2022-10-04 19:21:23
__የመልካም ሰው ጸባይ
_፩) ማንንም የሚያስቀይም ንግግር አይናገርም።
፪) ሁልጊዜም ለእኛ ለሕይወታችን መርሕ የሆነውን የእግዚአብሔርን ሕግ ይጠብቃል።
፫) የሰውን ድካም ስለሚያውቅ በማንም ቂም አይዝም። በማንም አያዝንም። ይልቅስ ያንን ይቅር ብሎ ለወደፊቱ መልካም ግንኙነት ያስባል።
፬) ጥፋቱን በንሥሓ እና በይቅርታ ያርማል።
፭) ኃጢዓትን እንጂ ኃጢዓተኛን አይጠላም።
፮) ሰውን በሰውነቱ ያከብራል ይወዳል እንጂ በቀለሙ፣ በጾታው፣ በእድሜው፣ በተወለደበት ሰፈር፣ በዝምድና እና በመሳሰሉት እያለ አይለያይም።
፯) እውነትን ይወዳል።
፰) በእግዚአብሔር እንጂ በሌላ አይመካም።
፱) ንሥሓ እየገባ የክርስቶስን ሥጋውን ደሙን ይቀበላል።
፲) ይጸልያል፣ ይጾማል፣ በሁሉ ነገር ፈጣሪውን ያመሰግናል፣ ሌላውን ሰው እንደራሱ ይወዳል፣ ይመጸውታል።
፲፩) ሥጋዊ ክብርን ከንቱ ውዳሴን እና ተርእዮን ይጠላል።
፲፪) ራሱን የሚመዝነው በእግዚአብሔር ሕግ ነው።
፲፫) ትሑት ነው፣ ታጋሽ ነው፣ ራሱን የገዛ ነው።
፲፬) እግዚአብሔርን ይፈራል።
፲፭) ለሁሉም ሰው መልካም ያስባል፣ መልካም ያደርጋል።
።
እስኪ በእናንተ እይታስ መልካም ሰው የምትሉት እንዴት ዓይነቱን ነው? ጨምሩበት። እና እንማማር።
። እግዚአብሔር መልካም ሰው እንድንሆን ይርዳን።
1.3K views16:21