Get Mystery Box with random crypto!

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

የቴሌግራም ቻናል አርማ betremariyamabebaw — በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw
የቴሌግራም ቻናል አርማ betremariyamabebaw — በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw
የሰርጥ አድራሻ: @betremariyamabebaw
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.24K
የሰርጥ መግለጫ

አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 73

2022-09-21 11:42:44 ደስታ
አራት ዓይነት ደስታዎች አሉ። እነዚህም:-
            ፩) ፍሥሓ መላእክት
            ፪) ፍሥሓ ኖሎት
            ፫) ፍሥሓ ቍንጽል (የቀበሮ ደስታ)
            ፬) ፍሥሓ መስቴማ
ናቸው። ፍሥሓ መስቴማ ማለት የሰይጣን ደስታ ማለት ነው። ሰይጣን ሌሎች ሰዎች ሲሳሳቱ፣ ሲወድቁ፣ ሲሞቱ፣ ሲጎዱ በጣም ይደሰታል። በሌሎች ሰዎች ኀዘን እና ጉዳት የሚደሰቱት ደስታ የሰይጣን ደስታ ይባላል። ሁለተኛው የደስታ ዓይነት የቀበሮ ደስታ ነው። ቀበሮ የጣዝማ ማር ስታገኝ ከደስታዋ ብዛት የተነሳ ማሩ እስኪጠፋት ትዘላለች። የደስታዋ ምንጭ የሚበላ አገኘሁ ብላ ነው። የሰው ልጅ በሥጋዊ ነገሮች የሚደሰተው ደስታ የቀበሮ ደስታ ይባላል። ሦስተኛው ደስታ የእረኞች ደስታ ነው። እኒህም ጌታ በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ የተደሰቱት ደስታ ነው። ይህ ደስታ ነፍሳዊ ደስታ ነው። በጌታ መወለድ በሲኦል ተግዞ የነበረ አዳም ወደ ገነት የሚመለስበትን የምሥራች ከመልአኩ የሰሙበት ነውና። እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘይከውን ፍሥሓ ለክሙ እንዲል። የመላእክት ደስታ የፍጹማን ደስታ ነው። መላእክት አንድ ኃጥእ ንሥሓ በገባ ጊዜ በሰማያት ታላቅ ደስታ ይሆናል ተብሎ የተነገረላቸው ናቸው። የመላእክት ደስታ ከግላዊ ጥቅም የተለየ ደስታ ነው። ሌላው ሲጠቀም፣ ሌላው ሲያገኝ፣ ሌላው ሲሾም፣ ሌላው ሲደሰት የሚደሰቱት ደስታ ነው። እንግዲህ ገላ. ፭፣፳፪ ደስታ የመንፈስ ፍሬ ነው የተባለው በሁለቱ ዓይነት ደስታዎች ነው። እነዚህም ፍሥሓ ኖሎት እና ፍሥሓ መላእክት ናቸው። ትክክለኛው ደስታ የሚገኘው በቁስ አይደለም። በእግዚአብሔር ነው። መዝ. ፺፬፣፩ "ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን" ተብሏል። ቅዱስ ጳውሎስም በመልእክቱ ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ብሏል። በሌላ ቦታ ቅዱስ ዳዊት "ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ" ብሏል። ደስታ የሚገኘው ከእግዚአብሔር ቤት ነውና። ደስታ የራቃችሁ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ። ያን ጊዜ ደስ ይላችኋል። ሰማእታት እየተገደሉ ግን ደስተኞች ነበሩ። ለምንድን ነው ስንል የደስታቸው ምንጭ እግዚአብሔር ስለሆነ ነው። እግዚአብሔር ደግሞ ሕይወተ ሕይወት ብርሃነ ብርሃን መሠረተ መሠረት ስለሆነ ነው። ደስታችንን በእግዚአብሔር እናድርግ።
