መዝፈን፣ ወይ መቀለድ፣ አሊያም ሰውን ጥቂት ያጫውታል፣ ያዝናናል የሚለውን ማናቸውንም ነገር መናገር ነው። የራሱንም አስገራሚ የህይወት አጋጣሚ ቢሆን! ይህን ሲፈጽም ሙሉ ዜጋ ይሆናል። የውጪውን ዓለም ዜግነቱን ሽሮ፣ የዋሻውን ዓለም ዜግነት ያገኛል። የመኖሪያ ፈቃዱን ይወስዳል። የመታሰር መብቱን ያስከብራል። የመታሰር ሊቼንሳውን ይረከባል፤ ማለት ነው። ከዚያ ወዲያ ነፃነት የሚባል ነገር፣ እንደልብ መሆን የሚባል ነገር የት አግኝቶት?! በሰላም ጭብጥ፣ ኩርምት ብሎ ዓመታቱን ይገፋል። ያ ምልዐተ - እስረኛ ገበያ ቀዝቅዞ ወደ ዋሻው የሚገባ ሰው ሲጠፋ አዲስ ወሬ የሚያመጣለት፣ አዲስ ፊት የሚያሳየው፣ አዲስ እርጥባን የሚለግሰው ትኩስ ዜጋ ያጣ ጊዜ፣ አቤት ያለ ዐይን ማፍጠጥ! አቤት ያለ ድብርት! አቤት የሰው ረሀብ! አቤት መሰላቸት! ደግነቱ ዜጋ ሆዬ ከረጅም ጊዜ ልምዱ በመነሳት እርስ በርስ ተፋጠን ከምንሰለቻች ጨዋታ እንፍጠር! ከምንደበር መላ - መትተን ጊዜ እንግፋ ይላል! ለዚህ እንግዲህ ቴያትር ያዘጋጃል /ባይፈቀድም ውስጥ ውስጡን ተስማምቶ ድምፁን አጥፍቶ ይሠራዋል/ ግሩም ቲያትር! እዚያው የክፍሉአስረኛ እያየ እየሰማ ተሠርቶ፤ በኋላ በል ውጣና አንድ አንድ ብር እየከፈልክ እንደታዳሚ ግባና እይ የሚባልበት ኮሚክ ነገር ነው - ቴአትር! ዋናው ነገር ቴአትሩ የዕውነት ቴአትር ነው። እኔም የዕውነት ተመልካች ነኝ ብሎ የማመን ጉዳይ ነው! ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል!

ይቀጥላል…
2.6K views06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 09:05:51
2.2K views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 06:33:55
በመላው ዓለም ሆናችሁ 1443ተኛውን የኢድ-አላድሃ (ዓረፋ) ክብረ-በዓል በማክበር ላይ ያላችሁ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን እንኳን አደረሳችሁ። አደረሰን።
ኢድ-ሙባረክ!

ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf ቻናል

@Bookshelf13 @Bookshelf13
@Bookshelf13 @Bookshelf13
2.9K views03:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