2022-09-07 08:40:45
#ግእዝ #ክፍል #ስልሳ #ስምንት
'ሁ፣ኑ፣እንጋ' ወይ፣ን ይሆናሉ። "ሁ" እመን ሶበን ይዞ ይነገራል። "ኑ" በስምና በእርባ መካከል ይነገራል። "እንጋ" ሁን ምን ይከተላል። ሲገቡም ዘመጽኡ ሰብአ ሰገል ሶበሁ ተወልደ ክርስቶስ ይላል ትርጉሙ ሰብአ ሰገል የመጡ ክርስቶስ ቢወለድ ነውን? /ነው ወይ? ይላል። ተወልደኑ እንጋ ይላል ትርጉሙ ተወልዶ ይሆንን ይላል።
+
ዘንድ አንቀጽ 'ከመ'ን ይዞ ሳይዝም መፍትው፣ ድሎት፣ ጽድቅ፣ ፍትሕ፣ ርትዕ፣ ሥርዐት፣ ኩነት፣ ርቱዕ በማሰሪያነት ሲነገሩ ባለቤት ይሆናል። ምሳሌ መፍትው ከመ ያድኅኖ ለአዳም አምላክ ይላል ትርጉሙ አምላክ አዳምን ያድነው ዘንድ ይገባል ይላል። ያድኅኖ የዓረፍተ ነገሩ ባለቤት ነው። አምላክ የዘንድ ባለቤት ነው።
+
እመ፣ሶበ፣ከመ ባለቤት ይሆናሉ። ከመ ሲገባ ተነግረ በነቢያት ወተሰብከ በሐዋርያት ከመ አንተ በአብ ወአብ ብከ ይላል ትርጉሙ አብ በአንተ አንተም በአብ እንዳለህ በሐዋርያት ተሰበከ በነቢያትም ተነገረ ይላል። ሶበ ሲገባ እምኄሶ ለሰብእ ሶበ ይምሕር/ከመ ይምሕር ነዳየ ወይገብር ሰናየ ይላል ትርጉሙ ለሰው ለነዳያን ቢመጸውት መልካምንም ቢሰራ ይሻለው ነበር ይላል። ኄሶ በእም የታገዘ ማሰሪያ አንቀጽ ነው። እም ደግሞ ማሰሪያ አገዝ ነው።
+
በመካከል ሆነው የሚቆጥሩ የሚጠቀልሉ "ህ" እና "እ" ናቸው። በዘር በነባር ይቆጥራሉ ይጠቀልላሉ። ልዕልና ትሕትና ሲል ይጠቀልላሉ ይቆጥራሉ። ድርድሮች የወ ሳድስ የየ ራብዕ ከሆኑ ይቆጥራሉ ይጠቀልላሉ። አዕዋም፣ አውያን ይላሉ። አይቴ፣ ባሕታዊ ይቆጥራሉ ይጠቀልላሉ። "አ" በራሱ ሳድስ ተደርድሮ ድርድሩን የረ፣ የነ፣ የደ፣ የጸ ካዕብ የጸ ሳድስ የበ ራብዕ ሲቀበላቸው ይቆጥራሉ ይጠቀልላሉም። አዕጹቅ፣ አዕኑግ፣ አዕጽምት፣ አዕሩግ፣ አዕባን፣ አዕዱግ ይላል።
+
የሀገር ስም ሰው ሲያመጣ ለሴት ለወንድ ለአንድ ለብዙ ይሆናል። ምሳሌ ወተፈሥሑ ግብፅ በጸአቶሙ ግብፆች (እስራኤላውያን) በመውጣታቸው ተደሰቱ ይላል።
+
በ'ወ' የጨረሰ እርባ ሳድስ ቅጽሉ ካዕብ ቀለም የለውም። ፍትው፣ ድልው፣ ውርዝው ይላል።
+
"ቀ፣ተ፣ደ፣ጠ፣ጸ" ከሴቲቱ ሳድስ ቅጽል ሲደርሱ ቀለማቸውን ያጠብቃሉ። ተ ሲያጠብቅ ምውት፣ ትሕት ይላል። ደ ሲያጠብቅ ዋሕድ፣ ንእድ ይላል። ጠ ሲያጠብቅ ሥልጥ ይላል። ቀ ሲያጠብቅ ጥምቅ፣ መጥምቅ ይላል። ጸ ሲያጠብቅ ሕንጽ፣ ድንግጽ ይላል።
+
የሚበዳደሩ ቀለማት ስምንት ናቸው እነዚህም ኈ፣ ቈ፣ ኰ፣ ጐ፣ ኀ፣ ቀ፣ ከ፣ ገ ናቸው። ለምሳሌ ከ ሲበደር ተኬነወ-ብልሀት ሰራ ብሎ ኵናት ይወጣል። ኰ ሲበደር ለሐኰ-ፈጠረ ብሎ ለሐኮ-ፈጠረው ይላል። ሌሎችም እንዲሁ ነው።
+
በቀተለ ቤት በወ ተነስቶ በማናቸውም ሲደርስ መስም ቅጽሉ ይጠብቃል መነሻው አይፈርስም። መወልድ መወርድ ማለቱን ያሳያል።
+
1.2K views05:40