                           ።
የመንፈስ ፍሬዎችን በአጭር በአጭር ተማምረን ጨርሰናል። አነሳስቶ ላስጀመረን፣ አስጀምሮም ላስፈጸመን ልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይገባል።
3.0K views08:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 09:08:41 ፍቅር የአንዱን ድካም አንዱ ሲሸከም ነው። ሰማዕትነት የሌለበት ፍቅር ፍቅር አይባልም። በአፍ ብቻ እወድሃለሁ እወድሻለሁ ማለት ውሸት ነው። ይህንንስ ባላገሩ "የአፍ ዘመድ ከገበያም አይገድ" ብሎ ተርቶበታል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሐ. ፲፭፣፲፫ "ነፍሱን ስለወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም" ብሎ የፍቅርን ትርጓሜ አስተማረን። ፍቅር በአፍ የሚናገሩት ብቻ አይደለም በሕይወት የሚኖሩትም ነው እንጂ። ለዚያም ነው ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን በቃል ከተናገረ በኋላ በተግባር ደግሞ አዳምን ለማዳን በመስቀል የተሰቀለ። መስቀል ፍቅር በተግባር የተገለጠበት አደባባይ ነው። ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት ብሎ ሊቁ የገለጠው ይህንን ነው። ፍቅር ራሱ እግዚአብሔር ነው። ፩ኛ ዮሐ.፬፣፰-፳ "ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም እግዚአብሔር ፍቅር ነውና----ማንም እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው" ይላል። ይህ የሚነግረን በፍቅር ጥላቻ እንደሌለ ነው። ፍቅር ሌላውን እንደ ራስ መውደድ ነው። ማቴ. ፯፣፲፪ "ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው" ተብሎ እንደተጻፈ ሰውን መውደድ በእኛ ሊደረግብን የማንፈልገውን በሌላውም እንዲደረግ አለመፈለግ ሲሆን እግዚአብሔርን መውደድ ደግሞ ትእዛዙን በመፈጸም ይገለጣል።ዮሐ. ፲፬፣፳፩ "ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው" እንዲል።
√√√
√√√
ማቴ. ፯፣፳፩-፳፫ "በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን ይሉኛል። የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም እናንተ አመፀኞች ከእኔ ራቁ ብየ እመሰክርባቸዋለሁ" እንዲል የጌታን ስም ብዙ ጊዜ ብትጠራ፣ በስሙ ተአምራትን ብታደርግ፣ በስሙ ትንቢትን ብትናገር፣ በስሙ አጋንንትን ብታወጣ ይህ የፍቅር ምልክት ተደርጎ አይያዝም። እግዚአብሔርን የመውደድ ዋናው ምልክቱ ፈቃዱን መፈጸም ነው። ፈቃዱ ምንድን ነው ከተባለ ዘጸ. ፳፣፩ ጀምሮ ያሉ አስሩን ሕግጋት መፈጸም ነው። ማቴ. ፲፱፣፲፯ "ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ" እንዳለ። ዮሐ. ፲፪፣፶ "ትእዛዙም የዘለዓለም ሕይወት እንደሆነች አውቃለሁ"እንዲል።
