2023-07-20 21:20:41
እምልህ…ጥሩ ነው። ማለፊያ ነው— የክብሩ ዶክትሬት።
We should celebrate this Man. Let's celebrate him through condemning our acts.
ይሄን ሰው በቅጡ ሰለብሬት ለማድረግ ያደረገውን ጠቅሰህ መሸለም አይደለም። በትክክለኛው መንገድ ልትወድሰው፤ ልታከብረው ካሻህ—ሲያደርግ የነበረውን ጠቅሰህ መሸለም ሳይሆን— ስታደርግ የነበረውን ጠቅሰህ ማውገዝ— ያ ነው ሀቀኛው መንገድ።
እንዴት? ጥሩ። Let's dive in to some depth Psychology.
① ስታደርግ የነበረውን ነገር ቆም ብለህ በድፍረት ተጋፈጠው።
ሀቀኛ ከሆንክ— You will find yourself being one of the Sadists in your society.
ወሲብ ላይ ብቻ እንዳይመስልህ። ማህበራዊ መስተጋብር ውስጥም እንዲሁ— ሳዲዚም በሌሎች ስቃይ ደስታን የመግዛት ግብር፣ ልምምድ፣ ዝንባሌ ነው።
{አስታውስ!}
ከዕለታት ብዙ ቀኖችን በመንገድ ላይ በተመፅዋች ለምታየው የከፋ ጉዳት፤ አሰቃቂ እክል ብሮችና ሳንቲሞች ወርውረህ አልፈሀል።
የመጀመሪያውን ጊዜ ለማየት የዘገነነህን ያህል ቀጣዮቹን ጊዜያት ተመሳሳይ ስሜት አታሳድርም።
አትሸሽም። መንገድ አትቀይርም። ልበደንዳናነትን ትለማመደውና ጥቂት ሳንቲሞች በመወርወር "ትራጄዲውን ከፍለህ" መመልከት ዝንባሌህ ይሆናል።
ጥቂት ምፅዋትህ ላንተ Instant moral relife ያድልሀል። ያንን የሞራል ረፍት ዓለማዊ ወይም መንፈሳዊ ትርጉም ስለምታበጅለት ግብርህ "ልክ" ሆኖ ይሰማሀል።
የተመፅዋቹ በነበረበት ቀጥሎ ለውጥ አለማሳየቱ በአንድ ጥግ ያንተን ሳዲስትነት ያረጋግጣል። ልብ ካልከው።
② ዙሪያህን ከተከላክሎ ሥልት(Defense Mechanism) ወጥተህ ተመልከተው። ተመፅዋቹን ተመልከት።
"ቸግሮኛል እርዱኝ" የሚለው ሃሳብ ብቻውን ተዓማኒነትን ስላጣ የልቦናችንን የመጨረሻ የጭካኔ ጥግ ለመፈታተን በማህበረሰቡ የማይፈቀዱ( taboo) የሰውነት ክፍሎች ሳይቀር ቆስለው ና ክፉኛ ተጎድተው ፀሃይ ላይ እየተሰጡ ሰዎች በግድ ኪሳቸውን እንዲፈትሹ ያስገድዳሉ።
አንተም "የሞራል እፎይታ" አግኝተህ ደስ ባይልህ እንኳን እንዳዘንክ እንዳትውል ያህል ምፅዋት ትሰጣለህ። You trade pleasure from others's wound. ሳዲስት።
ተመፅዋቹ በአንፃሩ በመሰቃየት፣ በመጎሳቆልና እና ተሸማቅቆ በመታየት ምቾቱን ይገዛል። ይሄ ደግሞ Masochism ነው—The enjoyment of an activity that appears to be painful or tedious.
③ Let's all Celebrate the only sane personality among us.
እናውግዝ። የገዛ ማንነታችንን። ያኔ አንድ ሰው ይገዝፋል።
እኛ ሁላችን— ማህበራዊ በሆነ መንገድ Sadomasochism ውስጥ ነበርን!
ደስታን ስንገዛ የነበረው አንድም የሌሎችን ቁስል በማየት፤ አንድም የገዛ ቁስላችንን በመነገድ ነው። ይሄን ማመን አለብህ።
④ ይሄን ጊዜ የሚገንን አንድ ሰው አለ።
ሳምራዊው አይደለም። የኛ ምድር ላይ ያለ አንድ ሰው። ምናልባትም ትክክለኛው "የሰውኛ ተፈጥሮ ልክ" ላይ የሚገኝ። ተፈጥሮ ያኖረችለት :
☞ርህራሄ
☞ ፍቅር
☞ ክብር
☞ ሌሎችን እንደራስ ማየት
☞ በሌሎች ጉዳት /ሃዘን የመጎዳት /የማዘን
☞ በሌሎች ደስታ ሃሴት የማድረግ ባህርይ ስሜትና አመለካከት በሙሉ ዛሬም ድረስ ጢም እንዳሉ ሞልተው የምናስተውልበት።
ሰው ስንሆን ቢኒያምን የምንሆን ያህል ነን፣ ከሰውኛ አውድ ስንጎድል ደግሞ ልክ እንዲህ እንዳሁኑ!
Surafel Ayele
2.2K views18:20