2022-08-31 08:45:47
#ሃይማኖተ #አበው #ክፍል #ስድስት
--------ዘጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት-------
+
=> ምዕራፍ ፲፫:- ጎርጎርዮስ ማለት ንቁ የተጠበቀ /ዕቁብ ንቁሕ ማለት ነው።
=> ጎርጎርዮስ ብዙ ተአምራትን ያደርግ ስለነበረ ገባሬ መንክራት ተብሏል።
=> ቦርፎሪኮን የሚባለው ነቢያት ከእግዚአብሔር የሰሙት ዝርው ቃል ነው። አአትሪኮን የእኛ የሰዎች ቃል ሲሆን ዝርው ነው። አተርጋዎን የሚባለው ቃልም ዝርው ቃል ነው። (ወልድን ቃል ስንለው ግን አካላዊ ቃል መሆኑን መረዳት አለብን። ክርስቶስ ራሱ አካላዊ ቃል ነው። ክርስቶስ ለሐዋርያት ሲያስተምራቸው ከአንደበቱ ይወጣው የነበረው ቃል ግን ዝርው ቃል ነው። ይኽውም ከቦርፎሪኮን ጋር ይመሳሰላል)።
+
=> የወልድ ከአብ የተወለደው ልደቱ አይፈጸምም። (ይህም ማለት ሁልጊዜ ሲወለድ ይኖራል ማለት አይደለም። ወልድ ወልድ ሲባል ይኖራል ማለት ነው። አያልቅም ማለቱ እናት ልጇን ስትወልድ ከማኅጸኗ የነበረው ይወጣል። ወልድ ከአብ ተወለደ ስንል ግን በዘመን ሳይቀድም ከህልውናውም ሳይለይ ስለሆነ ተመትሮ የለበትም ለማለት ነው)።
=> ለአንድ ሰው ልብ ቃል እስትንፋስ እንዳለው ሥላሴም በአንድ ልብ አስበው በአንድ ቃል ተናግረው በአንድ እስትንፋስ ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ።
=> ሥላሴ በአካል ሦስት በመለኮት አንድ ናቸው።
=> ክርስቶስ ከሁለት አንድ የሆነ ነው።
=> የወልድ ከአብ መወለድ እንዴት እንደሆነ አይመረመርም። ይኽውም ከሰው መረዳት በላይ ስለሆነ ነው።
=> ምዕራፍ ፲፬:- በባህርይው የማይታይ እግዚአብሔር ሰው ሆኖ በሥጋ ታየ። ይኽም ሲሆን በመለኮቱ ፍጹም ነው። እግዚአብሔር እኛን ለማዳን እግዚአብሔርነቱን ሳይለቅ ሰው ሆነ።
+
---------ዘጎርጎርዮስ ዘአርማንያ--------
ምዕራፍ ፲፭:- ይህ ጎርጎርዮስ ሰማዕት ዘእንበለ ደም እየተባለ ይጠራል። የአርማንያው ንጉሥ ድርጣድስ በሃይማኖት ምሰለኝ ቢለው ጎርጎርዮስ ሃይማኖቴን አለቅም በማለቱ ከአዘቅተ ኩስሕ (ሽንት ቤት) አስጥሎታል። በዚያም ሲጣል ያየች ሴት ምግቡን በገመድ አስራ እያላከችለት ፲፭ ዓመት ኖረ። በኋላ ንጉሡ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ ብሎ ቅድስቲቱ ደግሞ እምቢ ብትለው አስገደላት። ከዚያ በኋላ መልኳን እያሰበ አእምሮውን ነስቶት እያለ ለአደን እንደሄደ እሪያ ሆኖ ቀረ። ደግ እህት ነበረችው ማን ባዳነልኝ ስትል መልአክ መጥቶ ጎርጎርዮስ ነው የሚያድንልሽ አላት። እርሷም ጎርጎርዮስማ የዛሬ ፲፭ ዓመት ጉድጓድ ውስጥ ተጥሎ ሞቶ የለምን አለች። እንዳልሞተ ነገራት። ከጉድጓዱ ሄዳ አስወጣችው። መልኩ ከሰል መስሎ ወጣ። ድርጣድስንም አሳምኖ አስጠምቆታል። ንጉሡም ጎርጎርዮስን ኤጲስ ቆጶስነት እንዲሾም አመልክቶ ማመልከቻው ተቀባይነት አግኝቷል።
=> ኢየሱስ ክርስቶስ ያለወንድ ዘር ከድንግል ማርያም ተወለደ።
=> እግዚአብሔር ወልድ ሰው ሲሆን መለኮትነቱ ወደ ሰውነት አልተለወጠም። ሥጋን ስለተዋሐደም ሕጸጽ አላገኘውም።
=> ጣዖት ቀርጸው ያመልኩ ለነበሩት (የጣዖትን ከንቱነት አሳይቶ) ለጌትነቱ ሥራ ይገዙ ዘንድ (እነርሱ በሚያስቡትና ሊያዩት በሚፈልጉት) በሰው ባሕርይ ተገኘ።
916 views05:45