√√√
√√√
ቅዱስ ጳውሎስ ፍቅርን ጠቅለል አድርጎ ሲያቀርበው እንዲህ ብሎታል። ፩ኛ ቆሮ. ፲፫፣፪-፰ " ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድኾችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም። ፍቅር ይታገሣል፣ ቸርነትንም ያደርጋል፣ ፍቅር አይቀናም፣ ፍቅር አይመካም፣ አይታበይም፣ የማይገባውን አያደርግም፣ የራሱንም አይፈልግም፣ አይበሳጭም፣ በደልን አይቆጥርም፣ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለዓመፃ ደስ አይለውም። ሁሉን ይታገሣል፣ ሁሉን ያምናል፣ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፣ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም" ብሎ ገልጾታል።
2.5K views06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 08:26:04 እምነት አካሌን የሰጠ፣ የሚያስፈልገኝን ነገር ሁሉ የፈጠረ እግዚአብሔር እስከ ዕለተ ሞቴ ይመራኛል ብሎ ሙሉ ተስፋን በእግዚአብሔር ላይ ማድረግ ነው።እምነት ካለመኖር የፈጠረኝ እግዚአብሔር በመግቦት ያኖረኛል ብሎ ቁርጥ ሀሳብን ለእግዚአብሔር መስጠት ነው። ብዙዎቻችን እምነት የለንም። እምነት ያለው ሰው ስለምንም አይጨነቅም። ከምንም በላይ የሆነው እግዚአብሔር አለኝ ብሎ በልቡ ስለሚያምን የሚያሳስበው የሚፈራው እና የሚያስጨንቀው ጉዳይ አይኖርም። እምነት ከመንፈስ ፍሬዎች አንዱ ነው። ገላ. ፭፣፳፪። እምነት ያለው ሰው ተስፋ አይቆርጥም። ምክንያቱም ምንም ዓይነት ፈተና ውስጥ ቢኖር እግዚአብሔር በጥበቡ ከዚያ እንደሚያወጣው ተስፋ ያደርጋልና። እምነት ያለው ሰው እንደ ዳንኤል አንበሳ ጉድጓድ ውስጥ ሊጣል ይችላል። ነገር ግን እግዚአብሔር አንበሶች እንዳይበሉት ያደርጋል። እምነት ያለው ሰው ሰማዕት ሊሆን መከራ ሊደርስበት ይችላል። ነገር ግን ከሁሉም የምትበልጠውን መንግሥተ ሰማያት ያገኛል። መዓልትና ሌሊትን፣ ክረምትና በጋን እያፈራረቀ የሚመግበን የሚያኖረን እግዚአብሔር ስላለን አንፈራም አንጨነቅም። ሰው እምነት እያጣ ሲሄድ ይጨነቃል፣ ያዝናል። ነገር ግን ከእኛ የሚጠበቀውን የድርሻችንን እየተወጣን ረድኤተ እግዚአብሔርን እየጠየቅን በተስፋ እንኑር። እምነታችን አይጉደል። ቀድሞ ቅዱሳንን የረዳ እግዚአብሔር ነው። አሁንም ያለው ራሱ ነው። እኛንም ይረዳናል። ይረድአነ አምላክነ ወመድኃኒነ። አምላክነሰ አምላከ አድኅኖ። ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ። እግዚአብሔርን በሙሉ ልባችን እንመነው። መልካም የሆነውን ሁሉ ያደርግልናል።
