2022-09-26 08:21:30
_ኒቁስጣኑ ኒቁስጣጣኑ
_በዓለመ መላእክት ሳጥናኤል ቅዱሳን መላእክትን በገጠማቸው ጊዜ ያሸነፉት በረቂቅ ክንፋቸው የነበረውን መስቀል አሳይተው በረድኤተ እግዚአብሔር ነበር። መስቀል የአሸናፊነት ምልክት ነው።
።
መስቀል በኋላም ክርስቶስ ሰይጣንን ከምድር ከፍ ከሰማይ ዝቅ አድርጎ ያሰቃየበት አደባባይ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም መዳን ደሙን ያፈሰሰበት መስቀል ነው። ቅዱስ ያሬድ በድጓው መስቀል ሞዐ ሞት ተሞዐ ብሏል። መስቀል አሸነፈ ሞት (ዲያብሎስ) ተሸነፈ ማለት ነው።
።
ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ በሰማይ ኒቁስጣኑ ኒቁስጣጣኑ ተብሎ ተጽፎ አየ። በእኛ ሀገር ትርጉም በዚህ መስቀል ጠላቶችህን ታሸንፋለህ ማለት ነው። ንጉሡም ከጦሩ የመስቀል ምልክትን አድርጎ ከመክስምያኖስ ጋር ጦርነት ቢገጥም መክስምያኖስን አሸንፎታል። ስለዚህ መስቀል አሸናፊ ነው።
።
ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀሉ ተአምር እያደረገ ስህተታቸውን ስለገለጠባቸው አይሁድ ቀበሩት። በኋላ ግን ንግሥት ዕሌኒ አረጋዊው ኪራኮስን (ኪሪያኮስን) አማክራ ከተቀበረበት ከ300 ዓመታት ገደማ በኋላ አውጥታዋለች። ደመራ አስደምራ በደመራው ዕጣን ጨምረችበት። ጢሱም ከፍ ከፍ ብሎ መስቀሉ የተቀበረበትን አሳየ። በዚህ መልኩ ተቆፍሮ ወጥቷል። ዘዕጣን አንጸረ ሰገደ ጢስ መባሉ ለዚያ ነው።
።
ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ይቅር አለን። ነገረ መስቀሉን ሁልጊዜም እናስበው ዘንድ መሓሪ እግዚአብሔር ይርዳን።
1.1K views05:21