2.3K views05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 18:54:06
ከምጽፈው ጽሑፍ ጥያቄ ካለ በፌስቡክ ገጼ(በሚሴንጀር) መጠየቅ ይቻላል። ማንኛውም ሃይማኖታዊ ጥያቄ ካለ መጠየቅ ይቻላል። የፌስቡክ ገጼ https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው። የቴሌግራም ግሩፕ ልከፍት ነበር። መሰዳደብ ስለ በዛ ትቼዋለሁ። በፌስቡክ ገጼ መጥታችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ።
2.4K views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 17:06:33 ራስን ከመግዛት የበለጠ ንጉሥነት የለም። ራስን መግዛት በምን ከተባለ በእግዚአብሔር ሕግ ነው። ራስን መግዛት ስሜታችንን አሸንፎ እውነት በሆነው ቃለ እግዚአብሔር መመራት ነው። ከስሜት በላይ መሆን ነው። ነፍስን በሥጋ ላይ ማሰልጠን ነው። ራስን በራስ መቆጣጠር ነው። ለሰውነታችን ሕግ መሥራት ነው። ዓይናችን ክፉ እንዳያይ፣ ጆሯችን ክፉ እንዳይሰማ፣ እጃችን ክፉ እንዳይዳስስ፣ ምላሳችን ክፉ እንዳይናገር፣ አፍንጫችን ክፉ እንዳያሸት መቆጣጠር ነው። አንድ ነገር ክፉ የሚባለው ፍጻሜው የእግዚአብሔርን ሕግ ወደመሻር የሚያደርስ ከሆነ ነው። ዓለምን ከመግዛት ራስን መግዛት ይበልጣል። ራሱን የገዛ ሰው ፍጻሜው መንግሥተ ሰማያት ነውና። ንዴትን፣ ሐሜትን፣ ቁጣን፣ ስሜትን መግራት ነው። አርምሞ (ዝምታ) አንደበትን ለመግዛት ዋናው መሳሪያ ነው። የፈቲው ጾርን (አመንዝራነትን) ለማስወገድ መጾም፣ ውሃ አለማብዛት እና እንቅልፍን መቀነስ ዋና መድኃኒቶች ናቸው። ራሳችንን በጾም፣ በጸሎት መግራት መልካም ነው። ራስን መግዛት ከመንፈስ ፍሬዎች አንዱ ነው። ገላ. ፭፣፳፪።

ኑ በራሳችን ላይ እንንገሥ (ንጉሥ እንሁን)።
2.3K views14:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 15:58:51 በጎነት ለራስም ለሌላውም መልካም መሆን ነው። ደግነት እና ቅንነት ይመሳሰሉታል። ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ሲባል ለመልካም ነው ለማለት ነው። የመልካምነት መለኪያው የእግዚአብሔር ቃል ነው። አንድ ሰው በጎ የሚባለው እንደ እግዚአብሔር ቃል ሲኖር ነው። በሌሎች ሰዎች ክፉ አለማድረግና ለሌሎች ሰዎች መልካም ማድረግ በጎነት ነው። ስለሌሎች ሰዎች ጥሩ አስተያየት አነጋገር ካለው በጎ ነው ይባላል። ብናጠፋ፣ ብንበድል እንኳ እግዚአብሔር ፈጥኖ አያጠፋንም። ለእኛ በጎ ስለሆነ የንሥሓ እድሜን ይሰጠናል። እንዲህ ከሆነ ታድያ አንዳንድ ክፉዎችን እግዚአብሔር ፈጥኖ የሚያጠፋቸው ስለምንድን ነው? ቢባል ቢቆዩ ኃጢዓትን አብዝተው ስለሚሰሩ በሰማይም ፍዳቸው ይቀንስ ዘንድ ቶሎ ያጠፋቸዋል። አንዳንድ መልካሞችንስ ወዲያው የሚያጠፋቸው ለምንድን ነው? ከተባለ ከቆዩ ኃጢዓት ሊሰሩ ይችላሉና። በአሁኑ ጽድቃቸው ዋጋቸውን ለመስጠት ነው። አንዳንድ መልካሞች ብዙ ዘመን ይቆያሉ ለምንድን ነው? ከተባለ ለክብር የሚያበቃቸውን ሥራ አብዝተው ይሰሩ ዘንድ እና ለኃጥዓን ተግሣጽ ይሆኑ ዘንድ ነው። አንዳንድ ክፉዎችን ደግሞ ብዙ ያቆያቸዋል ለምንድን ነው? ቢሉ የሰሯት መልካም ሥራ ካለች እርሷን በዚህ ምድር በድሎት እንዲኖሩ አድርጎ በሰማይ ፍዳቸው ይበዛ ዘንድ ነው። አንዳንድ ኃጢዓተኞች በዚህ ምድር ደስተኛ ሆነው ይኖራሉ አንዳንድ ኃጢዓተኞች ደግሞ በዚህ ምድር በመከራ ይኖራሉ ለምንድን ነው? ከተባለ። በዚህ ምድር ደስተኛ የሆኑት እንደ ነዌ በሰማይ ፍዳቸው የሚበዛ ሰዎች ናቸው። በዚህ ምድር ኃጢዓተኛ ሆነው በመከራ የሚኖሩት ደግሞ የኃጢዓታቸውን ፍዳ ጥቂቱን በዚህ ምድር ስለተቀበሉ በሰማይ ይቀልላቸዋል።ድኃው አልዓዛር በዚህ ምድር ለምን ተሰቃየ ቢሉ ምንም እንኳ ጻድቅ ቢሆን ሰው ከድንግል ማርያም በስተቀር ጽነት አያጣውምና ለዚያ ፍዳውን በዚህ ምድር ተቀብሎ በሰማይ ዋጋው ይበዛለት ዘንድ ነው። ሰው በዚህ ምድር እስካለ ድረስ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ስለማያውቀው ሁልጊዜም ለሁሉም ሰው በጎ ሊሆን ይገባል። አንዳንዱን በደለኛ እግዚአብሔር ወዲያው ይቀስፈዋል ለምን ቢሉ በሕይወተ ሥጋ ላሉት ምሳሌ ይሆን ዘንድ ነው። አንዳንዱን በደለኛ እግዚአብሔር በዚህ ምድር ያቆየዋል ለምን ቢሉ ንሥሓ ይገባ ዘንድ ነው። በማንኛውም ጊዜ በማንኛውም ቦታ በማንኛውም ሁኔታ በጎ እንሁን።
2.4K viewsedited  12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 14:10:59 ቸርነትን ግእዙ "ምጽዋት" ይለዋል። ከተቀባዩ ምንም ሳይፈልጉ የሚሰጡት ስጦታ ነው። አሁን ያሉ የኢትዮጵያ የአብነት መምህራን በችግር ተምረው ያገኙትን እውቀት በነጻ ያስተምራሉ። እውቀት ይመጸወታል። ገንዘብ ይመጸወታል። ጉልበትም ይመጸወታል። ሁሉም የቸርነት ሥራዎች ናቸው። ቸሩ እግዚአብሔር እንዲምረን እኛም ቸር እንሁን። ሰው በቸርነት ፈጣሪውን ይመስላል። እግዚአብሔር ቸር ስለሆነ እኛነታችንን፣ አካላችንን፣ ተፈጥሮን ሰጥቶናል። ከዚህ በኋላ በታናናሾች አድሮ ምጽዋትን እየተቀበለ ሰማያዊ ዋጋን ይሰጠናል። በኋላ በምጽአት ጻድቃንንና ኃጥዓንን ሲለይ በዋናነት የሚጠይቀው ቸርነትን (ምጽዋትን) ነው። ብራብ አብልታችሁኛል፣ ብጠማ አጠጥታችሁኛል፣ ብታረዝ አልብሳችሁኛል፣ እንግዳ ብሆን ተቀብላችሁኛል፣ ብታመም ጠይቃችሁኛል፣ ብታሰር አስፈትታችሁኛል የሚሉት ቃላት ምሥጢራቸው ቸርነት ነው። ምጽዋት (ቸርነት) ሰው ፈጣሪን የሚመስልበት መልካም ሥራ ነው። ፈጣሪ ሁሉን በነጻ እንደ ሰጠን የሚመጸውት ሰውም ፈጣሪ ከሰጠው ጸጋ በነጻ የሚሰጥ ነው። ቸርነት (ምጽዋት) በከንቱ ዘነሳእክሙ በከንቱ ሀቡ ያለውን የሐዋርያውን ቃል በተግባር ማዋል ነው። ቸርነት ሰው ሌላውን ሰው እንደራሱ ከመውደዱ የተነሳ የሚደረግ የመንፈስ ፍሬ ነው። ለዚያ ነው ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች የመንፈስ ፍሬዎችን ሲነግራቸው አንዱ ቸርነት ነው ያላቸው። ገላ. ፭፣፳፪። የቸርነት ሥራዎች ለከንቱ ውዳሴ ከዋሉ ዋጋ አያሰጡም። ጌታ ሲያስተምር ቀኝህ የሰጠችውን ግራህ አትወቅ ምጽዋትህ ሰው ይይልኝ ብለህ ሳይሆን በስውር ይሁን ያለን። አሁን ሰው መጽውቶ በማኅበራዊ ሚዲያ ካልተነገረለት ይከፋል። መምህር አስተምሮ ማስተማሩ በሁሉ ካልታወቀለት ይከፋዋል። ቸርነትና ውዳሴ ከንቱ አይስማሙም። በአደባባይ ከመወደስ በአደባባይ መሰደብ ይሻላል። ቸሩ መድኃኔዓለም ይቅር እንዲለን ቸርነትን ገንዘብ እናድርግ።
2.2K views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 12:26:49 ቅድስት ድንግል ማርያምን ሰላማዊት ይላታል። ልጇም ሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ ይባላል። አንድ ሰው ውስጣዊ ሰላም ይሰማኛል ሲል ብትሰማው የሐሳብ ስምምነት የአእምሮ ዕረፍት እንዳገኘ ትረዳለህ። ውስጣዊ ሰላም የሕዋሳቶቻችን ስምምነት ውጤት ነው። ሰላም ተሳለመ_ተፈቃቀረ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ዘመድ ዘር ነው። ሰላም ፍቅር ማለት ነው። ምሥጢራዊ ትርጓሜው ግን ከተሰናእዎ ጋር ይቀራረባል። የነገር እና የሐሳብ ስምምነት ማለት ነው። ሰላም ሆነ ማለት ስምምነት ላይ ተደረሰ ማለት ነው። አምላከ ሰላም ክርስቶስ ሰላምን እሰጣችኋለሁ ብሏል። ለሰውነታችን የተስማማች ገነትን ሰጥቶም አረጋገጦልናል። ሲኦል ግን ለእኛ ሰውነት የማይስማማ ቦታ ነው። በሲኦል ሰላም የለም። ሁከት ብጥብጥ ዋይታ ለቅሶ ይበዛል። ውስጣዊ ሰላም የሚገኘው በድለን ከነበረ ንሥሓ ገብተን ኃጢዓታችንን አስወግደን መልካም ሥራ ስንሰራ ነው። ነገር ግን ሌላውን እያስቀየምን፣ እያናደድን፣ እየተሳደብን ውስጣዊ ሰላም ይሰማናል ብንል ውሸታም እንባላለን። ነቢዩ ኤርምያስ እንደተናገረው "ወይቤሉ ሰላም ሰላም ወአልቦ ሰላም" እንዳሉት ሐሰተኛ ነቢያት እንሆናለን። የልቡና ሰላም የሚገኘው እውነትን ፍቅርን ትሕትናን ስንይዝ ነው። ፍጹም ሰላማዊት ወደ ሆነችው መንግሥተ ሰማያት ለመግባት ከተጣላናቸው ጋር በይቅርታ ታርቀን፣ የበደልነውን ክሰን በፍቅር እንኑር።

ክርስቶስ ሰላምን የሰጠን በደላችንን ይቅር ብሎ ነው። እኛም በትክክለኛ ፍትሕ ያጠፋው ክሶ፣ የተበደለው ተክሶ በሰላም እንኑር። ውስጣዊ ሰላም ለማግኘት ከፈለጉ የተጣሉትን ይታረቁ፣ ቂም በቀል ጥላቻ ዘረኝነት ካለብዎ ያስወግዱ። ከእርስዎ የሚጠበቀውን መልካምነት ያድርጉ። የድርሻዎትን ይወጡ። ከመንፈስ ፍሬዎች አንዱ ሰላም ነው። ገላ. ፭፣፳፪።
2.3K views09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 17:02:45 የጥያቄዎች መልስ
1ኛ) ሀ
2ኛ) ለ
3ኛ) መ/ለ
4ኛ) ለ
5ኛ) መ
6ኛ) ሀ
7ኛ) ሐ
8ኛ) ሐ
9ኛ) ሐ
10ኛ) ሀ
11ኛ) ለ
12ኛ) መ
13ኛ) መ
14ኛ) ሀ
15ኛ) ለ
16ኛ) ለ
17ኛ) መ
18ኛ) ሀ
19ኛ) ሠ
20ኛ) ሐ
21ኛ) ከረኀብ ጦር ይሻላል።
22ኛ) ከረሱት ሁሉ ይረሳል።
23ኛ) እውነት ያሸንፋል
24ኛ) እጸድቃለሁ ብየ ባዝላት
25ኛ) የፍቅር ኃይል ከሁሉ ይበልጣል።
701 views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